የህንድ ፓርላማ ሴቶች በሙሉ ክፍያ የሚወጡትን የወሊድ ፍቃድ ከ12 ሳምንት ወደ 26 ሳምንት የሚያሳድግ ህግን አፀደቀ።

አዲሱ ህግ ከ10 በላይ ሰዎችን በስራቸው ቀጥረው በሚያስተዳድሩ ተቋማት በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል፡፡

የህንድ የሠራተኞች ሚኒስትር ባንዳሩ ዳታትሬያ ህጉ ለሴቶች ከሚገባቸው በታች ነው ብለዋል።

ኒው ደልሂ የወሊድ ፍቃድ ህጓን ስታሻሻል ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው።

በዚህም 50 እና 44 ሳምንታት የወሊድ ፍቃድን በቅደም ተከተል ከሚሰጡት ካናዳ እና ኖርዌይ ቀጥላ ሶስተኛዋ ረጅም ጊዜ
የወሊድ ፍቃድን በሙሉ ክፍያ የሰጠች ሀገራ ሆናለች።

ሆኖም ሴቶቹ 26 ሳምንቱን በሙሉ ክፍያ የወሊድ ፍቃድ የሚወጡት በመጀመሪያ ለሚወለዷቸው ሁለት ልጆች ብቻ ነው።

ከመጀመሪያ ሁለት ልጆቻቸው በተጨማሪ የሚወልዱ ከሆነ የወሊድ ፍቃዱ 12 ሳምንት ብቻ ይሆናልም ተብሏል፡፡

አንዳንዶች ህጉ ሴቶች ከእርግዝና በኋላ ስራቸውን እንዲለቁ እንዲሁም ልጃቸው ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ የሚያደርግ ነው ሲሉ፥ የህንድ የሴቶች እና ህጻናት ልማት ሚኒስተር ማኔካ ጋንዲ በበኩላቸው ህጉ ጤናማ እናት እና ልጅን የሚያስገኝ ነው በማለት አሞካሽተውታል፡፡ምንጭ፡- ቢቢሲ