በዱባይ የአለማችን ውዱ በርገር በ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መሸጡ ተሰምቷል።

በከተማዋ ጋለሪስ ላፋየት ሞል ለሽያጭ ከቀረበው በርገር የተገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ስራ እንደሚውል ነው የተነገረው።

አስማ አል ፋቲህ የተሰኙ ባለሃብት በርገሩን በጨረታ አሸንፈዋል፤ ጥያቄው ፋቲህ ይህን ውድ በርገር ጨክነው ይበሉት ይሆን የሚለው ነው።

በዱባይ ውድ ዋጋ ያወጣው በርገር ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ለበጎ አድራጎት ስራ በፒንክ ካራቫን ቡድን 7 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተሸጠውን በርገር በ3 ሺህ ዶላር በመብለጥ ነው ክብረወሰኑን የያዘው።

ፒንክ ካርቫን በጡት ካንሰር ዙሪያ የቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን የሚያከናውን ድርጅት ነው።

ድርጅቱ ለዚሁ ስራው እንዲያግዘው በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ጨረታ በማካሄድ በርገር በ5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መሸጡን ግሩብ ስትሪት በዘገባው አስታውሷል።

ምንጭ፦ www.msn.com/