Author: admin

አራት እግር ይዛ የተወለደችው ህጻን በቀዶ ህክምና ትርፍ እግሮቿ ተወገዱላት

አይቮሪኮስታዊቷ የ10 ወር እድሜ ያላት ህጻን ስትወለድ አራት እግር እና ሁለት አከርካሪ ይዛ ነው የተወለደቺው፡፡ ጥገኛ መንትያው በአግባቡ ራሱን ችሎ ባለማደጉ ከሰውነቷ ጋር ተያይዞ እንደተፈጠረ የአዕምሮ ቀዶ ሃኪሙ ዶከተር አር ሩጅ ተናግረዋል፡፡ ህጻን ዶሚኒክ በጀርባዋ እና በአንገቷ ላይ ተጣብቀው በበቀሉት ትርፍ እግሮቿ ምክንያት ትክክለኛ የሰውነት ቅርፅ ይዛ እንዳልተወለደች ነው የተነገረው፡፡ በቺካጎ በሚገኝ አንድ ሆስፒታል በተደረገላት ቀዶ ጥገና ትርፍ እግሮች እና አከርካሪዎች ተወግዶላታል፡፡ ይህ ዓይነቱ ህክምና በጣም ያልተለመደ እና ውስብስብ ነው ተብሏል፡፡ በልጆች የህክምና ማዕከል በተደገረገ ቀዶ ህክምና ስድስት ሰዓታትን የወሰዱ አምስት ቀዶ ጥገናዎች ተሰርቶላታል፡ ህፃኗ በሆስፒታሉ ለአምስት ቀናት ቆይታ አድርጋለች፡፡ ጥገኛ መንትያው ራሱን ልቻለ በመሆኑ ከዶሚኒኬ ልብ እና ሳንባ...

Read More

አፕል ቀዩን አይፎን 7 እና ርካሹን አይፓድ አስተዋውቋል

ግዙፉ የኤሌክትሮኒክስ መሳሪያዎች አምራች ኩባንያ አፕል አዳዲስ ምርቶቹን እያስተዋወቀ ነው። ኩባንያው ከሰሞኑ ረከስ ባለ ዋጋ የአይፓድ ምርቱን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ ከተለመደው ቀለም በተለየ መልኩም የአይ ፎን ስልኩን ለገበያ ሊያቀርብ ነው ተብሏል። አፕል በቀይ ቀለም አይፎን 7 እና አይፎን 7 ፕላስን ያስተዋወቀ ሲሆን፥ በሳምንቱ መጨረሻም ለገበያ ይቀርባሉ። ኩባንያው በሚያደርጋቸው አለም አቀፍ የበጎ አድራጎት ስራዎች ገቢ ማስገኛ ከሆኑት የኩባንያው ምርቶች አንዱ የሆነው ቀዩ አይፎን፥ 699 ዩሮ ዋጋም ተቆርጦለታል። አዲሱ አይፎን ከፍ ያለ የመያዝ አቅም ያለውና ዘመናዊ መሆኑም ተነግሯል። በኩባንያው በመጭው አርብ ለገበያ የሚቀርበው ሌላው ምርት ደግሞ ርካሹ አይፓድ ይሆናል። አይፓዱ 9 ነጥብ 7 ኢንች የስክሪን ስፋት ሲኖረው ቀለል ያለና ምቹ ሆኖ መሰራቱን...

