) የጀርመኗ መሪ አንጌላ ሜርክል ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሶቺ ተገናኝተው መክረዋል፡፡

መራሂተ መንግስቷ በሩሲያ ተግኝተው ከፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ከ2015 ወዲህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡

ሁለቱ መሪዎች በሶሪያ የእርስ በርስ ግጭትና እና በክሬሚያ ከዩክሬን መገንጠልና ወደ ሩሲያ መቀላቀልን ተከትሎ በመጣው ቀውስ ላይ ላይ እንደተወያዩ ተነግሯል፡፡

ሩሲያ ከዩክሬን ክሬሚያን ከገነጠለችበት 2014 ጀምሮ ከጀርመን ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሯል፡፡

ጀርመን የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ ለጣላቸው ማዕቀቦች ግፊት በማድረግ ሩሲያ ጀርመንን ተጠያቂ በማድረጓ ነው ግንኙነታቸው የሻከረው፡

ሜርክል በዩክሬን ያለው ብጥብጥ እንዲቆም ሞስኮ አፍቃሪ ሩሲያውያን ተገንጣዮች ላይ ጫና እንድታሳድርና የበኩሏን ጥረት እንድታደርግ ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

መራሂተ መንግስቷ በሶሪያ ሰላም እንዲሰፍን ሩሲያ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ለማድረግ ፑቲንን እንደሚጠይቋቸው ተጠቁሟል፡፡

ፑቲን ነገ ሜርክልን ከሸኙ በኋላ ከቱርኩ አቻቸው ሬሲብ ጣይብ ኤርዶኻን ጋር ይመክራሉ ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-ቢቢሲ