Author: admin

4 ሚሊየን ዶላር የሚያወጣ የወርቅ ሳንቲም ከጀርመን ሙዚየም ተሰረቀ

በጀርመን መዲና በርሊን የሚገኘው ቦዴ ሙዚዬም 4 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር የሚያወጣ የወርቅ ሳንቲም መዘረፉ ተሰምቷል። የበርሊን ፖሊስ እንዳለው ዘራፊዎች ወደ ሙዚየሙ ዘልቀው በመግባት 100 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን የወርቅ ሳንቲም ሰርቀው ተሰውረዋል። “big maple leaf” በመባል የሚታወቀው ግዙፉ ሳንቲም 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ዋጋ እንዳለው ቢታተምበትም 100 ኪሎ ግራም ንፁህ 24 ካራት ወርቅ በመሆኑ በአሜሪካ ገበያ 4 ሚሊየን ዶላር ያወጣል ተብሏል። ዘራፊዎቹ በምሽት በሙዚዬሙ መስኮት በኩል በመግባት ሳንቲሙ የተቀመጠበትን ሳጥን በመሰባበር ውዱን ሳንቲም ዘርፈዋል፤ ፖሊስ ከመድረሱ በፊትም ከአካባቢው ተሰውረዋል ነው ያሉት የሙዚየሙ ቃል አቀባይ ስቴፈን ፒተርሰን። ሶስት ሴንቲሜትር ውፍረት እና 53 ሴንቲሜትር ዲያሜትር ያለው የወርቅ ሳንቲሙ በፊት ገፁ የንግስት ኤልሳቤጥ...

Read More

33 ጊዜ የመንጃ ፈቃድ ፈተናዎችን የወሰደው ጎልማሳ በመጨረሻው ተሳክቶለታል

ስኬታማ ከናንተ ብትርቅም ተስፋ አትቁረጡ፤ ሞክሩ፣ ሞክሩ፣ ሞክሩ… ይላል ለ25 አመታት የመንጃ ፈቃድ ፈተናዎችን ማለፍ ያልቻለው ጎልማሳ። ክርስቲያን ዊትሊይማሶን ይሰኛል፤ ባለፉት 25 አመታት 33 የመንጃ ፈቃድ ፈተናዎችን ወስዷል። 14 የተለያዩ አሰልጣኞችንም ቀያይሮ ፈተናውን ለማለፍ ሞክሯል። ክርስቲያን ለሩብ ክፍለ ዘመን 85 የትምህርት ክፍለ ጊዜዎችን ስነ አነዳድ እና የትራፊክ ህጎች የተማረና 10 ሺህ ፓውንድ ያወጣ ቢሆንም ያለመው የመንጃ ፈቃድ እጁ ሊገባ አልቻለም። በመጨረሻው 33ኛው ሙከራ ግን ክርስቲያን የ25 አመታት ድካሙ ሰምሮለት የመንጃ ፈቃድ ፈተናውን ማለፍ ችሏል። የ42 አመቱ ጎልማሳ በእንግሊዝ ደቡብ ዮልክሻየር ነዋሪ ሲሆን፥ ለመጀመሪያ ጊዜ የመንጃ ፈቃድ ፈተና የወሰደው እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ1992 ነበር። ይህን ፈተናም ማለፍ ያልቻለው ክርስቲያን በተከታታይ...

