Author: admin

የቆዳ መሸብሸብን እንዴት መከላከል ይቻላል?

የሰውነትዎን ቆዳ ልስላሴና ጤንነት በመጠበቅ የወጣትነት ገጽታዎን ባለበት ማቆየት ይችላሉ። የስነ ውበት ባለሙያዎች ደግሞ ለመልካም የሰውነት ገጽታ የሚረዳውን የቆዳዎን ጤንነት ለመጠበቅ እና የቆዳ መሸብሸብን ለማስወገድ እነዚህን መንገዶች ይከተሉ ይላሉ። አብዝቶ የፀሃይ ብርሃን አለመመታትና ሰውነትን ለፀሃይ ጨረር አለማጋለጥ፤ ሲጋራ አለማጨስ፦ የቆዳ መሸብሸብ የሚያጨሱ ሰዎች ላይ ይከሰታል፤ በሃኪም የሚመከሩ የሰውነት ቆዳ ላይ ቅባቶችን በመጠቀም ቆዳን ማለስለስ፤ በጀርባ መተኛትን ማዘውተር፦ በጎንዎ አልያም በፊትዎ ተደፍተው የሚተኙ ከሆነ አንሶላውና ብርድ ልብሶች ሰውነትዎ ላይ መስመር ያወጣሉ። በጎንዎ መተኛትን ሲዘወትሩ ደግሞ በጭን እና በጉንጭ አካባቢ የቆዳ ላይ መስመሮችን በማውጣት በሂደት የቆዳ ላይ መሸብሸብን ያስከትላል፤ በፊትዎ መተኛት ደግሞ በጭራሽ አይመከርም። አሳን አዘውትሮ መመገብ፦ አሳ በተፈጥሮው የፕሮቲን ምንጭ...

Read More

ለፍቅር የተከፈለ ድንቅ መስዋዕትነት

ፍቅር ባላባቱን ሎሌ የሚያደርግ ታላቅ ሀይል እንዳለው ይነገርለታል᎓᎓ የተለያዩ ፀሀፍቶች ብዙ ብለውለታል᎓᎓ ይህ ታላቅ ሀይል ያለውን የፍቅር ስሜት ድምፃውያኑ ሞዝቀውለታል᎓᎓ ይሁን እንጂ ምንም ቢነገርለትም ከስሜቱ ጥልቀት የተነሳ ተነግሮለት የማያልቅ፣ በየጊዜው አዳዲስ ነገሮችን የሚያስተናግድ እንደሆነ ቀጥሏል። ለአብነትም ፍቅርን በአየር የሚመስሉ ዘፈኖች በብዛት እንሰማለን᎓᎓ «አንተን ማጣት ማለት ልክ አየር በሌለበት ዓለም ውስጥ እንደመኖር ነው»፣ «ስተነፍስ ብቻ ነው የምናፍቅሽ»፣ «የምታስፈልጊኝ ልቤ ሲመታ ብቻ ነው» ተብሎለታል። አስቡት እስኪ ሁሉም የማይቻል ነገር ነው᎓᎓ ነገር ግን በፍቅር ሁሉም ይቻላል᎓᎓ ደግሞም ለአፍቃሪ ሁሉም ነገር ትክክል ነው᎓᎓ እንዴት ከግማሽ አካላችን ውጪ መኖር ይቻለናል? የዘፈኖቹ ሀሳብ እንደምንተነፍሰው አየር ሁሉ ካፈቀሩት ለሰከንድ እንኳን ተለይቶ መኖር ምን ያህል አስቸጋሪ እንደሆነ...

