Author: admin

የብሪታኒያ ተመራማሪዎች በዓለም ፈጣኑን የቲቢ መመርመሪያ ዘዴ አገኙ

በብሪታኒያ የኦክስፎርድ እና የበርሚንግሃም ተመራማሪዎች የቲቢ በሽታን በአጭር ጊዜ የሚለይ የዲኤንኤ የምርመራ ውጤቶችን በፍጥነት ማግኘት የሚያስችል ዘዴ ይፋ አድርገዋል። ተመራማሪዎቹ ጄኖም ሲኩዌንሲንግ በተባለ የምርመራ ስልት የበሽታውን እያንዳንዱን ጎጂ ህዋስ ዲኤንኤ በአጭር ጊዜ መለየት ችለናል ነው ያሉት፡፡ግኝቱ የቲቢ ህሙማኑ በሽታው ታውቆ መድሃኒቱን ለመጀመር ይወስድባቸው የነበረውን ረጅም ጊዜ በጥቂት ቀናት እንዲጀምሩ የሚያስችል የምርምር ውጤት መሆኑ ነው የተጠቀሰው። ጄኖም ሲኩዌንሲንግ የምርመራ ሂደት የተለያዩ የዲኤንኤ ናሙናዎችን በመውሰድ ከሳምንት በማይበልጥ ጊዜ ውስጥ የምርመራ ውጤቱን እንዲያገኙ እና መድሃኒት እንዲጀምሩ የሚያስችል ነው፡፡ የቲቢን በሽታ በፍጥነት መርምሮ ውጤቱን ማግኘት ህሙማኑ ቶሎ መድሃኒት እንዲጀምሩ በማድረግ በሽታው እንዳይጠነክር እነሱም እንዲድኑ ለማድረግ ይረዳል፡፡ይህ ባይሆን ግን በምርመራ መራዘም ምክንያት በሽታው በህሙማኑ...

Read More

ኖኪያና ፌስቡክ በሰከንድ 32 ቴራ ባይት መረጃን በማስተላላፍ አዲስ ክብረወሰን ያዙ

የቴክኖሎጂ አምራቹ ኖኪያ እና የማህበራዊ ትስስር ድረ ገጹ ፌስቡክ መረጃን በፍጥነት በማስተላለፍ አዲስ ክብረወሰን መስበራቸው ተነግሯል።ኩባንያዎቹ በባህር ስር በሚዘረጋው የፋይበር ኦፕቲክስን በመጠቀም በአንድ ሰከንድ 32 ቴራ ባይት (32 ሺህ ጊጋ ባይት) መረጃን ማስተላለፍ በመቻላቸው ነው ክብረወሰኑን ሊሰብሩ የቻሉት። ኖኪያ እና ፌስቡክ አዲስ የሞከሩት መረጃ የማስተላለፍ ፍጥነት አሁን በጥቅም ላይ ካለው ኦፕቲካል ማስተላለፊያ በ2 ነጥብ 5 እጥፍ እንደሚፈጥን ነው የተነገረው። ሙከራውም 5 ሺህ 500 ኪሎ ሜትር ርዝመት ያለውና ከአሜሪካዋ ኒውዮርክ እስከ አየርላንድ በባህር ስር በተዘረጋው የፋይበር ኦፕቲክስ መስመር ላይ ነው የተካሄደው። በፌስቡክ ኩባንያ የዓለም አቀፍ ኦፕቲካል ኔትዎርክ አርኪቴክት የሆኑት ስቴፈን ግረብ፥ “ፌስቡክ የቀጣዩ ትውልድ የፈጠራ እና ቴክኖሎጂ የማላመድ ፍጥነቱ እንዲጨምር...

