Author: admin

በአዲስ አበባ በቤንዚን አቅርቦት ችግር ለእንግልት መዳረጋቸውን አሽከርካሪዎች ገለፁ

በአዲስ አበባ በሚገኙ ነዳጅ ማዳያዎች በተፈጠረ የቤንዚን አቅርቦት ችግር ለእንግልት መዳረጋውን  አሽከርካሪዎች ገለፁ፡፡ ባለፉት 3 እና 4 ቀናት በአዲስ አበባ የሚገኙ  ነዳጅ ማደያዎች ረጃጅም የተሽከርካሪ ሰልፎች ሲያስተናግዱ ተስተውለዋል᎓᎓ ችግሩም በቤንዚን አቅርቦት ላይ እየተስተዋለ መሆኑን ነው ኢቢሲ ያነጋገራቸው አሽከርካሪዎች የገለፁት᎓᎓ የታክሲ አገልግሎት የሚሰጥ አንድ አሽከርካሪ የተፈጠረው ችግር በስራው ላይ እቅንቅፋት እንደሆበት ለኢቢሲ ተናግሯል፡፡ “ቢያንስ እኔ የቆምኩት ከ2 ሰአት በላይ ሁኖኛል፤ ከቤተመንግስት አካባቢ ነው የመጣሁት ፡፡የተጨመረው ተጨምሮ ቤንዚኑ በቶሎ ይድረስልን” ሲል ጠይቋል᎓᎓ የነዳጅ ማደያዎች ግን የአቅርቦት ችግር ያለመኖሩን ነው የሚገልፁት᎓᎓በማደያዎቹ አካባቢ ሰልፉ መኖሩን አምነው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ግን እንደማያውቁ ተናግረዋል፡፡ የማዕድን ፣ነዳጅና ተፈጥሮ ጋዝ ሚኒስቴር ችግሩ የአቅርቦት  ሳይሆን ኢታኖል የተቀላቀለበት ቤንዚን...

Read More

ኢትዮጵያ የምትታወቅበት የብራንድ ስያሜ “ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት” የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ፀደቀ

ኢትዮጵያ የምትታወቅበት ብራንድ ወይም ልዩ ምልክት የሆነው ኢትዮጵያ ዘላንድ ኦፍ ኦሪጅንስ “ኢትዮጵያ ምድረ ቀደምት” የሚል አቻ የአማርኛ ትርጉም ይፋ ሆነ፡፡ የቱሪዝም ትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት አራተኛ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ ምክር ቤቱ  በባለፈው ጉባኤው ሃገሪቱ በቱሪዝም  የምትተዋወቅበት ልዩ ምልክት “ኢትዮዽያ ዘ ላንድ ኦፍ ኦሪጂን” አፀድቆ የነበረ ሲሆን በዚህኛው ጉባኤውም  ትርጓሜውን “ኢትዮዽያ ምድረ ቀደምት”የአማርኛው የቱሪዝም  ልዩ ምልክት  ሁኖ በጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ ፀድቋል᎓᎓ የትራንስፎርሜሽን ምክር ቤት ሰብሳቢ ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ  ምክር ቤቱ  ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶ በርካታ ስራዎችን ያከናወነ  ቢሆንም አገሪቱ  ካላት ሰፊ የቱሪዝም ሃብት አነፃር ሲታይ አሁንም ተግባሩ አናሳ መሆኑን ገልፀዋል᎓᎓ የቱሪስት መስተንግዶ ተቋማት በተለይም አለም አቀፍ ተወዳዳሪነታቸውን  ለማሳደግ ከአለም ቱሪዝም...

