Author: admin

የህፃናትን የእምሮ የእድገት ደረጃ የሚያሳይ አዲስ የምርምር ውጤት ይፋ ተደረገ

የእንግሊዝ ተመራማሪዎች የህፃናት የአእምሮ የእድገት ደረጃን የሚያሳይ የመጀመሪያ የሆነውን የምርምር ውጤት ይፋ አድርገዋል፡፡ ይህ ግኝትም በመላው አለም ያሉትን ተመራማሪዎች ጤናማ የአእምሮ የእድገት ሂደትን ማወቅ ያስችላቸዋል ሲሉ ዘ ድቨሎፒንግ ሁማን ኮኔክተም የተሰኘ  ፕሮጀክት ባለሙያዎች ተናገረዋል፡፡ ጥልቅ የሆነው የኤም አይ አር የምርመራ ውጤት በአእምሮ ላይ የሚከሰቱ የአዕምሮ መዛባቶችንና ኦቲዚምን ይበልጥ ማወቅ ያስችላል ብለዋል፡፡ ግኝቱ እነዚህ በአእምሮ ውስጥ የሚገኙና በቢልየኖች የሚገኙ  ውስብስብ የአእምሮ ክፍሎችንም መለየት ያስችላል ተብሏል፡፡ ከ ለንደን ኪንግስ ኮሌጅ ኢምፔሪያል ኮሌጅ  እና ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የተሰባሰቡ የጥናት ቡድኖች እንደሚሉት ይህ የምርምር ውጤት እጅግ አስቸጋሪ  እና እልህ አስጨራሽ እንደነበርም ተናግረዋል፡፡ የጨቅላ ህፃናት አእምሮ በትሪሊየኖች የሚቆጠሩ ቱቦዎችና የደም ስሮች የያዙ ሲሆኑ እስከ አሁንም...

Read More

እናቴን እየጠላኋት ነው

እናቴን እየጠላኋት ነው… ለራሴም ገርሞኛል… በዚህ ፍጥነት እዚህ ውሳኔ ላይ እደርሳለሁ ብዬ ፈጽሞ አስቤ አላውቅም ነበር… ግን ሆነ… የምወደውን ሰው ዕድሜ ልክ እንደምወደው በማመን ሞኝነት ውስጥ መክረሜ አልታወቀኝ ኖሯል… አሁን ይህን የሚያነብ ሰው ‘እምዬን?… እንዴት አስችሎህ?! ምን ዓይነቱ ደንዳና ነህ?’ ከሚል ቁጣ ጋር እንደሚጠይቀኝ አውቃለሁ… አልፈርድበትም… እናቴን ባያውቃት ነው… ያዝ… የበደለችኝን ልቁጠርልህ… ልጅ እያለሁ የሰፈራችን ልጅ እንዳልሞት እንዳልሽር አድርጎ ደበደበኝ.. ጥቃቴን ብትመልስ ብዬ ለእናቴ ነገርኳት… ደሜን ስታይ እሪ.. ብላ ጮኸች… ከዚያም የጉልቤው ልጅ ቤተሰብ ዘንድ ሄዳ ያደረገውን አሳየቻቸው… ‘አንቺ ደግሞ.. ልጆች አይደሉ እንዴ.. ነገ ዞረው ይገጥማሉ..’ ብለው አጣጣሉባት… አሁን እንዲህ ዓይነት ጥጋበኛ ቤተሰብ ሲገጥማት ምን ማድረግ ነበረባት?.. መክሰስ ወይ...

