Author: admin

የጃፓን አዛውንቶች የመንጃ ፈቃዳቸውን ከመለሱ የቀብር ወጪያቸው ሊቀነስላቸው ነው

የጃፓን መንግስት በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ እየተጨመረ የመጣውን የትራፊክ አደጋ ለመቀነስ የእድሜ ባለጠጎች የመንጃ ፈቃዳቸውን እንዲመልሱና ማሽከርከር እንዲያቆሙ በመጠየቅ ላይ ነው። ለዚህም ይመስላል አዛውንቶች ማሽከርከር ካቆሙ ወይንም መንጃ ፈቃዳቸውን ከመለሱ የቀብር ማስፈፀሚያ ወጪያቸው ላይ ቅናሽ ይደረግላቸዋል የተባለው። በማዕከላዊ ጃፓን አይቺ ግዛት ነው አንድ 89 የመቃብር ቤቶችን የሚያስተዳድረው ኩባንያ የመንጃ ፈቃዳቸውን ለሚመልሱ አዛውንቶች የ15 በመቶ ቅናሽ ማድረጉን ያስታወቀው። ኬይዶ የተባለ የዜና አገልግሎት እንደዘገበው፥ ማንኛውም መንጃ ፈቃዱን መመለስ የሚፈልግ የእድሜ ባለጠጋ በአካባቢው ወደሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ በመሄድ በማመልከት የቅናሹ ተጠቃሚ መሆን ይችላል ተብሏል። ቅናሹ የማዕከላዊ አይቺ ግዛት ነዋሪ ያልሆኑ ነገር ግን ቤተሰቦቻቸው በዚያው የሚገኙ ሰዎችንም ተጠቃሚ ያደርጋል ነው የተባለው። እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2015...

Read More

ቱሪስቶች ጨረቃን ሊጎበኙ ነው

ስፔስ ኤክስ የተባለ የአሜሪካ የግል ሮኬት አምጣቂ ኩባኒያ እኤአ 2018 ሁለት ቱሪስቶችን ወደ ጨረቃ ወስዶ ሊያስጎበኝ እንደሆነ አስታወቀ፡፡ የቱሪስቶቹ የጨረቃ ጉዞ የሰው ልጅ ጥልቅ ወደ ሆነው የህዋ ክፍል ሲመጥቅ ከ45 ዓመታት ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ መሆኑን የስፔስ ኤክስ ዋና ሀላፊ ኤሎን ሙስክ ገልፀዋል፡፡ ሀላፊው አክለውም በቀጣዩ አመት መጨረሻ አካባቢ ሁለት ጎብኝዎችን ይዞ ለመጓዝ ዕቅድ እንደተያዘና ቱሪስቶቹም የሚጠበቅባቸውን ክፍያ አብዛኛውን ከፍለው ማጠናቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡ የቱሪስቶቹ ማንነት ለጊዜው ይፋ ያልተደረገ ሲሆን ከአሜሪካኑ የጠፈር ምርምር ተቋም ናሳ ጋር በመተባበር በዚህ አመት መጨረሻ የሙከራ በረራ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ የስፔስ ኤክስ ዋና ሀላፊ በሰጡት መግለጫ ወደ ጨረቃ የሚጓዙት ጎብኝዎች በቅርቡ የጤና ምርመራ እና የአካል ብቃት ፍተሻ...

Read More

ካናዳዊቷ መምህር የዓመቱ ምርጥ ተብላ የ1 ሚሊዮን ዶላር አሸነፊ ሆናለች

በየ ዓመቱ በሚካሄደው የዓመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት ካናዳዊቷ ማጂ ማክዶኔል የዓመቱ ምርጥ መምህር ተብላ የ1 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ለመሆን በቅታለች፡፡በውድድሩ ከተለያዩ አህጉራት የተወጣጡ 20ሺህ መምህራን ተሳትፍዋል፡፡ህልሜ አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ትውልድ መፍጠር ነው ስትል ተሸላሚዋ ማጂ ተናግራለች፡፡ ተሸላሚዋ ማጂ በካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሪዶ የመጪውን ዘመን ቀራጭ ተብላ ተሞካሽታለች፡፡በአርክቲክ በረዶ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናትን ፈጠራ በታከለበት መንገድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድርጓ  የተሸላሚዋ ልዩ ጥረት ተብሏል፡፡ልማቱን ያበረከተው አከባቢና ትምህርት ጥራት የሚሰራው ቫርኪ ፋውንዴሽን የተባለ ድርጅት ነው፡፡ ምንጭ፡-ዩሮ...

