Author: admin

ፅንስ ማስወረድ ጥርስ የመንቀል ያህል ቀሏል

ትምህርቷን ከዘጠነኛ ክፍል አቋርጣ የትውልድ መንደሯን ጥላ በስደት አዲስ አበባ እንድትመጣ ያስገደዳት ሳይታሰብ ድንገት የተፈጠረ እርግዝና ነው፡፡ ተወልዳ ባደገችበት ደብረብርሃን ከተማ፣ አብሯት ካደገው የልጅነት ጓደኛዋ ጋር ፍቅር የጀመሩት ገና በለጋ ዕድሜያቸው ነበር፡፡ ግንኙነታቸው ከጓደኝነትና ከከንፈር ወዳጅነት አልፎ አንሶላ ለመጋፈፍ ሲያበቃቸው ዕድሜያቸው ገና በአስራዎቹ መጨረሻ አካባቢ ላይ ነበር፡፡ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን መማር በጀመሩ ጥቂት ወራት ውስጥ በድብቅ የፈፀሙትን የፍቅር ግንኙነት ገሃድ የሚያወጣ ድንገተኛ ነገር ተከሰተ፡፡ የአስራ ስድስት ዓመቷ ሰናይት /ለዚህ ፅሁፍ ስሟ የተቀየረ/ በዕድሜ 3 ዓመት ከሚበልጣት የልጅነት ፍቅረኛዋ ማርገዟን አወቀች፡፡ ሁኔታው እጅግ አስደንጋጭ ነበር፡፡ ሰማይ ምድሩ ዞረባት። የትውልድ አካባቢዋ ከጋብቻ በፊት የሚከሰት እርግዝናን አጥብቆ የሚጠላና የሚጠየፍ መሆኑን ጠንቅቃ ስለምታውቅ፣...

Read More

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ‘ትሬይነር ፕላስ’ ሙሉ አባል ሆነች

ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ‘ትሬይነር ፕላስ’ ሙሉ አባል ሆነች። አቪዬሽኑ እንዳስታወቀው ሀገሪቱ የ’ትሬይነር ፕላስ’ አባል መሆን በዘርፉ ዓለም አቀፍ ስልጠናዎችን በመስጠት የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ያስገኝላታል ብሏል። የአቪዬሽን ቴክኖሎጂዎች እየተስፋፉና እያደጉ በመምጣት ላይ እንደሚገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ። በተጨማሪም የአየር ትራፊክ መጠን እየጨመረ በመሄዱ በዘርፉ የሚሰማሩ ባለሙያዎችን በብዛትና በጥራት ማሰልጠን ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነም ይነገራል። በኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን የስልጠና ማዕከል ዳይሬክተር አቶ ተሻለ በቀለ፥ ማዕከሉ ቀደም ሲል በተለያዩ የአቪዬሽን ሙያዎች ስልጠና ሲሰጥ መቆየቱን አስታውሰዋል። “አሁን የሙሉ አባልነት ማረጋገጫ የተገኘበት የዓለም አቀፉ ሲቪል አቪዬሽን ድርጅት ‘ትሬይነር ፕላስ’ ሃገሪቷ በዘርፉ ዓለም አቀፍ ስልጠናዎችን መስጠት ያስችላታል” ብለዋል። በዚህም የተሻለ የውጭ ምንዛሪ ማግኘት እንደሚቻል...

Read More

በ900 ሚሊየን ብር በባህር ዳር ለሚገነባው ሙዚየም የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ

በባህር ዳር ከተማ ከ900 ሚሊየን ብር በሚበልጥ ወጭ የሙዚየም ግንባታ ለማካሄድ ዛሬ የመሰረት ድንጋይ ተቀመጠ። በከተማዋ አየር ጤና አካባቢ ለሚገነባው ሙዚየም የመሰረት ድንጋይ ያስቀመጡት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ናቸው። የክልሉ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊ ዶክተር ሂሩት ካሳው በዚህ ወቅቱ እንደገለፁት የሚገነባው “የአማራ ህዝቦች ሙዚየም” የክልሉን ህዝብ ታሪክ፣ ባህል፣ ቅርስና መሰል ሃብቶችን አካቶ የሚይዝ ነው ። 15 ሺህ 650 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ለሚያርፈው የሙዚየሙ ግንባታ ዲዛይን ስራ የመጀመሪያው ምዕራፍ ተጠናቆ ማስተካከያዎች እየተደረጉለት መሆኑን ተናግረዋል። “ግንባታው በመጪው ዓመት መጀመሪያ ላይ ተጀምሮ በአምስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ” ብለዋል። የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እንደተናገሩት ሙዚየሙ ባህላዊ...

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ያስገነባቸውን የአውሮፕላን ቀለም መቀቢያና የጥገና ማእከሎች አስመረቀ

የአውሮፕላን ጥገና ማዕከሎቹ B747-800 አውሮላንን ጨምሮ የቦይንግ ትላልቅ አውሮፕላኖችን እንዲሁም በአንድ ጊዜ ከአንድ በላይ አውሮፕላኖችን የማስተናገድ አቅም አለው፡፡ ከጥገና ማእከሎቹ አንደኛው B777-200 አልያም B737 የቦንግ አወሮፕላኖችን ማስተናገድ ይችላል፡፡ ማእከሎቹ በሰፊ ቦታ ላይ ያረፉ ሲሆን በጣም ከፍታ ያለው ጣርያና የአውሮፕላን አጠቃላይ ጥገና ለመስጠት የሚያስችል አወቃቀር ያላቸው ናቸው፡፡ ከበስተጀርባ 15,000ሜ² ላይ ያረፈ የቢሮና የተለያዩ ሱቆች ቦታ መዘጋጀቱም ተገልጿል፡፡፡፡ ሪፖርተር፤ ብርሃን...

Read More

በበዓሉ ከትራንስፖርት አቅርቦቱ በላይ ፍላጎት አለ፡- ባለስልጣኑ

መጪውን የትንሳኤ በዓል ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ወደ ተለያዩ ክልሎች የሚደረገው ጉዞ የትራንስፖርት አቅርቦት ችግር እንደገጠመው የፌደራል ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡ ከዚህ ቀደም ከ5 እስከ 6 አውቶቢሶች የሚጠይቁ መስመሮች አሁን እስከ 30 መጠየቃቸውን ባለስልጣኑ ገልጿል፡፡ባለስልጣኑ ችግሩን ለመፍታት የትራንስፖርት ማህበራቱ ከመደበኛ ውጭ በፍቃደኝነት መስመር እንዲይዙ እና በጭማሪ ክፍያ እንዲሰሩ እየተሰራ መሆኑን ገልጿል፡፡ የባለስልጣኑ የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ይግዛው ዳኘው እንዳሉት ህብረተሰቡ በዓሉን ከቤተሰቦቹ ጋር እንዲውል ለማስቻል በኮሚቴ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት እየተደረገ ነው፡፡በበዓሉ የሚፈጠሩ ወከባዎችን እና ስርቆትን ለመቀነስም ከፖሊስ ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን  አቶ ይግዛው ገልጸዋል፡፡ በአዝመራው...

Read More