Author: admin

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መራዘም – በህገ መንግስቱ ዓይን

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መራዘም ከፖለቲካና ከህግ አንጻር እንዴት ይታያል? የህግ ባለሙያዎች የአዋጁ መራዘም                   ከህገ መንግስት ውጪ ነው ሲሉ ይሞግታሉ፡፡ ፖለቲከኞች በበኩላቸው፤ህዝቡ ህገ መንግስታዊ መብቱን ተነፍጎ ወታደራዊ አገዛዝ በሚመስል ሁኔታ ውስጥ ወድቋል ይላሉ፡፡ የአዲስ አድማስ ጋዜጠኛ አለማየሁ አንበሴ፣ ፖለቲከኞችንና የህግ ባለሙያዎችን አነጋግሮ አስተያየታቸውን እንደሚከተለው አጠናቅሮታል፡፡ ‹‹አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት አስቸኳይ አዋጅ አይታወጅም›› አቶ ተማም አባቡልጉ (የህግ ባለሙያ) በአጠቃላይ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሲባል መጀመሪያ አስቸኳይ ሁኔታ መኖር አለበት፡፡ ይሄ ሲኖር ነው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚታወጀው። አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት አስቸኳይ አዋጅ አይታወጅም፡፡ በኢትዮጵያ ወቅታዊ እውነታ አስቸኳይ ሁኔታ በሌለበት ቦታ ሁሉ አዋጁ መታወጁ፣ አስቸኳይ አዋጅ አስፈላጊ እንዳልነበረ ያሳያል፡፡ አዋጁ የፖለቲካ ፍላጎትን ማሳኪያ ነው የሆነው፡፡...

Read More

ዓለማችን ላይ ስልሳ ሺህ የዛፍ ዝርያዎች አሉ፡- ጥናት

ዓለማችን ላይ ስልሳ ሺህ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ አንድ ጥናት አስታወቀ፡፡ በአለም ላይ በሚገኙ  እጽዋቶች ላይ የተደረገው አጠቃላይ ጥናት እንዳመለከተው በአለም ላይ ከስላሳ ሺ በላይ የዛፍ ፍሪያዎች  ይገኛሉ፡፡ ዓለም አቀፉ  የቦታኒካል አትክልት ጥበቃ ከአምስት መቶ አባል ድርጅቶቹ የሰበሰባቸው መረጃዎች ዋቢ በማድረግ ነው የዝርያ አይነቶቹን ይፋ ያደረገው፡፡ ድርጅቱ የሰባሰባቸው መረጃዎች በቁጥር አናሳ የሆኑትንና ሊጠፉ የተቃረቡትን የዛፍ ዝርያዎች በመለየትና ዝርያዎቹን ለመታደግ አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጿል፡፡ በዘርፉ በተደረገው ጥናት መሰረት ብራዚል የ8715 የተለያዩ የዛፍ ዘርያዎች መገኛ በመሆን ትልቁን ድርሻ ይዛለች፡፡ በንፍቀ ክበብ አከባቢ የሚገኙ አገራት ምንም አይነት የዛፍ ዝርያ የሌላቸው መሆኑንና በአርክቲክ አከባቢ የሚገኙ የሰሜን አሜሪካ አገሮች ደግሞ ከ1400 በታች...

Read More

ስንፍና እንደበሽታ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል፡- ጥናት

አንዳንድ ሰው በተፈጥሮው ስልቹና ደካማ ሊሆን ቢችልም በቅርቡ የተሰራ ጥናት እንደሚያመለክተው ስንፍና ልክ እንደበሽታ ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፍ አረጋግጧል፡፡ በአካባቢያችን ስራ መስራት በማይወዱ ሰነፍ ሰዎች የተከበብን እንደሆነ የነሱ ስንፍና ሊጋባብን እንደሚችል ነው የፈረንሳይ የስነልቦና ተመራማሪዎች የጠቆሙት፡፡ የፈረንሳይ የጤና ምርምር ተቋም አዲ ባወጣው የምርምር ውጤት በአካባቢያችን ሰነፎች ካሉ አካባቢውን ለመምሰል በምናደርገው ተፈጥሮአዊ ባህሪ ምክንያት ስንፍናው ሊጋባብን እንደሚችል ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡ እንደጥናቱ ከስንፍናም ባሻገር እንደ ጥንቃቄ ማድረግና  ትግስት ማጣት ያሉ አጓጉል ባህሪዎችም ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፉ ተማራማሪዎቹ  አምልክተዋል፡፡ ጥናቱ በ56 ተሳታፊዎች ላይ የስንፍና ተጋላጭነት፣ ጥንቃቄና ትእግስት ማጣት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተሰርቶ ነው  እንደ ተላላፊ በሽታዎች  ከአንዱ ወደ ሌላው እንደሚሸጋገሩ ጥናቱን  ይፋ ማድረጉን...