Read More

በርካታ አፍሪካውያን ከቧንቧ ውሃ ይልቅ የሞባይል ስልክን በቀላሉ ማግኘት ይችላሉ- ጥናት

በአፍሪካ በትቦ አማካኝነት የሚቀርን ንጹህ የመጠጥ ውሃ ከማግኘት ይልቅ ሞባይል ስልክ መያዝ እንደሚቀል ጥናት አመልክቷል።ጥናቱ በአፍሪካ ከሚኖሩ ህዝቦች ውስጥ 63 በመቶ የሚሆኑት ብቻ የቧንቧ ውሃን የሚያገኙ ሲሆን፥ 93 በመቶው የአፍሪካ ህዝብ ግን የሞባይል ስልክ ተጠቃሚ ነው ይላል። አፍሮባሮሜትር በሚባል ተቋም የተሰራው ጥናት በ35 የአፍሪካ ሀገራት ላይ የተደረገ ሲሆን፥ ቁጥራቸው 50 ሺህ ለሚጠጉ ሰዎችም ፊት ለፊት ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸዋል። በበርካታ የአፍሪካ ሀገራት ሰዎች በቀላሉ በሞባይል ስልካቸው መነጋጋር ይችላሉ፤ ነገር ግን በዚያው ልክ መብራት አብርቶ መጠቀም እና ውሃን ከቧንቧ መቅዳት የማይታሰብ ነው ይላሉ የጥናት ቡድኑ መሪ ዋይኔ ሚቶላህ። ከአስርት ዓመታት ወዲህ በአህጉሪቱ መሻሻሎች ቢታዩም፤ ለውጡ ግን በሚፈለገው ደረጃ አይደለም የሚሉት ሚቶላህ፥...

Read More

ከ8 ዓመት በፊት የተሰረቀ ቦርሳ በውስጡ ከነበረው 141 ዶላር ጋር ለባለቤቷ ተመልሷል

የቦስተን ከተማ ነዋሪ የሆነቺው የነርሲንግ ተማሪዋ ኮርትነይ ከኖሊ የገንዘብ ቦርሳዋን የተሰረቀቺው በፈረንጆች 2009 ነበር፡፡ ይህን ተከትሎ በውስጡ የያዘውን ገንዘብ ጨምሮ ቦርሳዋን ለማግኘት ብዙ ጊዜ ተጨንቃለች፤ ከተሸከርካሪዋ እንደተወሰደባት እንደምታስታውስ ተናግራለች ኮኖሊ፡፡ ቦርሳው ላለፉት ስምንት ዓመታት ከሰረቀው ግለሰብ ተይዞ በፖሊስ እጅ ነበር፡፡ በዚህ ሳምንትም ፖሊስ የኮኖሊን ቤተሰቦች አድራሻ አፈላልጎ የገንዘብ ቦርሳዋን ውስጡ ከነበረው ገንዘብ እና ከሙሉ እቃው ጋር አስረክቧታል፡፡ ኮኖሊም ከስምንት ዓመት በፊት የጠፋውን ንብረቴን አላገኘውም በሚል እየተጨነቅኩ ነበር ብላለች፡፡ በቦርሳው ውስጥ ያለው ገንዘብ፣ የማህበራዊ ደህንነት ቁጥር እና የመገበያያ ካርዱ ማንም ሳይጠቀምባቸው በነበሩበት የተመለሰላት ኮኖሊ እንደገረማት ነው የገለፀቺው፡፡ በቅርቡ መልካም ዜና ይደርስሻል የሚል መልዕክት በቦርሳው ላይ ማግኘቷን የተናገረቺው ተማሪዋ ሁኔታውን አስገራሚ...

Read More

በአለም ዋንጫ ማጣሪያው በደቡብ አሜሪካ ምድብ ብራዚልና አርጀንቲና ድል ቀንቷቸዋል

የሩሲያው የ2018 የአለም ዋንጫ ማጣሪያዎች በተለያዩ ቀጠናዎች እየተካሄዱ ነው። በደቡብ አሜሪካ ምድብ ሌሊቱን የተለያዩ ጨዋታዎች ተደርገዋል። የምድቡ መሪ ብራዚል ወደ ሞንቴቪዲዮ አምርታ ኡራጓይን 4 ለ 1 አሸንፋ ተመልሳለች። ባለሜዳዎቹ በካቫኒ ጎል ቀደሚ ቢሆኑም፥ ሴሌሳኦቹ በፓውሊንሆና በኔይማር ጎል ታግዘው ሶስት ነጥብ ይዘው ተመልሰዋል። በሊዮኔል ሜሲ የምትመራው አርጀንቲናም ከገባችበት አጣብቂኝ የወጣችበትን ውጤት ማስመዝገብ ችላለች። በሜዳዋ ቺሊን ያስተናገደችው አርጀንቲና በሊዮኔል ሜሲ የፍጹም ቅጣት ምት ጎል 1 ለ 0 አሸንፋለች። ፓውሊንሆ ፓራጓይ በበኩሏ በሜዳዋ ኢኳዶርን አስተናግዳ 2 ለ 1 በማሸነፍ አስፈላጊውን ሶስት ነጥብ ይዛ ወጥታለች። ወደ ሩሲያ ለማምራት እድል ያላት ኮሎምቢያም ቦሊቪያን አስተናግዳ 1 ለ 0 ረታለች። ቬኒዝዌላ ከፔሩ ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ፥ ሁለት...

Read More