Read More

የሞሮኮ “የደስተኛነት ወታደሮች” ድብርትን ለማስወገድ አዲስ ስልት ተከትለዋል

ሞሮኮ በ2017 የዓለም የደስተኞች ሀገራት ሪፖርት ላይ 84ኛ ደረጃ ነው የተሰጣት፡፡ሆኖም ይህን ደረጃ ለማሻሻል ወጣቶቿ ብዙ እየጣሩ ሲሆን በስራቸው “የደስተኛነት ወታደሮች” ተብለዋል፡፡የ20 ዓመቱ አነስ ኤል ሃዲ የሰዎችን አዎንታዊ አስተሳሰብ በዓለም እንዲሰርፅ ከሚፈልጉት ወጣቶች አንዱ ነው፡፡ ከጓደኞቹ ጋር በመሆንም በሞሮኮ በተለያዩ ምክንያች የተደበሩ ሰዎች ዘና እንዲሉ እየሰሩ ነው፡፡ሃዲ እንደሚናገረው በማህበራዊ የትስስር ገጾች የሚለቀቁ ምስሎችና የሚራመዱ ሃሳቦች ሰዎችን ለማህበራዊ ቀውስ እየዳረጉ ናቸው፡፡በመሆኑም በሳይበር ጥቃት እነዚህን ሃሳቦችን የሚያራምዱ ሰዎችን ለመታገል ወስነናል ነው ያለው ሃዲ፡፡ በሌላ በኩል የደስተኛነት ወታደር የተባሉት ወጣቶቹ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ለድብርት የተጋለጡ ሞሮኳውያን ከዚህ አዚም የሚወጡበትን መንገድ ለማመቻቸት ዘና የሚያደርጉ የመድረክ ቲያትሮችን እያዘጋጁ ያሳያሉ፡፡እንደ ፎረም ትያትር ታዳሚዎችም እንዲሳተፉ ያደርጋሉ፡፡...

Read More

ኤፍ ቢ አይ የትራምፕ ረዳቶች ከሩሲያ ጋር ˝በመተባበር የሂላሪ ዘመቻን እንደጎዱ ˝ፍንጭ ማግኘቱ ተሰማ

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የምርጫ ቅስቀሳ ረዳቶች ከሩሲያ ተጠርጣሪዎች ጋር በመመሳጠር የሂላሪ ክሊንተንን የምረጡኝ ዘመቻ የሚጎዱ መረጃዎችን መልቀቃቸውን የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍ ቢ አይ) ፍንጭ ማግኘቱ ተሰማ፡፡ ኤፍ ቢ አይ የሰብዓዊ ስለላ መረጃዎችን ማለትም የጉዞ፣ የንግድ እና የስልክ ቅጂዎችን እንዲሁም የፊት ለፊት ግንኙነቶች እየመረመረ መሆኑን የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት እየተናገሩ ናቸው፡፡ የምርመራ ቢሮው የትራምፕ አራት የቀድሞ ረዳቶች ላይ ምርመራ እያካሄደ መሆኑ ተነግሯል፡፡ማይክል ፍሊን፣ ፖል ማንፎርት፣ ሮጀር ስቶን እና ካርተር ፔጅ ከሩሲያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ቢሆንም፤ አራቱም በጉዳዩ ውስጥ እጃቸው እንደሌለ ገልጸዋል፡፡ ኤፍ ቢ አይ ድምዳሜ ላይ ባይደርስም የትራምፕ ረዳቶች ከሩሲያ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ያቋረጡ ከመሆናቸው በላይ የሩሲያ ባለስልጣናት የግንኙነት አግባቦቻቸውን...

Read More

23 ኢንች ብቻ የሚረዝመው የ21 ዓመቱ ህንዳዊ

የ21 ዓመቱ ህንዳዊ ወጣት ቁመቱ 23 ኢንች አሊያም 58 ሴንቲ ሜትር ብቻ ነው የሚረዝመው። ማንፕሬት ሲንህ የሚባለው ይህ ወጣት የ6 ወር ህጻን ልጅ ያለውን ተክለ ሰውነት ያለው ሲሆን፥ ክብደቱም 7 ኪሎ ግራም ደገማ ነው። የ21 ዓመቱ ህንዳዊ ወጣት የዓለማችን ትንንሽ ሰዎች ተብለው ከሚጠሩት ውስጥ አንዱ መሆኑ እንዳልቀረም ነው በመነገር ላይ የሚገኘው። ወጣቱ በምን አይነት የጤና እክል እንዲህ ሊሆን ቻለ የሚለው እስካሁን በህክምና ያልተደረሰበት ሲሆን፥ የማጠሩ ምክንያት ግን እስከሁን ለበርካቶች ያልተፈታ ሚስጥር ሆኖባቸዋል። ማንፕሬት ሲንህ ሲወለድ ሙሉ ጤናማ እንደነበር የሚናገሩት ወላጆቹ፥ ልክ ስድስት ወር እንደሞላው ግን እድገቱ ሙሉ በሙሉ በቆሙን ነው የሚናገሩት። ወደ ህክምና ባለሙያዎች ብንወስደውም ዶክተሮች ተገቢውን ምርመራ አላደረጉለትም...

Read More