Read More

አሜሪካ በአይነቱ ግዙፍ የሆነ ቦንብ በአፍጋኒስታን በሚገኝ የአይ ኤስ ይዞታ ላይ ጣለች

አሜሪካ በአይነቱ ግዙፍ የሆነ ቦንብ በአፍጋኒስታን በሚገኝ የአይ ኤስ አይኤስ ይዞታ ላይ ጥላ 36 የቡድኑ አባላትን መግደሏን አስታወቀች፡፡ አሜሪካ በአፍጋኒስታን ናንጋርሃር በተሰኘው የአይ ኤስ ይዞታ ላይ ያፈነዳችው የቦንብ አይነት አሜሪካ “የቦምቦች እናት” ብላ የምትጠራውና በጦርነት አውድ ላይ  ከኒውከለር ቦንብ በመቀጠል ከጠቀመቻቸው የቦንብ አይነቶች ኃይለኛው ነው ተብሏል፡፡ቦንቡ 9ሺ 8ዐዐ  ኪሎ ግራም ይመዝናል፡፡ የአፍጋኒስታን የመከላከያ ሚንስቴርም  በጥቃቱ 36 የአይ ኤስ አባላት መገደላቸውን አረጋግጧል ፡፡ በሰላማዊ ዜች ላይ ግን ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱንም ሚኒስቴሩ አመልክቷል፡፡ የቀድሞው የአፍጋኒስታን ፕሬዝዳንት ሃሚድ ካርዛይ የአሜሪካን ጥቃት “ሰብዓዊነት የጎደለውና በአገራችን ላይ ጭካኔ የተሞላት  ድርጊት ፈፅማለች” ሲሉ   አውግዘዋል፡፡ ይሁንጂ የአፍጋኒስታን መንግስትና አሜሪካ የአሸባሪ ቡድኑን የጦር መሳሪያ ዶግ አመድ...

Read More

የፌስቡክ አድራሻችን መጠለፉን ለማወቅና ከጠላፊዎች ለመታደግ..

በአሁኑ ወቅት በዓለማችን ላይ በቢሊየን የሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች ካላቸው የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጽ ውስጥ ፌስቡክ ቀዳሚውን ድርሻ ይወስዳል። ታዲያ ይህ በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅነትን እያገኘ እና ለተለያዩ የማህበራዊ አገልግሎቶች እና የንግድ ስራዎች በስፋት ጥቅም ላይ እየዋለ ያለው ፌስቡክ የመረጃ ጠላፊዎች ሰለባ መሆኑ ለበርካቶች የራስ ምታት ሆኗል። የፌስቡክ አድራሻችን የመጠለፍ ጥቃት በመረጃ ጠላፊዎች ብቻ ሳይሆን ለኛ በጎ አመለካካት ቤላለቸው ሰዎች፣ በቀድሞ የፍቅር ጓደኞቻችን አሊያም በስራ ገበታችን ላይ ከኛ ጋር ተቀናቃኝ በሆኑ ሰዎች ሊደርስ ይችላል። ታዲያ የፌስቡክ አድራሻችን በቀላሉ በጠላፊዎች እጅ እንዳይገባ መጀመሪያ ላይ ማድረግ ያለብን ነገር ጠንካራ የሆነ የይለፍ ቃል ማዘጋጀት ነው። ለዚህም ይረዳን ዘንድ የይለፍ ቃላችን በሌሎች በቀላሉ ሊደረስበት በማይችሉ የፊደላት፣...

Read More