በቂ እንቅልፍ ይተኛሉ ? ጤናማ እና የተረጋጋ ሕይወት ለመምራት በቂ እንቅልፍ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን የህክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡

እንደባለሞያዎች ገለፃ ሳይበዛ ወይም ሳያንስ መተኛት ለአጠቃላይ ጤናችን አስፈላጊ ነው፡፡

ስለሚኖረው ጥቅም በአጭሩ …
1.በቂ እንቅልፍ መተኛት ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን
እንዲያዳብር ያስችላል (stronger immunity) ፡፡

2.የማስታወስ ችሎታ ይጨምራል (improve memory)

3.አዲስ የፈጠራ ሀሳብ ለማፍለቅ ይረዳል (creativity)
4.ጭንቅላት በትክክል፤ እንዲያስብ እና ተገቢ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ከፍተኛ አስተዋፅዎ አለው

5.አለቅጥ ውፍረት ወይም ቅጥነትን ለመቆጣጠር እና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች ያጎናፅፋል (weight control) ፡፡ ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ይተኙ…! ኢንሳይድሄልዝ