የ21 ዓመቱ ህንዳዊ ወጣት ቁመቱ 23 ኢንች አሊያም 58 ሴንቲ ሜትር ብቻ ነው የሚረዝመው።

ማንፕሬት ሲንህ የሚባለው ይህ ወጣት የ6 ወር ህጻን ልጅ ያለውን ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን፥ ክብደቱም 7 ኪሎ ግራም ደገማ ነው።

የ21 ዓመቱ ህንዳዊ ወጣት የዓለማችን ትንንሽ ሰዎች ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ አንዱ መሆኑ እንዳልቀረም ነው በመነገር ላይ የሚገኘው።

21_yrs_old_5.jpg

ወጣቱ በምን አይነት የጤና እክል እንዲህ ሊሆን ቻለ የሚለው እስካሁን በህክምና ያልተደረሰበት ሲሆን፥ የማጠሩ ምክንያት ግን እስከሁን ለበርካቶች ያልተፈታ ሚስጥር ሆኖባቸዋል።

ማንፕሬት ሲንህ ሲወለድ ሙሉ ጤናማ እንደነበር የሚናገሩት ወላጆቹ፥ ልክ ስድስት ወር እንደሞላው ግን እድገቱ ሙሉ በሙሉ በቆሙን ነው የሚናገሩት።

21_yrs_old_4.jpg

ወደ ህክምና ባለሙያዎች ብንወስደውም ዶክተሮች ተገቢውን ምርመራ አላደረጉለትም የሚሉት ቤተሰቦቹ፤ ለህክምናው የሚሆን ገንዘብ እንደሌላቸውም ተናግረዋል።

የ21 ዓመቱ ማንፕሬት ሲንህ መናገርም ሆነ መራመድ የማይችል ሲሆን፥ እግሮቹን ማንቀሳቀስ ያቆመውም ገና የ3 ዓመት ልጅ እያለ ነበር።

21_yrs_old_5.jpg

ሆኖም ግን ለአካባቢው ነዋሪዎች ደስታን ይዞ እንደመጣ ነው ቤተሰቦቹ የሚናገሩት።

ምክንያቱ ደግሞ የአካባቢው ሰዎች ማንፕሬት ሲንህ የሂንዱ እምነት አምላክ በእሱ ተመስሎ ተወልዷል በሚል እያመለኩት መሆኑ ነው።

21_yrs_old_2.jpg

በርካቶችም ማንፕሬት ሲንህ ፊት ሲሰግዱ ታይተዋል።

ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk