Author: admin

የዕድሜ ባለ ፀጋው ዴቪድ ሮክፌለር ሕልፈት

በሕይወት ዘመናቸው ሙሉ በአገር ውስጥና በውጭ አገሮች ግንኙነት ዙሪያ በተቀረፁ ፖሊሲዎች ውስጥ በመግባትና ቡድን በማዋቀር ሠርተዋል፡፡ ካርኒጊ ኢንዶውመንት ፎር ኢንተርናሽናል ፒስ ውስጥ ከ34ኛው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዲዋይት አይዘንአወር፣ ከአይቢኤም ፕሬዚዳንት ቶማስ ዋትሰን፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ለመመሥረት ከተሳተፉትና በኋላም ለቀድሞዋ ሶቪየት ኅብረት ሰልለዋል ከተባሉት የአሜሪካ ባለሥልጣን አልገር ሄስ፣ እንዲሁም ከ52ኛው የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ፎስተር ዳላስ ጋር በመሆን በቦርድ አባልነት አገልግለዋል፡፡ በአሜሪካ ከታዋቂው የንግድ ሰው ሶል ሊኖውትዝና ከሌሎችም ጋር በመሆን በደሃ አገሮች ቀጣይነት ያለው ልማት ለማምጣትና የግሉን ዘርፍ ለማበረታታት፣ ለትርፍ የማይሠራውን ዓለም አቀፍ ኤግዙኪዩቲቭ ሰርቪስ ኮርፕ ካቋቋሙዋቸው ድርጅቶች ውስጥ ይጠቀሳሉ፡፡በአገራችን አንድ ሰው ገንዘብ ካለውና ሲበትን ከተስተዋለ ‹‹ሮክፌለር ነው!›› እንደሚባለው ዓይነት...

Read More

ጀርመን በሲግናል ኤዱና ፓርክ እንግሊዝን በወዳጅነት ጨዋታ ትገጥማለች

ታላላቅ የአውሮፓ ሊጎች ተቋርጠው ተጫዋቾች ወደ ብሄራዊ ቡድኖቻቸው ሲመለሱ ለ2018ቱ የሩስያ አለም ዋንጫ ዝግጅት በወዳጅነት ጨዋታ የሚገናኙ ይሆናል። ዛሬ ምሽት ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል የ2014ቱ የአለም ዋንጫ አሸናፊ ጀርመን በሲግናል ኤዱና ፓርክ እንግሊዝን የምታስተናግድበት ጨዋታ ትኩረትን የሳበ ሆኗል። ሁለቱ ቡድኖች የቅርብ ተቀናቃኝ ከመሆናቸውም በላይ ከፈረንሳዩ የአውሮፓ ዋንጫ ወዲህ ተሸንፈው አለማወቃቸው የዛሬው ጨዋታ ትልቅ ፉክክር ሊታይበት እንደሚችል ግምት እንዲሰው አድርጓል። በምሽቱ ጨዋታ ፊል ጆንስና ሚኬል አንቶኒዮ በጉዳት ለእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አይሰለፉም፤ በጀርመን በኩል ሜሱት ኦዚል ጉዳት ላይ የሚገኝ ሲሆን ከዛሬው ጨዋታ ውጭ መሆኑ ታውቋል። 130ኛና የመጨረሻ የብሄራዊ ቡድን ጨዋታውን የሚያከናውነው ሉካስ ፖዶልስኪ ዛሬ ምሽት የጀርመን ብሄራዊ ቡድንን በአምበልነት እየመራ ወደ ሜዳ...

