Author: admin

“ዓለም ‘ፌይር’ አይደለችም”

ስሙኝማ…በደስተኝነት ከዓለም 119ኛ ሆንን! ይቺን ይቺንማ ዝም ብለን አናልፍም፡ ልክ ነዋ… ከፈለገ ‘ኤይድ’ ምናምን የሚሉት ነገራቸው ይቀራል እንጂ እንዲህማ ‘ለፍቶ መና’ አያደርጉንም! እናማ…እኛ በጣም ‘ደስተኞች’ መሆናችንን ዓለም እንዲያውቅልን መከራችንን እያየን፣ እዛ ታች አውርደው የሚፈጠፍጡን ለምንድነው! የፈረንጅ ምቁነት የሚያበቃው መቼ ነው! ቂ…ቂ…ቂ… ቆይማ…የሌሊቱ ሰዓት አልበቃ እያለን ቀኑን ሙሉ የቡና ቤቶችን ውስጥና በረንዳ ሳይቀር እያጨናነቅን የምንውለው ‘ቢከፋን’ ነው! እግራችንን ሰቅለን ‘ሲፕ’ ከማድረግ የባሰ ምን ደስተኝነት አለ! እነሱ እንደየ አገራቸው ስርአት ዳንስ ቤቱና ቡና ቤቱ ሌሊት በስድስትም፣ በስምንትም ሰዓት ይዘጋልና እዚህ ‘የ24 ሰዓት አገልግሎት’ እየተሰጠ… አለ አይደል… እንዴት ነው በደስተኝነት ጭራው አካባቢ ናችሁ የሚሉን! እኔ የምለው… ይኸው አዳዲሱን የቴሌቪዥን ጣቢያ ሁሉ ዘፈን፣...

Read More

የአይዳ ሙሉነህ የፎቶግራፍ ስራዎች በፓሪስ ኤግዚቢሽን ሊቀርቡ ነው

በትውልደ ኢትዮጵያዊቷ አይዳ ሙሉነህ የተዘጋጁት የኢትዮጵያን ትናንት እና ነገን የሚያሳዩት አፍሪካዊ ስራዎች አፍሪከስ ካፒታልስ “Afriques Capitales,” በሚል ርዕስ በፈረንሳይ ፓሪስ በተዘጋጀ የፎቶግራፍ ኤግዚቢሽን ለእይታ ሊቀርቡ ነው፡፡ በአፍሪካ ስራዎች ላይ የሚያተኩሩ ፎቶግራፎች የሚቀርቡበት አውደ ርዕይ በፓሪስ አይረን ኤንድ ግላስ የባህል ማዕከል ከነገ ጀምሮ እስከ ግንቦት 20 ለእይታ ክፍት ይሆናል፡፡ በሴቶች፣ በአፍሪካዊ ማንነት፣ በባህልና በአገር ላይ የሚያተኩሩት የአይዳ ሙሉነህ የፎቶ ስራዎችም በፌስቲቫሉ ላይ ይቀርባሉ፡፡አይዳ የኢትዮጵያን ባህልና የግል ህይወቷን በጥበባዊ መንገድ የሚያመለክቱ ሰውነታቸውን በተለያዩ ቀለማት ያሸበረቁ ሴቶች፣ ባህላዊ አልባሳትና ቁሳቁሶች ላይ ባተኮሩት የፎቶ ስራዎቿ አለማቀፍ ተቀባይነትና እውቅና ያገኘች ባለሙያ ነች፡፡ አይዳ የልጅነት ጊዜዋን በየመን፣ እንግሊዝ፣ ቆጵሮስ፣ ካናዳና አሜሪካ ያሳለፈች ሲሆን የፎቶ ጋዜጠኝነትን...

