Author: admin

«ዓለምን ለማዳን የሚያስችል ኃይል የሚገኘው ከፍቅር ነው» – አልበርት አንስታይን

ፍቅር በዓለም ላይ ካሉ ህልዮቶች ሁሉ የላቀው ነው። ሰውን ጨምሮ ማናቸውም ፍጥረታት ከፍቅር ጋር አንዳች ምስጢራዊ ውህደት ያላቸው ይመስላል። ይህም ህይወት ራሷ ያለ ፍቅር የማትታሰብ በመሆኗ ከፍቅር ጋር የመሰረተችው ወዳጅነት ነው። ከአፏ የደረሰን ምግብ ለልጇ የምታጎርስ ወፍን የተመለከተ ፍቅር ምን ያህል ለህይወት አስፈላጊ ኃይል መሆኑን ይታዘባል። የምድራችን ታላቁ ፍጥረት የሆነውን ሰውንም ስናስብ መላ ህይወቱ ከፍቅር ጋር የተሳሰረ መሆኑን እንረዳለን። ባልና ሚስትን፣ ወላጆችንና ልጆችን እህትና ወንድሞችን አስተሳስሮ የአገር መሠረት የሆነውን ቤተሰብን የፈጠረው ፍቅር ነው። እግሬን ለጠጠር ግንባሬን ለጦር ብሎ ሰው ክቡር ህይወቱን የሚሰዋው እትብቱ ለተቀበረባት፣ ከአለመኖር ወደ መኖር ሲመጣ እጇን ዘርግታ ለተቀበለችው ለተወለደባት ለተገኘባት ምድር፣ ለእናት አገሩ ባለው ፍቅር ነው።...

Read More

ለፍቅር የተከፈለ ድንቅ መስዋዕትነት

ፍቅር ባላባቱን ሎሌ የሚያደርግ ታላቅ ሀይል እንዳለው ይነገርለታል᎓᎓ የተለያዩ ፀሀፍቶች ብዙ ብለውለታል᎓᎓ ይህ ታላቅ ሀይል ያለውን የፍቅር ስሜት ድምፃውያኑ ሞዝቀውለታል᎓᎓ ይሁን እንጂ ምንም ቢነገርለትም ከስሜቱ ጥልቀት የተነሳ ተነግሮለት የማያልቅ፣ በየጊዜው አዳዲስ ነገሮችን የሚያስተናግድ እንደሆነ ቀጥሏል። ለአብነትም ፍቅርን በአየር የሚመስሉ ዘፈኖች በብዛት እንሰማለን᎓᎓ «አንተን ማጣት ማለት ልክ አየር በሌለበት ዓለም ውስጥ እንደመኖር ነው»፣ «ስተነፍስ ብቻ ነው የምናፍቅሽ»፣ «የምታስፈልጊኝ ልቤ ሲመታ ብቻ ነው» ተብሎለታል። አስቡት እስኪ ሁሉም የማይቻል ነገር ነው᎓᎓ ነገር ግን በፍቅር ሁሉም ይቻላል᎓᎓ ደግሞም ለአፍቃሪ ሁሉም ነገር ትክክል ነው᎓᎓ እንዴት ከግማሽ አካላችን ውጪ መኖር ይቻለናል? የዘፈኖቹ ሀሳብ እንደምንተነፍሰው አየር ሁሉ ካፈቀሩት ለሰከንድ እንኳን ተለይቶ መኖር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ...

