እንደ ድርጅቱ ገለፃ ባለፈው ዓመት 180ሺህ ስደተኞች ሊቢያን አቋርጠው ጣሊያን ለመግባት የሞከሩ ሲሆን 26 ሺህዎቹ ህጻናት ናቸው፡፡ከእነዚህ ውስጥ ብዙዎቹ ህጻናት የተለያዩ ብዝበዛዎችን ጨምሮ ፆታዊ ትንኮሳ የደረሰባቸው ናቸው ብሏል፡፡ሊቢያ በተከማቹ ስድተኞች ዘንድ የውሃ እና የምግብ እጥረትም የተለመደ መሆኑን ዘገባው ያስረዳል፡፡በሊቢያ ከሚገኙ 34 ህገ ወጥ ስደተኞችን ማቆያ ማዕከላት መካከል የተወሰኑት ታጣቂዎች በተቆጣጠሩት አካባቢ የተመሰረቱ በመሆኑ ለስደተኞችን ሰብአዊ እረዳታ ለማቅረብ እንኳ አስቸጋሪ አድርጎታል ይላል የዩኒሴፍ ሪፖርት፡፡በሊቢያ የሚገኙ የስደተኛ አዘዋዋሪዎች ሴቶችን ለፆታ ግንኙነት ብቻ ወደ አውሮፓ በመላክ ኪሳቸውን እንደሚያደልቡበትም ዘገባው ያስረዳል፡፡የሊቢያ ጎረቤቶች እና ዓለም አቀፍ ተቋማት የስደተዖችን ግፍ ለማስቆም በጋራ ሊሰሩ እንደሚገባም ዩኒሴፍ ጥሪ አቅርቧል፡፡ምንጭ፡-ቢቢሲ