Read More

ቻይናዊው ደረጃዎችን በጭንቅላቱ በመውጣት የአለም ክብረወሰን ሰበረ

ይናዊው በዓለም ድንቃ ድንቅ መዝገብ “Guinness World Book of Records” በጭንቅላቱ ቆሞ ደረጃዎችን በመወጣት ክብረወሰኑን ሰብሯል። ቻይናዊው ሊ ሎንግሎንግ የተባለው ግለሰብ በዚህ ሳምንት 36 ተከታታይ ደረጃዎችን በራሱ ቆሞ በመውጣት ተመልካቹን አስደንቋል፡፡ ከዚህ ቀደም ክብረወሰኑን ለመስበር ሞክሮ ያልተሳካለት ሊ ሎንግሎንግ ጠንካራ ልምምድ ባማድረግ ስሙን ድንቃ ድንቅ መዝገብ ላይ ማስፈር ችሏል፡፡ ክብረወሰን ለማግኝት ጥብቅ መመሪያዎች መከተል አስፈላጊ መሆኑ የተለጸ ሲሆን ተወዳዳሪው ከአምስት ሰከንዶች በላይ መቆም እንደማይችል እንዲሁም ሌላ የሰውነት ክፍሉ ደረጃውን መንካት እንደማይችል ዘገባው ያስረዳል፡፡ ምንጭ፤ ጊነስ ዎርልድ ኦፍ...

Read More

የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ የሰብዓዊነት ተግባር ለደቡብ ሱዳን

በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አዘጋጅነት በደቡብ ሱዳን ጁባ ለመጀመሪያ ጊዜ ከ5 ሺ በላይ አትሌቶች የሚሳተፉበት የጎዳና ላይ ሩጫ እንደሚያካሂድ ተገለፀ። ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አይሸሹም ተካ ከተባሉ ግለሰብ ጋር በመተባበር የሚያካሂዱትን የሩጫ ውድድር አስመልክቶ ትናንት መግለጫ በተሰጠበት ወቅት፣የታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ መስራችና የቦርድ ሊቀመንበር አትሌት ኃይሌ ገብረስላሴ እንደገለፀው፣ ስፖርት የሰላም ተምሳሌት ነው። ስፖርት ፆታ ዘር ቀለም ሃይማኖት አይለይም። ስፖርት ሁለት አገራትን ብቻ ሳይሆን ዓለምን ያስተሳስራል። አንድነትን ያጠነክራል። በታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስተባባሪነት ለመጀመሪያ ጊዜ የሚካሄደው የደቡብ ሱዳን ታላቁ ሩጫም በአገሪቱ ዜጎች መካከል ሰላምና አንድነትን ለማጎልበትና በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ የተከሰተው ድርቅ የዓለምን ትኩረት እንዲያገኝ ዓላማው ያደረገ ነው። «የጎረቤት አገራት ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም መሆን ፋይዳው...

Read More

በገጠር የሚኖሩ 51 በመቶ ኢትዮጵያውያን ንፁህ ውኃ እንደማያገኙ ሪፖርት አመለከተ

በገጠር የሚኖሩ 51 በመቶ ኢትዮጵያውያን ንፁህ ውኃ እንደማያገኙ ወተር ኤድ ‹‹ዘ ስቴት ኦፍ ዘ ወርልድስ ወተር 2017›› በሚል ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል፡፡ ሪፖርቱ በገጠር የንፁህ ውኃ ተደራሽነት ችግር ባለባቸው ቀዳሚ አሥር አገሮችና በንፁህ ውኃ ችግር የሚሰቃየውን የኅብረተሰብ ክፍል በመቶኛና በቁጥር ለይቶ አስቀምጧል፡፡ በሪፖርቱ መሠረት ኢትዮጵያ፣ በቁጥር ሲሰላ 40.9 ሚሊዮን የንፁህ ውኃ ችግር ያለባቸው የገጠር ነዋሪዎች መገኛ በመሆን ከህንድ፣ ከቻይናና ከናይጄሪያ ቀጥላ ከቀዳሚዎቹ ችግር ካለባቸው አገሮች በአራተኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች፡፡ በመቶኛ ሲሰላ ደግሞ በሪፖርቱ ከተካተቱት አገሮች በ15ኛ ደረጃ ላይ ተመድባለች፡፡ በንፁህ ውኃ ተደራሽነት ረገድ ከመጨረሻዎቹ 10 አገሮች ተርታ የተሰለፈችው አገሪቱ ግን ትልቅ መሻሻልን እያሳየች መሆኑም በሪፖርቱ ተካቷል፡፡ እ.ኤ.አ. 2000 በገጠራማው የአገሪቱ...

Read More