Author: admin

በሩሲያ ሞስኮ የፂም ትርኢት ተካሂዷል

በየዓመቱ የሚከበረውን የፂም ቀን ምክንያት በማድረግ የፂም ትርኢት በሩሲያዋ ሞስኮ ከተማ ተካሂዷል። በሩሲያ የፂም ቀን በየዓመቱ መጋቢት 28 ተከብሮ የሚውል ሲሆን፥ የፂም ትርኢቱም የዚሁ ቀን አካል መሆኑ ተነግሯል። ቀኑን በማስመልከት የተዘጋጀው የፂም ትርኢት ሻምፒዮናም ባሳለፍነው ቅዳሜ መጠናቀቁ ታውቋል። በሩሲያ የፂም ቀን እንዲከበር ምክንያት የሆነው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1698 ትሳር ፒተር ሩሲያ የሚገኙ እና ፂማቸውን ያሳደጉ ወንዶች በሙሉ እንዲላጩ የሚያስገድድ ህግ ተግባራዊ ማድረጉ ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በሀገሪቱ ፂሜን አልላጭም የሚል አሊያም ፂሙን አሳድጎ የተገኘ ማንኛውም ሩሲያዊ የገንዘብ መቀጮ ሲቀጣ ቆይቷል። ሆኖም ግን ክልከላው እና ቅጣቱ በካትሪን ዘ ግሬት እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር መጋቢት 28 1772 እንዲነሳ ተደርጓል። ይህንን ተከትሎም በየዓመቱ...

Read More

ስንፍና እንደበሽታ ከሰው ወደ ሰው ይተላለፋል፡- ጥናት

በአካባቢያችን ስራ መስራት በማይወዱ ሰነፍ ሰዎች የተከበብን እንደሆነ የነሱ ስንፍና ሊጋባብን እንደሚችል ነው የፈረንሳይ የስነልቦና ተመራማሪዎች የጠቆሙት፡፡ የፈረንሳይ የጤና ምርምር ተቋም አዲ ባወጣው የምርምር ውጤት በአካባቢያችን ሰነፎች ካሉ አካባቢውን ለመምሰል በምናደርገው ተፈጥሮአዊ ባህሪ ምክንያት ስንፍናው ሊጋባብን እንደሚችል ተመራማሪዎች አስታውቀዋል፡፡ እንደጥናቱ ከስንፍናም ባሻገር እንደ ጥንቃቄ ማድረግና  ትግስት ማጣት ያሉ አጓጉል ባህሪዎችም ከሰው ወደ ሰው እንደሚተላለፉ ተማራማሪዎቹ  አምልክተዋል፡፡ ጥናቱ በ56 ተሳታፊዎች ላይ የስንፍና ተጋላጭነት፣ ጥንቃቄና ትእግስት ማጣት ላይ ትኩረቱን አድርጎ ተሰርቶ ነው  እንደ ተላላፊ በሽታዎች  ከአንዱ ወደ ሌላው እንደሚሸጋገሩ ጥናቱን  ይፋ ማድረጉን ሜትሮ  ኒውስ...

Read More

አዳምና ሔዋን – ካልተከሉት ዛፍ የቀመሱት ፍሬ

የአዳምና የሔዋንን ዝነኛ ታሪክ፣ እንደገና አነበብኩት። እንዲህ አጭር ነው እንዴ? አንድ ገፅ፣… ቢበዛ ደግሞ ሁለት ገፅ ቢሆን ነው። ግን፣ እንደ እጥረቱ ሳይሆን፣ እንደ ዝናው፣ ከባድ መልዕክትን ያቀፈ፣ ሳያንዛዛ ትልቅ ቁምነገርን የሚያስጨብጥ ልዩ ትረካ ቢሆንስ? ለዚያውም፣ አይን ከፋች ቁምነገር! ትረካው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ፣ የአዳምና የሔዋን ነገረ ስራ፣ ግር ያሰኛል። “ነፍስ ያወቁ” ሕፃናት ይመስላሉ። ማሰብ የለ፤ መስራት የለ፣ ፍቅር የለ…። መብላትና መጠጣት ብቻ! ከዚያም በየፊናቸው መተኛት! እርቃናቸውን ነው የሚውሉት። ግን ምንም! እርስ በርስ በአድናቆት የመተያየትና በፍቅር የመሳሳብ ቅንጣት ምልክት የለም። እንኳን በእውናቸው በሕልማቸውም አይመጣላቸውም። በማግስቱ ከእንቅልፍ ሲነቁም፣ ያው እንደ ትናንቱ መብላት ነው። ለምለሙ የእርሻ ማሳ ውስጥ፣ ሁሉም ነገር ሙሉ፣ ሁሉም ነገር...