Read More

19 ልጆች የወለደችው እናት 20ኛውን ወልዳ ለመሳም እየተጠባበቀች ነው

በብሪታንያ 19 ልጆችን የወለዱት እናት 20ኛ ልጃቸውን ወልደው ለመሳም እየተጠባበቁ ነው። የ42 ዓመቷ እናት ሱ ራድፎርድ እና የ46 ዓመቱ ኖኤል በመጪው መስከረም ወር 20ኛ ልጃቸውን ወልደው እንደሚስሙ ለፌስቡክ ተከታዮቻቸው ይፋ አድርገዋል። የእነ ራድፎርድ ቤተሰብ 19ኛ ሴት ልጃቸው ቤተሰቡን የተቀላቀለችው ባለፈው ሀምሌ ወር ነበር። የሪያሊቲ ቲቪ ሾው ኮከቦቹ ሱ እና ባለቤቷ ሃሌ አላፊያ ቤው የተባለችውን ሴት ልጃቸውን በፈረንጆች 2015 ሰኔ ወር ላይ ከወለዱ በኋላ ልጅ የመጨመር ፍላጎት እንደሌላቸው ገልፀው ነበር። ሆኖም በመጪው መስከረም የምትወለደው ወይም የሚወለደው ህጻን 10 ወንድሞች እና 9 እህቶች ይኖረዋል ወይም ይኖራታል። የዓለማችን ብዙ አባላት ያሉት ቤተሰብ በህንድ ባክትዋንግ ሲሆን አባወራ ዚኦና ቻና ከ39 ሚስቶች 94 ልጆች...

Read More

ሰዎች ሳያስቡት በአቅራቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እንደሚላበሱ አንድ ጥናት አመለከተ

የፈረንሳይ ዓለም አቀፋዊ የጤና እና የህክምና ምርምር ኢንስቶትዩት ተመራማሪዎች የሰዎች የባህሪ ወይም የአዕምሯዊ ተግባራት ለውጥ እንዴት እንደሚከሰት አረጋግጠናል ብለዋል፡፡ በጥናቱ መሰረት ሰዎች በማህበራዊ ተራክቦ ሳቢያ የአመለካከት መደበላለቅ እና የባህሪ ለውጥ ያጋጥማቸዋል፡፡ ይህም ማለት ሰዎች በአቅራቢያቸው ካሉ ሌሎች ሰዎች የሚያደርጉትን የመላበስ ወይም የመቅዳት ዝንባሌ በአዕምሯቸው ላይ ያርፋል ማለት ነው፡፡ የሰው ልጅ ሰነፍ ወይም ብርቱ ለመሆኑ ተጠያቂ ሊያደርገው የሚችለው በቅድሚያ በአቅራቢያው ያለን ሌላ ሰው ነው፡፡ እንደ ጠንቃቃነት፣ ስንፍና እና ትዕግስት ማጣት ያሉ ባህሪያትን ሰዎች ሳያስቡት በአቅራቢቸው ካሉ ሰዎች የመውረስ አጋጣሚዎች መኖራቸውን ጥናቱ ይፋ አድርጓል፡፡ እነዚህ ባህርያት እንዴት ወደ ሰዎች እንደሚጋቡ ለማጥናት የሞከሩት ተመራማሪዎችም ምክንያቱ የሰዎች ባህሪ በሌሎች ላይ ተፅዕኖ የሚሳርፍ በመሆኑ...

Read More

ሳምሰንግ ጋላክሲ ኤስ8 ስልኩን በይፋ አስተዋወቀ

የደቡብ ኮሪያው ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ሳምሰንግ አዲሱን ጋላክሲ ኤስ8 ስማርት ስልኩን ትናንት በይፋ አስተዋውቋል። ጋላክሲ ኤስ8 ኩባንያው በኖት 7 ስልኩ ያጋጠመውን የ3 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ለማካካስ እንደሚረዳው ነው የተነገረው። የአይፎን ተፎካካሪ ሳምሰንግ አዲስ ስልክ በሁለት አይነት የስክሪን ስፋቶች ነው የመጣው፤ ጋላክሲ ኤስ8 በ5 ነጥብ 8 ኢንች እንዲሁም ጋላክሲ ኤስ8 ፕላስ በ6 ነጥብ 2 ኢንች። ኩባንያው ጋላክሲ ኤስ8 ስማርት ስልኩ ከዚህ ቀደም በጋላክሲ ኤስ7 ስልኮቹ ሲያጋጥም የነበረው አይነት የመፈንዳት ችግር እንደማያጋጥመው ገልጿል። የመለቀቂያ ጊዜ ሳምሰንግ አዲሱን ጋላክሲ ኤስ8 ስልክ ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 21 2017 ጀምሮ ለአሜሪካ ገበያ እንደሚያቀርብ አስታውቋል። ከሚያዚያ 28 ጀምሮ ደግሞ ብሪታንያን ጨምሮ ወደ መላው አለም ስማርት ስልኩ ለገበያ...

Read More