Author: admin

ዱባይ በዓለም ፈጣን የፖሊስ መኪና ባለቤት ሆነች

ዱባይ በዓለም ፈጣኗን ቡጋቲ ቨይሮን የፖሊስ መኪና ባለቤት ሆነች፡፡ የፖሊስ መኪናዋ በሰዓት 253 ማይል ወይም 407 ኪሎሜትር ትሽከረከራለች፡፡ የዓለም ድንቃድንቅ መዝገብ ለዱባይ ፖሊሶች የዓለም ፈጣን መኪና ባለቤት መሆናቸውን ማረጋገጫ ሰጥቷዋል፡፡ ከቨይሮን የመኪና እሽቅድምድም አሸናፊዋ የስፖርት ተሽከርካሪ ጋር ተመሳስላለች፡፡ በሰዓት 407 ኪሎሜትር የምትጓዘው ይህች ተሸከርካሪ 1 ሺህ የፈረስ ጉልበት ያለው ባለ 16 ሲሊንደር ሞተር ተገጥሞላታል፡፡ ይህ መሆኑ ደግሞ በሁለት ሰከንድ ከግማሽ ጊዜ ውስጥ ከዜሮ ተነስታ 60 ማይል በሰዓት የምትጓዝበትን ፍጥነት ይሰጣታል፡፡ ከዚህ ቀደም የጣሊያን ፖሊስ ኃይሎች የፈጣን ተሽከርካሪ ባለቤት ክብረወሰንን ይሰዘው ነበር፤ ተሽከርካሪያቸው ላምበርጊኒ ጋላራዶ ኤል560-4 ስትሆን በሰዓት 230 ማይሎችን ወይም 370 ኪሎ ሜትሮችን ትምዘገዘግ ነበር፡፡ አሁን የተዋወቀቺው የዓለም ፈጣኗ...

Read More

በተቃራኒ ጾታ ዘንድ ተፈላጊነትን የሚቀንሱ ምክንያቶች

ሁሉም በሚመቸው መልኩና ብዙሃኑ በተቀበላቸው መንገዶች ተቃራኒ ጾታን ለመሳብ የበኩሉን ጥረት ያደርጋል። ቀልድ መቀለድ፣ የተመራጩን ሰው ፍላጎት መሰረት ያደረገ አቀራረብ፣ ስጦታዎች፣ በእግር ጉዞ አጋጣሚን መጠቀምና ሌሎችንም መንገዶች ተጠቅሞ ይህን ለማሳካት የሚደረግ ጥረት ይስተዋላል። በዚህ መልኩ የፈለጉትን ሰው የራስ ማድረግና አብሮነትን ማዝለቅም ይቻል ይሆናል። ተመራማሪዎች ደግሞ አንድን ሰው ተፈላጊ እንዳይሆን የሚያደርጉ ያሏቸውን ምክንያቶች እንዲህ ይዘረዝሯቸዋል። የእንቅልፍ መቆራረጥ፦ ሌሊቱን አሁንም አሁንም ሲባንኑ አድረው እንቅልፍ ሳይጠግቡ ከነቁ ሰዎችን የመማረክና ለእይታ የመሳብ እድልዎ አናሳ ነው። ከዚህ ጋር በተያይዞ በስዊድን እና ኔዘርላንድስ ባደረጉት ጥናት ተደጋጋሚ የሆነ የእንቅልፍ መቆራረጥ የሚስተዋልባቸው ሰዎች ጤናቸው የተስተጓጎለ እና ሰዎችን የመማረክና የመሳብ እድላቸውም ዝቅ ያለ መሆኑን ገልጸዋል። እንቅልፍ ያጡቱ የአይን...

