Author: admin

በሊቢያ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ 97 ስደተኞች ጠፍተዋል

ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሜዲትራኒያ ባህር ላይ ትጓዝ ነበረች ጀልባ ሰምጣ በትንሹ 97 ሰዎች መጥፋታቸው ተነገረ፡፡ የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂን ጠቀሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፥ ከሊቢያ ትሪፖሊ በ10 ኪሎሜተሮች ርቀት ላይ ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ 23 ስደተኞች ማዳን እንደተቻለ ታውቋል፡፡ ጀልባዋ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሰደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ እያመራች በለበት ወቅት በድንገት ባህር ውስጥ ሰምጣለች፡፡ ከአደጋው በኋላ ሳይሰምጡ እንዳለቀረ የተጠቀሱት 97 የሚሆኑ ስደተኞች የጠፉ ሲሆን ፥ ከነዚህም 15 የሚሆኑት ሴቶች እና 5 ህጻናት እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡ እስካሁን ያልተገኙት ሰዎች የመትረፍ እድላቸው የመነመነ መሆኑ እና ፍለጋውን ለማካሄድ የአየር ሁኔታው አስቸጋሪ እንዳደረገው የሊቢያ ጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ አዮብ ቃሲም ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ከሜዲትራኒያ ወደ አውሮፓ የሚሸጋገሩ የ ስደተኞች...

Read More

ፀሎተ ሃሙስ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶና ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በተለያዩ ስነስርዓቶች እየተከበረ ነው

የፀሎተ ሀሙስ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርሰቲያን እና በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን የኢየሱስ ክርስቶስ ትህትና እየታሰበ በተለያዩ ስነ ስርኣቶች እየተከበረ ነው። ክርስቶስ በዛሬዋ እለት የሃዋርያትን እግር ዝቅ ብሎ በማጠብ ትህትናን እና ታዛዥነት ማስተማሩን በማሰብ ነው በዓሉ የሚከበረው። በአሁኑ ሰዓትም በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ስነስርዓቱ እየተከናወነ ነው። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁእ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ የብፁዕ ጳጳሳቱን እግር፥ ጳጳሳቱ ቆሞሳቱ እና ካህናቱም የምዕመናኑን እግር በማጠብ የኢየሱስ ክረስቶስን አርአያነት ተከትለው ስርዓቱን የመፈጸሙ ሰነስርዓት እእየተካሄደ ይገኛል፡፡ በተመሳሳይ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያንም ብጽእ ካርዲናል ብርሃነየሱስ ሱራፌል ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካዊያን በተገኙበት፥ በልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በዓሉ እየተከበረ ይገኛል ። የህፅበተ እግር ስነ ስርዓቱም ከጥቂት ሰዓት...

Read More

እናት እና አገር- የሁሉም ዘመን ምርጫ

ዓለማችን በብዙ ምርጫዎች የተሞላች ነች ፡፡ ምርጫ የሌለበት የለም፡፡ የማይመረጥም የለም፡፡ ልብስ ይመረጣል፤ ጓደኛ ይመረጣል፤ አጭር፣ ረጅም፣ ቁመት ይመረጣል፤ ምግብ ይመረጣል፤ መጠጥ ይመረጣል፤ የቤት ምርጫ አለ፤ የሠፈር ምርጫ አለ፤ ወዘተ. ምርጫ የሌለባቸው የዓለማችን ቀናት አልነበሩም፤ ወደፊትም የሚኖሩ አይመስለኝም፡፡ ያኔ ያኔ የሥልጣኔው ሀ ሁ ሲጀመር አንዳንድ የፈጠራ ውጤቶች ብርቅዬና ድንቅዬ በመሆን አማራጭ የለሽ ሆነው አማራጭ እስከሚገኝላቸው ድረስ ማንኪያ ላይ እንዳለ «እንቁላል» በጥንቃቄ ይዘን፤ በስስት ዐይን እያየን የምንጠቀምባቸው ጊዜያት ነበሩ፡፡ ዛሬ ላይ ግን በምርጫ ማዕበል ተገፍተውና ተወስደው ከእኛ ርቀው ትዝታና ታሪክ ሆነዋል፡፡ በየትኛውም ዘመንና ጊዜ ግን ለእናት እና ለአገር ምርጫ የለም፡፡ እናት በማህፀኗ ተሸክማ የወለደች አጥብታ ያሳደገች የሕልውና መሰረት ናት፡፡ አገርም...

Read More

ጡረታ ከወጡ በኋላ 10 ሺህ ስእሎችን የሳሉ የ77 ዓመቷ አዛውንት

የ77 ዓመቷ ቻይናዊት አዛውንት ከስራቸው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ 10 ሺህ ስእሎች መሳላቸውን ይናገራሉ። ዋንግ ሞ የሚባሉት አዛውቷ እነዚህን ስእሎች በሰሜናዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ሺጂያዙዋንግ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ነው የሳሏቸው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ1996 ከስራቸው በጡረታ የተገለሉት ዋንግ፥ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የሳሏቸው ስእሎችም ከ10 ሺህ በላይ መድረሱን ይናገራሉ። ዋንግ ከስራቸው በጡረታ ከመገለላቸው አስቀድመው ለ30 ዓመታት ያክል በኢንደስትሪያል ዲዛይነርነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፥ ስራቸውም በቻይና እና ከቻይና ውጭ በርካታ ሽልማቶችን እንዳስገኘላቸው ገልፀዋል። በጊዜው ሲሰሩት የነበረው ዲዛይንም ከ200 ጊዜ በላይ የተለያዩ አውደ ርእዮች ላይ ቀርበውም ተጎብኝተዋል። ዋንግ ይናገራሉ፥ “እኔ እና ብሩሽ ከተገናኘት ረጅም ዘመናትን አስቆጥረናል፤ ስእል መሳል ደሜ ውስጥ ገብቷል”። በቻይና አማካኝ በጡረታ...

Read More

ሥጋትን ወደ መልካም አጋጣሚ /ብ. ነጋሽ

ሥጋትን ወደ መልካም አጋጣሚ /ብ. ነጋሽ ሥር የሰደደ ድህነት ዜጎች የመኖር ዋስትናው ባልተረጋገጠ አስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንዲኖሩ ከማድረግ ያለፈ መዘዝ አለው። ሥር የሰደደ ድህነት ገዢ በሆነባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎች በኑሯቸው ተስፋ ይቆርጣሉ። በመኖርና ባለመኖር መካከል ያለው ልዩነት ጠፍቷቸው ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ምንም ነገር ቢመጣ የሚያጡት ነገር እንደሌለ ስለሚሰማቸው ማንኛውንም ርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ አይሉም። ሥር የሰደደ ድህነት ያለበት ሁኔታ ለእርስ በርስ ግጭት፣ ለአክራሪነት እንቅቃሴና ለአሸባሪነት መፈጠርና መስፋፋት አመቺ ነው። አሜሪካ በኢራቅ ላይ ባወጀችው “የፀረ ሽብርተኝነት” የጦርነት ዘመቻዎች ላይ የተካፈለ የባህር ላይ መኮንን ጃክ ሃሪሰን የተባለ ለ21ኛው ክፍለ ዘመን ሽብርተኝነትና የኃይል እንቅስቃሴዎች መሠረታዊ መንስዔ ሥር የሰደደ ድህነት ነው የሚል አቋም በመያዝ...

Read More