ተመራማሪዎች በየዕለቱ ለአንድ ሰዓት የሚደረግ ሩጫ ተጨማሪ ሰባት ሰዓት በሕይወት የመኖር እድልን እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡

የአይኦዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ በየዕለቱ ለአንድ ሰዓት የሚደረግ ሩጫ ተጨማሪ ሰባት ሰዓታትን በሕይወት የመኖር እድልን እንደሚጨምር በጥናት ደርሼበታለሁ እያለ ነው፡፡

በአሜሪካ የካርዲዮሎጂ ኮሌጅ ጆርናል ላይ የሰፈረው የዩኒቨርሲቲው ጥናት፥ በየቀኑ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ መሮጥ በልብ እና በደም ቧንቧ ህመም ሊመጣ የሚችልን ሞት ይቀንሳል ይላል፡፡

ጥናቱ በዳላስ የኩፐር ኢንስቲትዩት የቀረበውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መረጃ ተንትኗል፡፡

ምርምሩ በአካላዊ እንቅስቃሴ ፕሮፌሰሩ ደክ ቹል ሊ መሪነት የተሰራ ሲሆን፥ በየዕቱ የሚደረግ ሩጫም የአንድን ሰው አስቀድሞ የመሞት እድሉን በ40 በመቶ ይቀንሳል የሚል ግኝትን ይፋ አድርጓል፡፡

በሳምንት ውስጥ ሁለት ሰዓታት የሩጫ ልምምድ ማድረግ ከእድሜ ውስጥ 3 ነጥብ 2 በመቶ በህይወት የመቆየት እድልን እንደሚያሳድግም ጠቁሟል፡፡

በጥቅል ምክረ ሀሳቡ የአሯሯጥ ፍጥነትን እና ርቀትን ሳይወስኑ በየቀኑ መሮጥ የመሞት እድልን እንደሚቀንስ ነው በጥናቱ ያመላከተው፡፡

ሆኖም በፈረንጆች 2014 የተደረገው ይህ ጥናት በየቀኑ የአሯሯጥ ስልቶችን በመከተል ያለርቀት ወሰን የሚሮጡት፥ ረዥም ርቀትን ከሚሮጡት በተሻለ በህይወት የመኖር እድላቸው እንደሚጨምር ጠቁሟል፡፡

ምንጭ፡-www.indy100.com