ፈረንሳያዊው አርቲስት የዶሮ እንቁለል ታቅፎ ሙቀት እንዲያገኙ በማደረግ ጫጩት ማስፈልፈሉ ተነግሯል።

አብረሃም ፖይንቸቫል የተባለው ይህ ግለሰብ ጫጩቶቹ እንዲፈለፈሉም ለሶስት ሳምንታት ያክል እንቆላሎቹን እንደታቀፋቸው ነው የተገለጸው።

አርቲስቱ አዲሱ ፐሮጀክቱን ከወር በፊትጀመረ ሲሆን፥ ይህ ፕሮጀክትም ልክ እንደ ዶሮ ለእንቁላል ከሰውነቱ በየሚነጭ ሙቀት በመስጠት ጫጩቶችን ማስፈልፈል ነው።

ለዚህም 10 እንቁላሎችን የተጠቀመ ሲሆን፥ እንቁሎቹንም በእንስሳት መጠበቂያ መስታወት ውስጥ በመሆን በፓሪስ ፓላየስ ዲ ቶክዮ ሙዚዬም ውስጥ ነው የታቀፈው።

እንቁላሉን በመታቀፍ ማስፈልፈል ፕሮጀክቱ ሰራም ከ21 እስከ 26 ቀናት ውስጥ እንደሚጠናቀቅ የገመተው አብረሃም ፖይንቸቫል፤ የመጀመሪያውን እንቁላል ባሳለፍነው ሳምንት ማስፈልፈል ማቻሉ ነው ተነገረው።

የሙዝዬሙ ቃል አቀባይ እንዳስታወቁት በአብረሃም ማካኝነት ተፈለፈሉት ጫጩቶች መልከም ጤንነት ላይ ይገኛሉ፤ በቅርቡም በዶሮ እርባታ ውስጥ ከሚገኙ ጫጩቶች ጋር እንዲቀላቀሉ ይደረጋሉ ብለዋል።

አብረሃም ፖይንቸቫል ጫጩቶቹ እንዲፈለፈሉ ለመድረግ እንቁላቹን የያዘውን ሳጥን ወንበወር ላይ በማድረግ እዛ ላይ ሙቀት ሚሰጠው ብርድልብ ለብሶ ነው የተቀመጠው።

doro.jpg

በዚህ ጊዜም በቀን ውስጥ ከ30 ደቂቃ ላነሰ ጊዜ ብቻ ከወንበሩ ላይ ሲነሳ የነበረ ሲሆን፥ ይህም ምግብ ለመብላት ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ www.reuters.com