Author: admin

የስዊድኑ ሆቴል ፍቺ ለሚፈጽሙ ደምበኞቹ ካሳ ሊሰጥ ነው

ካንትሪሳይድ ሆቴልስ ግሩፕ የተባለው የስዊድን ሆቴል ከቅርንጫፎቹ በአንደኛው ለተወሰነ ጊዜ በማረፍ አገልግሎቱን የሚጠቀሙ የተኳረፉ ባለትዳሮች፣ በሆቴሉ ቆይታቸው ችግራቸውን የማይፈቱና በአንድ አመት ጊዜ ውስጥ ፍቺ በመፈጸም ትዳራቸውን የሚያፈርሱ ከሆነ ካሳ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ተዘግቧል፡፡ በትዳር ውስጥ የሚፈጠሩ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን በውይይት የመፍታት ባህልን የማዳበር ተልዕኮ ያነገበው ሆቴሉ፤ በተለያዩ ምክንያቶች የተኳረፉ ጥንዶች ከቅርንጫፎቹ ወደ አንደኛው ጎራ በማለት፣ እየተዝናኑ ችግራቸውን በውይይት እንዲፈቱና ትዳራቸውን ከመፍረስ እንዲያድኑ ምቹ ሁኔታን የሚፈጥር ሲሆን፣ በቆይታቸው ችግራቸውን መፍታት ካቃታቸውና በ1 አመት ጊዜ ውስጥ የሚፋቱ ከሆነ፣ ለተፋቺዎቹ የሁለት ቀን አዳር ሙሉ ወጪያቸውን በካሳ መልክ እንደሚሰጥ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ ሆቴሉ ይህንን ያልተመለደ አሰራር የቀየሰው ባለትዳሮች በመካከላቸው ግጭትና አለመግባባት ሲከሰት፣ ከመደበኛው ህይወታቸውና በግርግር ከተሞላው...

Read More

ሞትን ያስቀራል የተባለለት ምርምር በሰው ላይ ሊሞከር ነው

ለሞቱ ሰዎች ዳግም ህይወት መዝራት እንደሚያስችል የታመነት ምርምር የመጀመሪያ ሙከራ በያዝነው የፈረንጆቹ አመት ሊደረግ ቀጠሮ ተይዞለታል። በአሜሪካ ፊላደልፊያ ተቀማጭነቱን ያደረገው ኩባንያ ባዮኩዋርክ በ2016 መጀመሪያ የአዕምሮ ሞት የማይቀለበስ ነገር እንዳልሆነ መግለጹ ይታወሳል። የኩባንያው ዋና ስራ አስኪያጅ ኢራ ፓስተር በግንደ ህዋስ ወይም ስቲም ሴል የህክምና ዘዴ (የሰውን ልጅ ከበሽታ ለመፈወስ በራሱ ህዋስ የማከም ዘዴ) በላቲን አሜሪካ በቅርቡ ሙከራ ይደረግበታል። ሞትን ለማስቀረት ያስችላል የተባለው ሙከራ በየትኛው ሀገር እንደማይካሄድ ስራ አስኪያጁ ባይጠቅሱም በቅርቡ አጠቃላይ የሙከራውን ሂደት የተመለከተ ዝርዝር መረጃ ይፋ እናደርጋለን ብለዋል። ከዚህ ቀደም አንድ ሰው ሞተ የሚባለው የልብ ምቱ ሲቆም፣ መንቀሳቀስ ሲያቆም እና መተንፈስ ሳይችል ሲቀር ነበር። አሁን ግን ከዘመናዊ ቴክኖሎጂዎች መስፋፋት...

