አይቮሪኮስታዊቷ የ10 ወር እድሜ ያላት ህጻን ስትወለድ አራት እግር እና ሁለት አከርካሪ ይዛ ነው የተወለደቺው፡፡

ጥገኛ መንትያው በአግባቡ ራሱን ችሎ ባለማደጉ ከሰውነቷ ጋር ተያይዞ እንደተፈጠረ የአዕምሮ ቀዶ ሃኪሙ ዶከተር አር ሩጅ ተናግረዋል፡፡

ህጻን ዶሚኒክ በጀርባዋ እና በአንገቷ ላይ ተጣብቀው በበቀሉት ትርፍ እግሮቿ ምክንያት ትክክለኛ የሰውነት ቅርፅ ይዛ እንዳልተወለደች ነው የተነገረው፡፡

በቺካጎ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተደረገላት ቀዶ ጥገና ትርፍ እግሮች እና አከርካሪዎች ተወግዶላታል፡፡

ይህ ዓይነቱ ህክምና በጣም ያልተለመደ እና ውስብስብ ነው ተብሏል፡፡

በልጆች የህክምና ማዕከል በተደገረገ ቀዶ ህክምና ስድስት ሰዓታትን የወሰዱ አምስት ቀዶ ጥገናዎች ተሰርቶላታል፡

ህፃኗ በሆስፒታሉ ለአምስት ቀናት ቆይታ አድርጋለች፡፡

ጥገኛ መንትያው ራሱን ልቻለ በመሆኑ ከዶሚኒኬ ልብ እና ሳንባ በጋራ ይጠቀም እንደነበርም ተጠቁሟል፡፡

fourleg.jpg

ዶሚኒክ አሁን ደስተኛ ስትሆን ሁለት የወተት ጥርሶችን ማብቀሏ የተነገረ ሲሆን፥ እጆቿን ማወዛወዝም ችላለች፡፡