Read More

በአዲስ አበባ የፍሳሽ መስመር ፍትሻና የማስከፈት አገልግሎት ለማግኘት 6 ወራትን መጠበቅ ግዴታ ሆኗል

በአዲስ አበባ ከተማ የፍሳሽ መስመር ፍትሻ እና የማስከፈት አገልግሎት ለማግኘት ሰድስት ወራትን መጠበቅ ግዴታ ሆኗል። ጄት ማስተር በተሽከርካሪ በመታገዝ እስከ 35 ሜትር የተዘጋ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመርን ፈትሾ መክፈት የሚያስችል መሳሪያ ነው። አዲስ አበባ ከተማ ላለፉት በርካታ አመታት ሁለት የጄት ማስተር የተባለ መፈተሻ ብቻ ይዛ የከተማውን ህዝብ ስታገለግል ቆይታለች። በአሁኑ ወቅትም አንዱ ተበላሽቶ አንዱ ብቻ ነው አገልግሎት እየሰጠ ያለው። በዚህ ምክንያት የፍሳሻ ማስወገድ እና ፍትሻ የሚፈለጉ ተገልጋዮች ብዙ ወረፋ ለመጠበቅ መገደዳቸውን የሚናገሩ ሲሆን፥ ችግሩ በአፋጣኝ እንዲፈታላቸውም ይጠይቃሉ። በአዲስ አበባ ውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን የፍሳሽ ዘርፍ ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ባህረ በላይ፥ በከተማው አገልግሎት የሚሰጥ ጄት ማስተር ተብሎ የሚጠራው የፍሳሽ መስመር...

Read More

ያለእድሜዋ ያረጀችው ደቡብ አፍሪካዊት ከዚህ ዓለም በሞት ተለየች

በበርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ልብ ውስጥ ያለ እድሜዋ እርጅናን በመጋፈጥ የምትታወቀው ኦንትላሜስ ፋላስ በ18 ዓመቷ ከዚህ ኣለም በሞት ተለይታለች።ሃኪሞች ኦንትላሜስ ፋላስ ያለእድሜዋ ያጋጠማት እርጅና ከ14 ዓመት በላይ በሕይወት እንዳትኖር ያደርጋታል ብለው ነበር፡፡የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ለኦንትላስ ቤተሰቦች የሞት ሀዘን በመላክ የቀደማቸው የለም፡፡ሟቿ በጓደኞቿ እና በቤተሰቦቿ ዘንድ “ቀዳማዊት እመቤት” የሚል ስያሜም ተሰጥቷት ነበር፡፡ የደቡብ አፍሪካው ኢንካ መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱ የመልካምነት ሻምፒዮን ብሏታል፡፡ቤተሰቦቿም ሃላሰን ለማዳን ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሁሉ አመስግነው “በጣም ትናፍቂናለሽ፤ ነፍስሽን በገነት ያኑራት” ብለዋል፡፡ ኦንትላሜስ ባለፈው ወር 18ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ጃኮብ ዙማ በተገኙበት ያከበረች ሲሆን በዘር መዛባት ምክንያት ለሚከሰት ያለ እድሜ የማርጀት ክስተት የተጋለጠች ብቸኛዋ ጥቁር ሴት ነች፡፡የዘረመል...

Read More

ስሜታዊነትን የመቆጣጠር አቅምን የሚያሳድጉ መንገዶች

ስሜታዊነትን መቆጣጠር ለግለሰቦች የተሰጠ መብት እና ግዴታ ነው ይላል አዲስ የተጠና ስነልቦናዊ ጥናት፡፡ በየዕለቱ የሚያበሳጩ ወይም ስሜታዊ የሚደርጉ ነገሮች ሲያጋጥሙ በደመነፍሳዊነት ስሜታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ለስነ ልቦናዊ ጉዳት የተጋለጡ ናቸው፡፡ ስሜታዊነትን ለመቆጣጠር በሚያግዙ መንገዶች ዙሪያ በርካታ ጥናቶች ተሰርተዋል፡፡ ሰዎች የራሳቸውን ድክመት እና ጥንካሬ ሌላ ሰው እስካልነገራቸው ድረስ በራሳቸው መንገድ ያለመለየት ባህሪ ኣላቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ስሜታዊ የሚያደርጉ ነገሮችን ራስን ተቆጣጥሮ ችሎ ለማለፍ ይቸገራሉ፡፡ የአውበርን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪው ዳንኤል ሊ እንደሚለው ራስን መጠየቅ ስሜታዊነትን የመቆጣጠር አቅምን ያዳብራል፡፡ ይህ ራስን የመመልከቻ ጥያቄ ሁልጊዜ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ስሜታዊ ድርጊቶች ለመራቅ እና የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር ይረዳል ነው የሚለው ተመራማሪው፡፡ በተፈጠረው ነገር ስሜታዊ ሆኛለሁ፣ በጣም ተበሳጭቻለሁ ወይስ...

Read More