Read More

ሀይለኛ የራስ ምታት እንዲከሰት የሚያደርጉ 11 ነገሮች

በዓለማችን በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በራስ ምታት የሚሰቃዩ ሲሆን፥ ህመምተኞቹ ለራስ ምታቱ ያጋለጣቸውን ነገር በብዛት እንደማያውቁም ይነገራል፡፡ ጥናቶች ለከፍተኛ የራስ ምታት የሚያጋልጡ ምክንያቶችን ይፋ ያደሰረጉ ሲሆን፥ የራስ ምታት በጭንቀት፣ በከፍተኛ የራስ ህመም፣ እና በአዕምሮ ነርቭ ጉዳት ሊገለፅ ይችላል ይላሉ፡፡ የራስ ምታትን በመፍጠር እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማድረስ የሚከተሉትን ነገሮች ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያቶችን አቅርበዋል፡፡ 1. የህመም ማስታገሻዎችን አብዝቶ መጠቀም የህመም ማስታገሻን በብዛት መጠቀም ስቃዩን ሊቀንስ ይችላል እንጅ እንዴት የራስ ምታቱን ይጨምራል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡ ሆኖም የህመም ማስታገሻዎችን በብዛት እንደ መፍትሔነት መጠቀም ለከፍተኛ የራስ ህመም እንደሚያጋልጥ በኔዘርላንድስ የተደረገ አንድ ጥናት አመላክቷል፡፡ 2. ውሃ አብዝቶ አለመጠጣት ውሃ በብዛት አለመጠጣት አንጎል ሚዛናዊ ስራውን...

Read More

እንጆሪ ለምን ይመገባሉ?

ፍራፍሬዎች ብቻቸውንም ሆነ ከተለያዩ የምግብ አይነቶች ጋር በመቀላቀል ቢመገቧቸው በርካታ ጠቀሜታዎችን ያገኛሉ። ከጣፋጭነታቸው ባለፈ የጤና በረከቶች እንዳሏቸውም ይነገራል፤ ከፍራፍሬ ዘሮች አንዱ የሆነው እንጆሪም በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት። በቀን ስምንት ፍሬ እንጆሪን ቢመገቡ፥ ብርቱካን ተመግበው ከሚያገኙት ቫይታሚን ሲ በተሻለ መጠን ማግኘት ይችላሉ። አፕልን ሲመገቡ የሚያገኙትን የስኳር መጠን ግማሹን ያገኛሉ፣ ከሙዝ የሚያገኙትን 1/3 የካሎሪ መጠን እንዲሁም ከወይን የሚያገኙትን የአሰር መጠን በእጥፍ እንዲያገኙ ይረዳወታል። ከዚህ ባለፈ ግን እንጆሪ ቢመገቡ እነዚህን የጤና በረከቶች ያገኛሉ፤ ለልብ ጤንነት፦ እንጆሪን ብቻውንም ሆነ ከተለያዩ ምግቦች ጋር ቀላቅሎ መመገብ የልብ እና ተያያዥ የጤና እክሎችን እንዲሁም የደም ግፊትን ይቀንሳል። ምክንያቱም እንጆሪ በውስጡ ለልብ ደህንነት የሚረዱ እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ፎሌት፣...

Read More

ህጻናት አከባቶቻቸው ጋር የሚያሳልፉት ጊዜ ለአእምሯቸው ጠቀሜታ አለው- ጥናት

ህጻናት በመጀመሪያዎቹ እድሜያቸው ወራት ላይ ከአባቶቻቸው ጋር የሚኖራቸው ቆይታ ለአእምሯቸው ጠቀሜታ እንዳለው አዲስ የወጣ ጥናት አመልክቷል። በእንግሊዝ በሚገኙት የለንደን ኢምፔሪያል ኮሌጅ፣ ኪንግስ ኮሌጅ እና ኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ በጋራ የሰሩት ጥናት እንደሚያመለክተው፥ በመጀመሪዎቹ ወራት አከባታቸው ጋር ረጀም ጊዜን የሚያሳልፉ እና የሚጫወቱ ህጻናት የአእምሯቸው የመገንዘብ አቅም ከአባታቸው ጋር ከማይጫወቱት ጋር ሲነጻጸር የተሻለ ሆኖ ተገኝቷል። ጥናቱ 128 አባቶችን የተመለከተ ሲሆን፥ በጥናቱም የቤተሰቡን ገቢ፣ እድሜ፣ ቤተሰብ ከልጆቹ ጋር ያለውን ግንኙነት እና ወላጆች ልጆቻቸውን ገና በ3 ወራቸው ያለ አሻንጉሊት ማጫወትን እንዲሁም በ2 ዓመታቸው መጽሃፍ ሲያነቡላቸው አይቷል። በዚህም በአባት እና በልጅ መካከል ያለው የግንኙነት መጠን በልጆቹ አእምሮ ላይ በጎ ጎን እንዳለው መለየታቸውን ነው ተመራማሪዎቹ ያስታወቁት። ከልጆቻቸው...

Read More