Read More

ትዊተር ከሽብር ጋር ግንኙነት አላቸው ያላቸውን ከ600 ሺህ በላይ አድራሻዎች ዘጋ

የማህበራዊ ትስስር ገጽ የሆነው የትዊተር ኩባንያ 636 ሺህ 248 የትዊተር አድራሻዎች መዝጋቱን አስታወቀ። ኩባንያው ከፈረንጆቹ 2015 አጋማሽ ጀምሮ ነው ይህን እርምጃ የወሰደው።አድራሻዎቹን ከሽብርተኞች ጋር ግንኙነት አላቸው በሚል መዝጋቱንም ኩባንያው ገልጿል። እርምጃው ኩባንያው ሽብርተኝነትን ለመዋጋት የማደርገው እንቅስቃሴየ አካል ነው ብሏል።ከዚህ ውስጥ 376 ሺህ 890 የሚሆኑት በ2016 የመጨረሻዎቹ ስድስት ወራት የተዘጉ መሆናቸውንም ነው የገለጸው። ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ሽብርተኝነትን የሚያስፋፉና የሚያስተዋውቁ የግለሰብ አድራሻዎችን፥ የማህበራዊ ትስስር ገጾች እንዲከታተሉና እርምጃ እንዲወስዱ ሃገራት እየወተወቱ ይገኛል።ይህ የመንግስታት ውትወታም በሰባት በመቶ መጨመሩን ነው የኩባንያው መግለጫ የሚያሳየው። የተለያዩ ሃገራት ከሽብር ጋር ተያያዥነት ያላቸውና ሽብርተኝነትን የሚያስፋፉ መረጃዎች ከማህበራዊ ትስስር ገጾች ማስወገድ የሚቻልበት አሰራር እንዲሰፍን ይፈልጋሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞም የሚጠረጥሯቸው...

Read More

ፍልሰት የቀየረው የኢትዮጵያውያን የዘረመል አወቃቀር

በቅርቡ ይፋ የሆነው በኢትዮጵያውያን የዘረመል አወቃቀር ላይ ያተኮረ ጥናት  የኢትዮጵያውያን ዘረመል አወቃቀር ከጊዜ ወደ ጊዜ ለውጥ እየታየበት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ በጥናቱ መሠረት የሰው ልጆች ፍልሰት ለለውጡ እንደ ምክንያት የሚጠቀስ ሲሆን፣ በአንዳንድ የኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉ ነዋሪዎች ከየመናውያን፣ በሌሎች አካባቢዎች ያሉ ኢትዮጵያውያን ደግሞ ከምዕራብ አፍሪካውያን ጋር ተመሳሳይ ዘረመል እንዳላቸው በጥናቱ ተጠቁሟል፡፡ ከሰዎች ፍልሰት ጋር በተያያዘ የዘር መዋሃድ እንደሚፈጠር ጥናቶች የሚያሳዩ ሲሆን፣ የኢትዮጵያውያንን የዘረመል አወቃቀር ለውጥም በዚሁ ማብራሪያ መረዳት ይቻላል፡፡ በእንግሊዙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋም፣ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ለንደንና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪዎች ጥምረት የተሠራው ጥናት ከ70 በላይ የሚሆኑ የዘር ምድቦችን ከሚወክሉ 1,142 ኢትዮጵያውያን የዘረመል ናሙና ተወስዶ የተሠራ ነው፡፡ ተመራማሪዎቹ በ300 የተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የሚኖሩ...

Read More

ዘርፈ ብዙው የአፋር ባህላዊ ጨዋታ

ከጥቂት ሳምንታት በፊት አዲሱን የኤርትአሌ እሳተ ገሞራ ፍንዳታና ዳሎልን ለመጎብኘት ወደ አፋር ክልል ባቀናንበት ወቅት ካስተዋልናቸው መካከል በክልሉ ለ12ኛው የብሔር ብሔረሰቦች ክብረ በዓል የሚደረገው መሰናዶ ይጠቀሳል፡፡ የብሔር ብሔረሰቦች በዓልን ከሐረሪ ክልል በተረከበው ቀጣዩ አዘጋጅ አፋር ክልል በዓሉን በማስታከክ ከተጀመሩ ፕሮጀክቶች መካከል የስታዲየም ግንባታ ይገኝበታል፡፡ ከበዓሉ ጋር በተያያዘ በርካታ የአገር ውስጥ ጎብኚዎችን የመሳብ ፍላጎት መኖሩን የገለጹልን የአፋር ክልል የባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ መሐመድ ያዩ እንደተናገሩት፣ ስታዲየሙ በተያዘለት ጊዜ እንዲጠናቀቅ እየተሠራ ነው፡፡ አቶ መሐመድ ከስታዲየም ግንባታው ጎን ለጎን ለጎብኚዎች ምቹ ማረፊያ በማዘጋጀት እንዲሁም ክልሉን በማስዋብ ረገድ እየተደረገ ስላለው እንቅስቃሴም ይናገራሉ፡፡ ስለ ስፖርታዊ ክንውኖች ሲነሳ ቀዳሚ ቦታ ከሚሰጣቸው ስታዲየም አንዱ እንደመሆኑ...

Read More