Read More

አትክልትና ፍራፍሬዎች የሴቶችን የጭንቀት ተጋላጭነትን ይቀንሳሉ – ጥናት

አትክልትና ፍራፍሬን አብዝቶ መመገብ ለመላው ጤንነት መልካም መሆኑን የህክምና ባለሙያዎች ይመክራሉ። ከዚህ ጋር ተያይዞ በተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና የምርምር ማዕከላት የዚህን ጠቀሜታ የተመለከተ ጥናትና ምርምር ይደረጋል። በአውስትራሊያ የሲድኒ ዩኒቨርሲቲ የተደረገ ምርምር ውጤትም ከሰሞኑ ይፋ ሆኗል። ጥናቱ አትክልትና ፍራፍሬን መመገብ ለአዕምሮ ጤናና ጭንቀትን ከማስወገድ አኳያ ያለውን ጥቅም የተመለከተ ነበር። እናም በቀን አትክልትና ፍራፍሬን አብዝቶ መመገብ ጭንቀትን በተለይም በሴቶች በኩል ለመቀነስ ይረዳል ነው የሚለው የጥናቱ ውጤት። በጥናቱ እድሜያቸው 45 አመትና ከዛ በላይ የሆኑ 60 ሺህ 404 ወንድ እና ሴቶች ተካተዋል። ለሶስት አመታትም የሰዎቹ አመጋገብ በየቀኑ የተፈተሸ ሲሆን፥ በቀን ምን ያክል አትክልትና ፍራፍሬ እንደሚመገቡም ተለይቷል። በእነዚህ ጊዜያት ታዲያ የሰዎቹ የስነ ልቦና ጥንካሬ...

Read More

በስሙ ምክንያት 40 የስራ ማመልከቻዎች ውድቅ የተደረጉበት ኢንጅነር ሳዳም ሁሴን

ህንዳዊው ሳዳም ሁሴን በታሚል ናዱ ኖሩል ዩኒቨርሲቲ በባህር ሃይል ምህንድስና ትምህርት ዘርፍ በጥሩ ውጤት ተመርቆ ወጥቷል።ከምረቃ በኋላ አብረውት የተማሩት የትምህርት ቤት ጓደኞቹ ወደ ስራ አለም ሲሰማሩ እርሱ ግን በስራ ፍለጋ ብዙ ለፍቷል። በዩኒቨርሲቲው በጥሩ ሁኔታ ስለመማሩ የትምህርት ማስረጃው ቢገልጽም፥ አያቱ ከ25 አመት በፊት ያወጡለት ስም ግን ለዚህ እንቅፋት ሆኖበታል።ወጣቱ የትምህርት ማስረጃዎቹን በመያዝ ወደ 40 ለሚጠጉ ጊዜያት ቢያመለክትም “ሳዳም ሁሴን” የሚለው መጠሪያው ችግር ፈጥሮታል። ሳዳም ሁሴን በሃገራቸው ህዝብ ላይ ጭቆናን ፈጽመዋል ተብለው የተወነጀሉና የቀድሞው የኢራቅ መሪ መጠሪያ ስም ነበርና። እናም ይህን ስም ይዘህ በኩባንያችን ውስጥ እንዴት ትሰራለህ በሚል ሁኔታ ደጃቸውን የጠናቸው ተቋማት ምሩቁን ለመቅጠር አሻፈረኝ ብለዋል።በዚህ ሳቢያ የበርካታ ድርጅቶችን ደጅ...

Read More