Read More

ማስተዋልና ጥሞና!

‹‹መፅሐፍ እያነበብክ ጊዜህን ማሳለፍ ትመርጣለህ ወይንስ ከሰዎች ጋር መዝናናት?›› የሚል ጥያቄ እንደ ሰውየው ምርጫ የሚወሰን ከመሰለቻችሁ ተሳስታችኋል፡፡ “መፅሐፍን እመርጣለሁ›› ብሎ በፍጥነት የሚመልሰው አስመሳይ ነው፡፡ አላዋቂ አስመሳይ። ተንኮል አስቦ ላይሆን ይችላል ወገኛ መልስ የሚሰጠው፡፡ ሁሉ ሰው ይኼን መሰል ጥያቄ ሲቀርብለት፣ በማህበረሰቡ “ማንበብ” ተቀባይነት አለው ብሎ ስለሚያስብ፣ መፅሐፍ አንባቢነትን ይመርጣል፡፡ ሁለቴ ሳያስብ፡፡ “ከሰዎች ጋር በመሆን ጊዜዬን ማሳለፍ እመርጣለሁ” የሚለውም የዘፈቀደ ምላሽ፣ ሁለቴ ሳያስቡ የሚሰጥ ነው፡፡ በመሰረቱ ጥያቄው ራሱ አሳሳች ነው፡፡ በሁለቱም አንፃር ቢመለስ ያልተሟላ ወይንም ለጥያቄው መልስ የሚሰጠውን ሰው የሚያስወነጅል የጥያቄ አይነት አለና፡፡ “ዘንድሮስ መዋሸት አቁመሀል?” ለሚል ጥያቄ የ“አዎ” ወይንም “አይደለም” መልስ ጠያቂው ለመስጠት ከፈቀደ፣ መላሹ ራሱን ከመወንጀል አይተርፍም፡፡ ዘንድሮስ መዋሸት...

Read More

ስደተኞችን ይዛ በሰመጠችው ጀልባ ውስጥ የአራት ቀን ህጻን በሕይወት ተገኘች

በመካከለኛው የሜዲትራኒን ባህር በርካታ ስደተኞችን ይዛ የሰመጠችውን ጀልባ ሲፈልጉ የነበሩ የነፍስ አድን ሰራተኞች የአራት ቀን እድሜ ያላት ህጻን ጨምሮ 480 ስደተኞችን መታደጋቸውን ገልጸዋል፡፡ ባለፈው ቅዳሜ ሁለት ጀልባዎች ከ200 የማያንሱ ስደተኞችን ይዘው ከሊቢያ የባህር ዳርቻ 22 ማይል ርቀት በሜዲትራኒያን ባህር የሰመጡ ሲሆን፥ ህጻኗም በአንደኛው ጀልባ ውስጥ ነበረች ተብሏል፡፡ ጀልባዎቹ ከመካከለኛው እና ሰሜን አፍሪካ፣ ከስሪ ላንካ እና ከየመን የተነሱ ስደተኞችን ይዘው ነው የሰመጡት፡፡ ከነፍስ አድን ሰራተኞች ውስጥ አንዱ የሆነው ዳኒኤል ካልቬሎ “ባለፈው ሳምንት በርካታ ሰዎችን በባህሩ ውስጥ ሞተው አስከሬናቸውን አውጥቼ ነበር፡፡ ዛሬ ግን አዲስ ህይወትን ታድጊያለሁ” ሲል ተናግሯል፡፡ የህጻኗ እናት የ29 ዓመቷ ናይጀሪዊት እና አባቷ የ34 ዓመቱ ጋናዊ በሕይወት አድን ሰራተኞች...

Read More