Author: admin

ጉንፋንን በቤት ውስጥ ማከሚያ መንገዶች

ጉንፋን በአብዛኛው በቫይረስ አማካኝነት የሚተላለፍ በሽታ ነው።ጉንፋን የተለመደ በሽታ እንደመሆኑ መጠን ምናልባትም በአመት ሁለት እና ከዚያ በላይ ለሆነ ጊዜ ለዚህ በሽታ የመጋለጥ እድል መኖሩን ጥናቶች ያመለክታሉ። ጉንፋንን ሙሉ በሙሉ ማስቀረት ባይቻልም ማከም እና መከላከል ግን ይቻላል፤ ለዚህ ደግሞ አብዛኛውን ጊዜ በቤት ውስጥ በሚዘጋጁ መፍትሄዎች መከላከል እንደሚቻል ባለሙያዎች ይናገራሉ። እነዚህ መከላከያ መንገዶች ደግሞ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ጨምሮ፣ የአፍንጫ መዘጋት እና መታፈን፣ ሳል፣ የፊት እና በተለይም የአፍንጫ አካባቢ መቅላት እና ህመምን መከላከል ያስችላሉ። መፍትሄ መጉመጥመጥ፦ አፍን ወደ ላይ ቀና አደርጎ ከጀርባ ወደ ኋላ ገለል በማለት ጥቂት ውሃ ወደ ጉሮሮ በማፍሰስ መጉመጥመጥ የጉሮሮ መከርከርና ማቃጠልን ለመከላከል ይረዳል።ለዚህ ደግሞ 1 የሻይ ማንኪያ ጨውን ለብ...

Read More

ጎግልና ሌቪስ አዲስ የሰሩትን ስማርት ጃኬት ይፋ አደረጉ

የቴክኖሎጂ ኩባንያው ጎግል እና የልብስ አምራቹ ሌቪስ በአይነቱ ለየት ያለ ስማር ጃኬት መስራታቸውን አስታውቀዋል።የቴክኖሎጂ እና የልብስ አምራች የሆኑት ሁለቱ ግዙፍ ኩባንያዎች በጥምረት በመሆን የሰሩት ስራ የቴክኖሎጂ እና የፋሽን ዓለምን አንድ ላይ የሚያስተሳስር ነው ተብሏል።ኩባንያዎቹ በአንድ ላይ በመሆን የዓለማችንን የመጀመሪያ ስማርት ጃኬት የሰሩ ሲሆን፥ ጃኬቱ ውስጥም የኤሌክትሮኒክስ ክሮች እንዲገቡ ተደርጎ ነው የተሰራው። “ፕሮጄክት ጃኩዋርድ” በመባል የሚጠራው የስማርት ጃኬት ስራው እንደ አውሮፓውያን አቆጣጣር በ2015 የተጀመረ ሲሆን፥ “Commuter™” በሚል የንግድ ስያሜም ተሰጥቶታል። አዲሱን ስማርት ጃኬት ከስማርት ስልካችን ጋር በቀላሉ ማገናኘት የምንችል ሲሆን፥ ስልካችንን ከኪሳችን ውስጥ ሳናወጣ በስማርት ጃኬቱ ብቻ ስልክ ማነጋጋር፣ ሙዚቃ ማዳመጥ፣ አቅጣቻዎችን ለማወቅ እና መሰል ተግባራትን ለማከናወን ያስችለናል። ስማርት ጃኬቱ...

Read More

በአዲስ አበባ ቆሼ በሚባለው አካባቢ የተከመረ ቆሻሻ ተደርምሶ እስካሁን የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ

በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የተከመረ ቆሻሻ በ15 መኖሪያ ቤቶች ላይ ተደርምሶ እስካሁን የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ። የአዲስ አበባ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ፥ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ተከምሮ የነበረው ቆሻሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው በሚገኙ ቤቶች ላይ ተደርምሶ ጉዳት አድርሷል። ትናንት በምሽት በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪም በ37 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል። በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአለርት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው...

Read More

ህንድ ለሴቶች የሚሰጠውን የወሊድ ፍቃድ ከ12 ወደ 26 ሳምንት አሳደገች

የህንድ ፓርላማ ሴቶች በሙሉ ክፍያ የሚወጡትን የወሊድ ፍቃድ ከ12 ሳምንት ወደ 26 ሳምንት የሚያሳድግ ህግን አፀደቀ። አዲሱ ህግ ከ10 በላይ ሰዎችን በስራቸው ቀጥረው በሚያስተዳድሩ ተቋማት በሙሉ ተግባራዊ ይሆናል፡፡ የህንድ የሠራተኞች ሚኒስትር ባንዳሩ ዳታትሬያ ህጉ ለሴቶች ከሚገባቸው በታች ነው ብለዋል። ኒው ደልሂ የወሊድ ፍቃድ ህጓን ስታሻሻል ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነው። በዚህም 50 እና 44 ሳምንታት የወሊድ ፍቃድን በቅደም ተከተል ከሚሰጡት ካናዳ እና ኖርዌይ ቀጥላ ሶስተኛዋ ረጅም ጊዜ የወሊድ ፍቃድን በሙሉ ክፍያ የሰጠች ሀገራ ሆናለች። ሆኖም ሴቶቹ 26 ሳምንቱን በሙሉ ክፍያ የወሊድ ፍቃድ የሚወጡት በመጀመሪያ ለሚወለዷቸው ሁለት ልጆች ብቻ ነው። ከመጀመሪያ ሁለት ልጆቻቸው በተጨማሪ የሚወልዱ ከሆነ የወሊድ ፍቃዱ 12 ሳምንት ብቻ...

Read More

በማዳጋስካር ከእግር ኳስ ጨዋታ ይልቅ የዶሮ ፍልሚያ ታዋቂ መሆኑን ያውቃሉ?

በአፍሪካዊቷ ሀገር ማዳጋስካር በአለማችን የብዙዎችን ቀልብ ከሚስበው የእግር ኳስ ጨዋታ ይልቅ የዶሮዎች ግጥሚያ በርካታ ተመልካች አለው። በመዲናዋ አንታናናሪቮ አምቦሂማንጋኪሊ አካባቢ የዶሮዎች ፍልሚያ መመልከት የተለመደ እና ተወዳጅ መዝናኛ ነው። የዶሮ ግጥሚያ በሚኖርባቸው ጊዜያት ከ400 በላይ ሰዎች በአምቦሂማንጋኪሊ የዶሮዎች መፋለሚያ ስፍራዎችን ያጣብባሉ። ከሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎችም የዶሮ አርቢዎች ምርጥ ተፋላሚ ዶሮዎቻቸውን ለማሳየት ወደ አምቦሂማንጋኪሊ ያመራሉ። የግጥሚያዎቹ ተመልካቾችም ያሸንፋል ብለው ለሚያስቡት ዶሮ ገንዘብ በማስያዝ ከሌሎች ሰዎች ጋር ይወራረዳሉ። በአንድ ግጥሚያ ብቻም እስከ 12 ሚሊየን አሪያሪ ወይንም 3 ሺህ 870 የአሜሪካ ዶላር በውርርድ ይንቀሳቀሳል ተብሏል። የዶሮዎች ግጥሚያ የሚጠናቀቀው ተጋጣሚዎቹ ለሁለት ስአታት ሳይሸናነፉ ከቆዩ፣ አንደኛው ተጋጣሚ ሁለቱንም አይኖቹን ካጣ አልያም የመፋለም ፍላጎት ካላሳየ፣ ወይንም ሁለቱም...

Read More