በየዓመቱ የሚከበረውን የፂም ቀን ምክንያት በማድረግ የፂም ትርኢት በሩሲያዋ ሞስኮ ከተማ ተካሂዷል።

በሩሲያ የፂም ቀን በየዓመቱ መጋቢት 28 ተከብሮ የሚውል ሲሆን፥ የፂም ትርኢቱም የዚሁ ቀን አካል መሆኑ ተነግሯል።

ቀኑን በማስመልከት የተዘጋጀው የፂም ትርኢት ሻምፒዮናም ባሳለፍነው ቅዳሜ መጠናቀቁ ታውቋል።

beard_moscow_2.jpg

በሩሲያ የፂም ቀን እንዲከበር ምክንያት የሆነው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1698 ትሳር ፒተር ሩሲያ የሚገኙ እና ፂማቸውን ያሳደጉ ወንዶች በሙሉ እንዲላጩ የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ማድረጉ ነው።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በሀገሪቱ ፂሜን አልላጭም የሚል አሊያም ፂሙን አሳድጎ የተገኘ ማንኛውም ሩሲያዊ የገንዘብ መቀጮ ሲቀጣ ቆይቷል።

beard_moscow_3.jpg

ሆኖም ግን ክልከላው እና ቅጣቱ በካትሪን ዘ ግሬት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር መጋቢት 28 1772 እንዲነሳ ተደርጓል።

ይህንን ተከትሎም በየዓመቱ መጋቢት 28 በመላው ሩሲያ የፂም ቀን ተደርጎ ነው የሚከበረው።

beard_moscow_4.jpg

ምንጭ፦ CGTN Africa