Read More

ቻይናዊቷ በሆዷ ውስጥ እያደገ የነበረ እንጉዳይ በቀዶ ህክምና ወጣላት

ቻይናዊቷ በሆዷ ውስጥ እያደገ የነበረ እንጉዳይን ሀኪሞች በቀዶ ህክምና አውጥተውላታል፡፡ የ50 ዓመቷ ግለሰብ ደረቅ እንጉዳዮችን ሳታበሰብስ እና በደንብ ሳታላምጥ በመመገቧ ነው በሆዷ ውስጥ ብቅለት የጀመረው፡፡ እንጉዳዩ በሴትዮዋ አካል ውስጥ እያደገ እንደነበርም ተነግሯል፡፡ በዚህም እድገቱ 7 ሳንቲሜትር የደረሰው እንጉዳይ የጨጓራ ህመም እያስከተለ ያስቸገራት ሴትዮዋ ወደ ሆስፒታል ስትሄድ ሃኪሞቹ ባደረጉት ምርመራ እንጉዳዩ በጨጓራዋ ተንሰራፍቶ ያገኙታል፡፡ ከቀዶ ጥገና ሀኪሞቹ አንዱ የሆኑት ዶክተር ዋግ ዌይፈይ እንዳሉት፥ በምርመራቸው ወቅት በቀጭን አንጀቷ እና በጨጓራዋ መገናኛ ድንበር ላይ በርካታ የእንጉዳይ ጥርቅም ተገኝቷል፡፡ ሃኪሞቹም ባደረጉላት የቀዶ ህክምና እንጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አውጥተውታል፡፡ ሰዎች እንጉዳይን ከመመገባቸው በፊት በውሃ በደንብ ማራስ ወይም ማበስበስ እና በደንብ አብስሎ አላምጦ መዋጥ እንደሚገባቸውም ተመክሯል፡፡...

Read More

በፈረንጆች 2016 ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን የማያንሱ ቻይናውያን ጥንዶች ለፍቺ ወደ ፍርድ ቤት አምርተዋል

የቻይና ፍርድ ቤቶች በ2016 ከ1 ነጥብ 4 ሚሊየን የማያንሱ ጥንዶችን የፍቺ ጉዳይ መፈፀማቸውን የሀገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ገለጸ፡፡ በተመሳሳይ ዓመት በፍርድ ቤት የፍቺ ጥያቄ ካቀረቡት ውጭ 3 ነጥብ 46 ሚሊየን ቻይናውያን ጥንዶች፥ በማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ በኩል ፍቺ መፈፀማቸውን የቻይና ህዝባዊ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ከፍተኛ ባለስልጣን ዱ ዋንሁዋ ተናግረዋል፡፡ የፍርድ ቤት ዳኞች ለፍቺ በቀረቡት መዝገቦች መሰረት የቤተሰብ ችግሮችን ለማስታረቅ ማህበራዊ እና ስነልቦናዊ ጉዳዮችን እንዳጣሩ ነው ዱ የጠቀሱት፡፡ በዚህም መሰረት 10 ሚሊየን ሰዎች በቀጥታ በችግሩ ውስጥ የተሳተፉ ሲሆን፥ ልጆችን፣ ቤተሰብን እና የቅርብ ዘመዶችን ጨምሮ 50 ሚሊየን የሚሆኑ ሰዎች በፍቺው ምክንያት ለጉዳት ተጋልጠዋል፡፡ የሀገሪቱ ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር እንዳስታወቀው በፈረንጆች 2014 በማህበራዊ ጉዳይ...

Read More

የራስን ሕይወት መቆጣጠር እና መምራትን የሚያዳብሩ 10 ነጥቦች

ሰዎች እቅዳቸውን በሚገባ ለማሳካት ራሳቸውን መቆጣጠር እና መምራት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ፍላጎትን እና እቅድን ባለማጣጣም እንዲሁም መመሪያቸውን በአግባቡ ባለመተግበራቸው የቀን ውሏቸው እና የሕይወት ስኬታቸው ወጣ ገባ ይሆናል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ራስን የመቆጣጠር እና የመምራት አቅምን ለማሳደግ የሚጠቅሙ 10 ምክሮችን አቅርበናል፡፡ 1. በተግባር የሚገለፅ አመለካከት ራስን ማየት በነጻነት የምንሰራቸውን ስራዎች ሃላፊነት እንድንወስድባቸው ያደርገናል፡፡ በመሆኑም ሊተገበር የሚችል አስተሳሰብን ማስፈን እና አስቀድሞ አቅዶ የዕለት ውሎን መምራት ፋይዳው የጎላ ነው፡፡ ይህም ራስን በራስ ለማረም ይረዳል፤ ያልተፈለገ ጭንቀት እንዳያጋጥም ያደርጋል፡፡ 2. ግብ ማስቀመጥ አንድ ሰው ሲኖር የሕይወት ግብ ሊኖረው ይገባል፤ ግቦች ደግሞ ምርጫን ይወስናሉ፤ ግብን በውል ለይቶ ያስቀመጠ ሰው ያሳካዋል፡፡ የተዘበራረቀ ግብ...

Read More