አንዳንድ ሰው በተፈጥሮው ስልቹና ደካማ ሊሆን ቢችልም በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው ስንፍና ልክ እንደበሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ አረጋግጧል፡፡

በአካባቢያችን ስራ መስራት በማይወዱ ሰነፍ ሰዎች የተከበብን እንደሆነ የነሱ ስንፍና ሊጋባብን እንደሚችል ነው የፈረንሳይ የስነልቦና ተመራማሪዎች የጠቆሙት፡፡

የፈረንሳይ የጤና ምርምር ተቋም አዲ ባወጣው የምርምር ውጤት በአካባቢያችን ሰነፎች ካሉ አካባቢውን ለመምሰል በምናደርገው ተፈጥሮአዊ ባህሪ ምክንያት ስንፍናው ሊጋባብን እንደሚችል ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡

እንደጥናቱ ከስንፍናም ባሻገር እንደ ጥንቃቄ ማድረግና  ትግስት ማጣት ያሉ አጓጉል ባህሪዎችም ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፉ ተማራማሪዎቹ  አምልክተዋል፡፡

ጥናቱ በ56 ተሳታፊዎች ላይ የስንፍና ተጋላጭነት፣ ጥንቃቄና ትእግስት ማጣት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተሰርቶ ነው  እንደ ተላላፊ በሽታዎች  ከአንዱ ወደ ሌላው እንደሚሸጋገሩ ጥናቱን  ይፋ ማድረጉን ሜትሮ  ኒውስ ዘግቧል፡