Read More

በአምባገነኖች መላወሻ ያጡ ህዝቦች

በአፍሪካ ደረጃ የዲሞክራሲ ሂደትን ለማበረታታት የተቋቋመው የኢብራሂም የሽልማት ፕሮግራም (የሞህ ኢብራሂም ፋውንዴሽን አካል) በቅርቡ እንዳስታወቀው፤ የመድብለ ፓርቲ ባህል በሃገሩ ለማስጀመር ወይም ለማስቀጠል የቆረጠ የአፍሪካ መሪ በመታጣቱ በያዝነው ዓመት ያዘጋጀውን የሽልማት ገንዘብወደ ካዝናው መልሶታል፡፡ የሽልማቱ መጠን አጓጊ ሲሆን በአስር ዓመት ተከፍሎ የሚያልቅ አምስት ሚሊየን ዶላር ገንዘብና እድሜ ልክ በየአመቱ የሚከፈል ሁለት መቶ ሺህ ዶላር የጡረታ አበል ያካትታል፡፡ እንደ ድርጅቱድረ ገጽዘገባ፤ ለሽልማቱ ለመወዳደር እጩ የሚሆኑ የአፍሪካ መሪዎች በምርጫ ወደ ስልጣን የወጡ፣ በህገ መንግስታቸው የተደነገገውን የምርጫ ግዜ አጠናቀውከስልጣን በሰላም የወረዱ እንዲሁም በስልጣን ዘመናቸው ምሳሌ የሚሆን ተግባር የፈጸሙ መሆን ይገባቸዋል። ድርጅቱ ከተቋቋመ 2006 (እ.ኤ.አ) ጀምሮ ብቁ ተሸላሚዎች ሲታጡ ለተደጋጋሚ ግዜ መሆኑንም ገልጿል፡፡ እንደሚታወቀው...

Read More

የአለማችን ውዱ በርገር በ10 ሺህ ዶላር ተሽጧል

በዱባይ የአለማችን ውዱ በርገር በ10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር መሸጡ ተሰምቷል። በከተማዋ ጋለሪስ ላፋየት ሞል ለሽያጭ ከቀረበው በርገር የተገኘው ገቢ ለበጎ አድራጎት ስራ እንደሚውል ነው የተነገረው። አስማ አል ፋቲህ የተሰኙ ባለሃብት በርገሩን በጨረታ አሸንፈዋል፤ ጥያቄው ፋቲህ ይህን ውድ በርገር ጨክነው ይበሉት ይሆን የሚለው ነው። በዱባይ ውድ ዋጋ ያወጣው በርገር ከዚህ ቀደም በተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ለበጎ አድራጎት ስራ በፒንክ ካራቫን ቡድን 7 ሺህ የአሜሪካ ዶላር የተሸጠውን በርገር በ3 ሺህ ዶላር በመብለጥ ነው ክብረወሰኑን የያዘው። ፒንክ ካርቫን በጡት ካንሰር ዙሪያ የቅድመ መከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን የሚያከናውን ድርጅት ነው። ድርጅቱ ለዚሁ ስራው እንዲያግዘው በአሜሪካ ላስ ቬጋስ ጨረታ በማካሄድ በርገር በ5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር...

Read More

ሰሚ ያጣው በቦኮሃራም የታገቱ የቺቦክ ትምህርት ቤት ልጃገረዶች ጩኸት

በናይጄሪያ በሰሜን ምስራቅ ክፍል በቦርኖ ግዛት ከሚገኘው ከቺቦክ ከተማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት 276 ሴት ተማሪዎች በአሸባሪው ቦኮሃራም ታግተው ከተወሰዱ ድፍን ሦስት ዓመት ሊሞላ አንድ ወር ብቻ ይቀራል ፡፡ እንደ አውሮፓውያኑ በ2014 ሚያዚያ ወር መባቻ ላይ አሸባሪ ቡድኑ ኮረዳዎቹን አግቶ ወዳልታወቀ ሥፍራ መውሰዱን ተከትሎ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድርጊቱን በጥብቅ አውግዞታል። ይህንንም ተከትሎ በርካታ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ተቋማት እና ግለሰቦች ልጃገረዶቹ ከእገታ እንዲለቀቁ እና የመማር መብታቸው እንዲከበር ቅስቀሳዎችን ሲያካሂዱ ቆይተዋል ፡፡ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተደረጉት የማስለቀቅ ዘመቻዎች 81 ልጃገረዶችን ብቻ ማስለቀቅ የተቻለ ሲሆን ፣ 195ቱ ግን እስካሁን እንደታገቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ሴቶች ያሉበት ቦታ ሳይታወቅ ሦስት ዓመት ሊሞላ ነው...

Read More