በአለም ላይ እጅግ ጤናማ ልብ ያላቸዉ ህዝቦች ተገኙ
በአለም ላይ እጅግ ጤናማ ልብ ያላቸዉ ጺማኔ የተሰኙ ህዝቦች በቦሊቪያ ጫካ እንደሚኖሩ አንድ ጥናት አመለከተ ፡፡
16,000 ጺማኔዎች በአማዞን ጫካ በማኒኪ ወንዝን አሳ በማደንና በእርሻ ስራ ይተዳደራሉ ፡፡
ሳይንቲስቶች 705 የሚሆኑ ጺማኔዎችን ልብ በመመርመር ከሌላው በተሻለ ጤነኛ ልብ እንዳላቸው ያረጋገጡት፡፡
• 17% አመጋገባቸው የዱር አሳማና ሮደንት
• 7% በንጹህ ውሀ ላይ የሚገኝ አሳ
• ቀሪዎቹ ከቤተሰብ እርሻ የሚገኝ ሩዝ፣ በቆሎ፣ ስኳር ድንችና ሙዝ መሳይ ፕላቲኒያ የተሰኘ ተክል
• እንዲሁም ፍራፍሬና ለውዝ ተመጋቢዎች ናቸው፡፡
ህዝቦቹ በአመጋገባቸዉም ሆነ በአኗ ኗራቻቸዉ ከየትኛዉም የአለም ህዝብ ይለያሉ፡ የእነዚህ ህዝቦች የአኗኗር ዘዴ የሰዉ ልጅ ከሺ አመታት በፊት ከደረሰበት ስልጣኔ ጋር ይመሳሰላል ተብሏል፡፡
ምንጭ፡- ቢቢሲ