የቦስተን ከተማ ነዋሪ የሆነቺው የነርሲንግ ተማሪዋ ኮርትነይ ከኖሊ የገንዘብ ቦርሳዋን የተሰረቀቺው በፈረንጆች 2009 ነበር፡፡

ይህን ተከትሎ በውስጡ የያዘውን ገንዘብ ጨምሮ ቦርሳዋን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ተጨንቃለች፤ ከተሸከርካሪዋ እንደተወሰደባት እንደምታስታውስ ተናግራለች ኮኖሊ፡፡

ቦርሳው ላለፉት ስምንት ዓመታት ከሰረቀው ግለሰብ ተይዞ በፖሊስ እጅ ነበር፡፡

በዚህ ሳምንትም ፖሊስ የኮኖሊን ቤተሰቦች አድራሻ አፈላልጎ የገንዘብ ቦርሳዋን ውስጡ ከነበረው ገንዘብ እና ከሙሉ እቃው ጋር አስረክቧታል፡፡

ኮኖሊም ከስምንት ዓመት በፊት የጠፋውን ንብረቴን አላገኘውም በሚል እየተጨነቅኩ ነበር ብላለች፡፡

በቦርሳው ውስጥ ያለው ገንዘብ፣ የማህበራዊ ደህንነት ቁጥር እና የመገበያያ ካርዱ ማንም ሳይጠቀምባቸው በነበሩበት የተመለሰላት ኮኖሊ እንደገረማት ነው የገለፀቺው፡፡

በቅርቡ መልካም ዜና ይደርስሻል የሚል መልዕክት በቦርሳው ላይ ማግኘቷን የተናገረቺው ተማሪዋ ሁኔታውን አስገራሚ የምስራች ብላዋለች፡፡

ምንጭ፡- www.upi.com