Read More

ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ አህመድ ካትራዳ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

ደቡብ አፍሪካዊው የፀረ አፓርታይድ ታጋይ አህመድ ካትራዳ ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰማ። በፀረ አፓርታይድ ትግሉ ወቅት ከፍተኛ ተሳትፎ ያደረጉት አዛውንቱ ካትራዳ፥ በዛሬው እለት በጆሃንስበርግ ህልፈታቸው ተሰምቷል። በርካታ ደቡብ አፍሪካውያንም ትልቁን የነጻነት መሪ አጣን ሲሉ ሃዘናቸውን ገልጸዋል። የነጻነት ታጋዩ አህመድ ካትራዳ፥ የቀድሞው የነጻነት ታጋይ እና የደቡብ አፍሪካ ፕሬዚዳንት ኔልሰን ማንዴላ የቅርብ ወዳጅ እንደነበሩ ይነገራል። በ19 50ዎቹ መጀመሪያ ከነጻነት ታጋዩ ኔልሰን ማንዴላ ጋር በመገናኘት ፀረ አፓርታይድ እንቅስቃሴን አሃዱ ብለው ጀምረውታል። አህመድ ካትራዳ የነጮችን ጭቆና በመቃወማቸው ሳቢያም በሮቢን ደሴት እና ፖልስሞር 26 አመታትን በእስር አሳልፈዋል። ለደቡብ አፍሪካ ነጻነት የታገሉት ካትራዳ፥ ባደረጉት የፀረ አፓርታይድ ዘመቻ በፈረንጆቹ 19 52 ከኔልሰን ማንዴላ ጋር የ9 ወራት የእስር...

Read More

በቂ እንቅልፍ ይተኛሉ ?

በቂ እንቅልፍ ይተኛሉ ? ጤናማ እና የተረጋጋ ሕይወት ለመምራት በቂ እንቅልፍ ማግኘት አስፈላጊ መሆኑን የህክምና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡ እንደባለሞያዎች ገለፃ ሳይበዛ ወይም ሳያንስ መተኛት ለአጠቃላይ ጤናችን አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሚኖረው ጥቅም በአጭሩ … 1.በቂ እንቅልፍ መተኛት ሰውነታችን በሽታ የመከላከል አቅሙን እንዲያዳብር ያስችላል (stronger immunity) ፡፡ 2.የማስታወስ ችሎታ ይጨምራል (improve memory) 3.አዲስ የፈጠራ ሀሳብ ለማፍለቅ ይረዳል (creativity) 4.ጭንቅላት በትክክል፤ እንዲያስብ እና ተገቢ ውሳኔ እንዲያሳልፍ ከፍተኛ አስተዋፅዎ አለው 5.አለቅጥ ውፍረት ወይም ቅጥነትን ለመቆጣጠር እና ሌሎችም በርካታ ጥቅሞች ያጎናፅፋል (weight control) ፡፡ ስለዚህ በቂ እንቅልፍ ይተኙ…!...

Read More

ዜድ ቲ ኢ በዓለም የመጀመሪያውን የ5ኛ ትውልድ ስማርት ስልክን አስተዋወቀ

ዜድ ቲ ኢ በዓለም የመጀመሪያውን የ5ኛ ትውልድ የሆነ በሰከንድ አንድ ጊጋ ባይት የማውረድ አቅም ያለው ስማርት ስልክ አስተዋወቀ፡፡ የፈረንጆች 2020 ሲደርስ የዓለም ትውልድ መረጃዎቹን በአምስተኛ ትውልድ በደረሰ የኔትወርክ አቅም አሁን ያለውን ገመድ አልባ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገድ ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ እንደ ኖኪያ፣ ሳምሰንግ፣ አልካቴል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች በእርግጥ በከፊልም ቢሆን የአምስተኛ ትውልድ የቴክኖሎጂ እድገት ላይ ደርሰዋል፡፡ በቅርቡም የቻይናው የስማርት ስልክ አምራች ዜድ ቲኢ በባርሴሎና በዓለም አቀፉ ሞባይል ኮንፈረንስ ላይ አምስተኛ ትውልድ የኔትወርክ አቅም ያለው ስማርት ስልኩን አስተዋውቋል፡፡ ስልኩ በመረጃ ማውረድ ፍጥነቱ የተነሳ ˝ጊጋ ባይት ስልክ˝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ አንድ ጊጋ ባይት መረጃን በሰከንድ የማውረድ (download) አቅም ያለው የመጀመሪያው...

Read More