Read More

ከአካል ጉዳተኛ ልጃቸው ጋር ትምህርት ቤት እየዋሉ ያስተማሩት እናት የክብር ዲግሪ ተሰጥቷቸዋል

አሜሪካዊቷ እናት አካል ጉዳተኛ ልጃቸው ጋር ትምህርት ቤት በመሄድና ሁሉንም የትምህርት አይነት እኩል በመከታተል ትምህርቱን እንዲያጠናቅቅ በማድረጋቸው የክብር ዲክሪ ተሰጥቷቸዋል። ጁዲ ኦ ኮነር የተባሉት እኚህ እናት በአካል ጉዳት ምክንያት መፃፍ ለማይችለው ልጃቸው ማርተይ ኦ ኮነር የሚማርበት ክፍል ድረስ በመግባት መምህራኖቹ የሚሰጡትን ጽሁፎች እየጻፉለት ከቻፕማን ዩኒቨርሲቲ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የድህረ ምረቃ ትምህርቱን በማጠናቀቅ በማስተርስ ዲግሪ እንዲመረቅ ረድተውታል። የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የነበሩት እና አሁን ከስራቸው በጡረታ የተገለሉት እናት ጁዲ ባሳለፍነው ቅዳሜ በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይም ልጃቸውን በተሽከርካሪ ወንበር እየገፉ ወደ መመረቂያው ስፍራ ወስደውታል። ማርተይ እንደ አውሮፕዋኑ አቆጣጣር በ2012 የመውደቅ አደጋ ደርሶበት ከትክሻው በታች ያለው የሰውነት ክፍሉ መንቀሳቀስ አይችልም። ታዲያ...

Read More

ያለ ንግድ ፈቃድ መነገድ ለአራት ዓመት ፅኑ እስራት ቅጣት

 ሙሉቀን  ቸርነት  ተካሳሽ ነው፡፡  ከሳሽ ደግሞ የፌደራሉ ዓቃቤ ህግ ሲሆን ግለሰቡ የተከሰሰበት የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሹ የፀና የንግድ ፈቃድ ሳይኖረው በንግድ ዓለም በመሰማራቱ ነው ይላል፡፡ ሲዘረዘር ተከሳሽ የሚኖረው በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 05 ክልል ውስጥ ልዩ ቦታው ቀጨኔ ሁለገብ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ አካባቢ በቤት ቁጥር 9999 ውስጥ ነው፡፡ በዚሁ መኖሪያ ቤቱ ውስጥ ወሩና ቀኑ ባልታወቀ ከ2007 ዓመተ ምህረት ጀምሮ ቤቱ እስከታሸገበት እለት መስከረም 23 ቀን 2009 ዓ.ም ድረስ ቤቱን ያለፈቃድ በጋራዥ ስራ መልክ ሲሰራበት በመገኘቱ ለክሱ ምክንያት መሆኑ ተጠቁማል፡፡ ጉዳዩን ሲመለከት የሰነበተው የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት የዓቃቤ ህግን የሰነድ፣ የሰውና ሌሎች የኢግዚቢት መረጃዎችን በማየት...

Read More

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳዑዲ አረቢያ የጀመሩት ይፋዊ ጉብኝት ውጤታማ ነበር ተባለ

የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በሳውዲአረቢያ  የጀመሩት  የመጀመሪያ የውጭ አገር ይፋዊ ጉብኝት  ውጤታማ ነበር ተባለ ። አሜሪካና ሳዑዲ አረቢያ የ350 ቢሊዮን ዶላር የንግድ ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ የአረቡ አገራት አክራሪነትና ጽንፈኝነትን እንዲዋጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የመጀመሪያቸውን የውጭ ሀገር ይፋዊ ጉብኝት በሳዑዲ አረቢያ አድርገዋል ። ፕሬዚዳንት ትራምፕ ሪያድ ንጉስ ካሊድ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ በንጉስ ሳልማን ቢን አብዱልአዚዝና ሌሎች ከፍተኛ የአገሪቱ ባለስልጣናት አቀባበል ተደርጎላቸዋል። የፕሬዚዳንቱ ጉብኝት አሜሪካ ከሳዑዲ አረብያ ጋር ያላትን ግንኙነት የበለጠ የማጠናከር አጀንዳን የሰነቀ ነው ተብሏል፡፡ አክራሪነትን መዋጋትም ሌላው የመሪዎቹ ውይይት የትኩረት አቅጣጫ ነው፡፡ ሁለቱ አገራት በጋራ በሚሠሩባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በስፋት ተወያይተዋል መክረዋል፡፡ የመሪዎቹን ውይይት ተከትሎ በአሜሪካ ታሪክ ከፍተኛ የሆነውን...

Read More