Author: admin

“ስጋት” ጠቀሜታ እንዳለው ያውቃሉ…?

የአሜሪካው የካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ያወጣው ጥናት ነገሮችን መስጋት በርካታ ጠቀሜታዎች እና በጎ ጎኖች እንዳሉት ያመለክታል። ተመራማሪዎች በጥናቱ ላይ የምንሰጋ ከሆነ የተከላካይነት እና ራስን የመጠበቅ ባህሪያችን እንዲነቃቃ ከማድረግ አንጻር ያለውን ሚና ለይተዋል። በሪቨር ሳይድ ካፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ፕሮፌሰር ኬይት ስዊኒ፥ ስጋት በእኛ ላይ የሚያስከትለው መጥፎ ጎኑ እንዳለ ሆኖ መልካም ጎኖች እንዳሉት ጥናቱን በማስመልከት በሰጡት መግለጫ ላይ አስታውቀዋል። ስጋት ያለን ተነሳሽነት እንዲጨምር በማድርግ የስሜት መነቃቃትን ይፈጥራል ሲሉም ፕሮፌሰር ኬይት ተናግረዋል። ስጋት አሊያም አብዝቶ ማሰብ ከአሰቃቂ ገጠመኞች እያገገምን መሆኑን፣ ለነገሮች እቅድና ዝግጅት እደረግን መሆኑን እንዲሁም ከድብርት እያገገምን መሆኑን ሊያመላክት እንደሚችልም ጥናቱ አስቀምጧል። በጥናቱም ነገሮችን ይሰጋሉ ተብለው የተለዩ ሰዎች በስራ ቦታም ሆነ...

Read More

የጀርመኗ መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክል ከፑቲን ጋር መከሩ

) የጀርመኗ መሪ አንጌላ ሜርክል ከሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በሶቺ ተገናኝተው መክረዋል፡፡ መራሂተ መንግስቷ በሩሲያ ተግኝተው ከፑቲን ጋር ያደረጉት ውይይት ከ2015 ወዲህ የመጀመሪያቸው ነው፡፡ ሁለቱ መሪዎች በሶሪያ የእርስ በርስ ግጭትና እና በክሬሚያ ከዩክሬን መገንጠልና ወደ ሩሲያ መቀላቀልን ተከትሎ በመጣው ቀውስ ላይ ላይ እንደተወያዩ ተነግሯል፡፡ ሩሲያ ከዩክሬን ክሬሚያን ከገነጠለችበት 2014 ጀምሮ ከጀርመን ጋር ያላት ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ሻክሯል፡፡ ጀርመን የአውሮፓ ህብረት በሩሲያ ላይ ለጣላቸው ማዕቀቦች ግፊት በማድረግ ሩሲያ ጀርመንን ተጠያቂ በማድረጓ ነው ግንኙነታቸው የሻከረው፡ ሜርክል በዩክሬን ያለው ብጥብጥ እንዲቆም ሞስኮ አፍቃሪ ሩሲያውያን ተገንጣዮች ላይ ጫና እንድታሳድርና የበኩሏን ጥረት እንድታደርግ ግፊት ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ መራሂተ መንግስቷ በሶሪያ ሰላም እንዲሰፍን ሩሲያ ትልቅ ሚና እንድትጫወት ለማድረግ ፑቲንን...

Read More

ወለል ላይ ተቀምጦ የመመገብ ጥቅሞች…

እንደ አሁኑ ወንበር ተቀምጦ ከመመገብ በፊት ወለል ላይ ማዕፍድ ቀርቦ መመገብ የተለመደ ነበር። ወለል ላይ ተቀምጦ መመገብ ምንም እንኳን በምዕራቡ ዓለም የተለመደ ነገር ባይሆንም አሁንም እንደ ባህል የቀጠለባቸው አንዳንድ ሀገራት አሉ። ይህ ጥንታዊ ልማድ ከዮጋ እና ከህንዳውያን ባህላዊ ህክምና (አዩርቬዳ) ጋር ተያይዞ የመጣ ሲሆን፥ ሳይንሳዊ ጥናቶችም ጠቀሜታውን አረጋግጠዋል። እርስዎም ወለል ላይ መቀመጥ የሚመችዎ ከሆነ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ምግብዎንም ወለል ላይ ተቀምጠው ይብሉ፤ እነዚህን ጥቅሞችም ታገኛላችሁ ብሏል ቶፕ ሄልዝ ሪሜይዲስ። ወለል ላይ ተቀምጦ የመመገብ ጥቅሞች 1. እግር አቆላልፎ ወለል ላይ መቀመጥ የዮጋ ስፖርት ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤ በተለይም ከአንገት በላይ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ምቹ ነው። 2. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል 3. ከተቀመጥንበት...

Read More

በቀን 3 ሲኒ ወፈር ያለ ቡና መጠጣት የፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነትን በ50 በመቶ ይቀንሳል ተባለ

በቀን ውስጥ ሶስት ሲኒ ወፈር ያለ ቡና መጠጣት የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ ተጋላጭነትን በ50 በመቶ እንደሚከላከል ጥናት አመለክቷል። በዓለማችን ላይ ከሚገኙ ከስድስት ወንዶች አንዱ የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ የተጋለጠ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ። ሆኖም ግን በዚህ ካንሰር ከተጠቁ 36 ወንዶችው ውስጥ አንዱ ብቻ ነው ለሞት የተጋለጠው። ምክንያቱ ደግሞ ፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ ሞት እንዲከሰት በምክንያትነት ከሚቀመጡ በሽታዎች ወስጥ ሶስተኛ ደረጃን የያዘ በመሆኑ ነው። ተመራማሪዎች አዲስ አገኘነው ባሉት የጥናት ውጤት ከፌይን ንጥረ ነገርን አብዝተው የሚወስዱ ወንዶች ለፕሮስቴት ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ መሆኑን ያመለክታል። በጣሊያኑ “ኢንስቲተዩቶ ኒዮሮሎጂኮ ሜዲትሪያኖ ኔዩሮሜድ (IRCCS)”...

Read More

ሴቷ ለሴቶች ያበረከተችው የፈጠራ ሥራ

በምስሉ ላይ የሚታየው መሣሪያ በእጅ የሚሠራ የብርኬት ማምረቻ ማሽን ነው፡፡ ማሽኑ በፈጠራ መብት ባለቤቷ ወይዘሮ ስንትአበባ ፈለቀ ሰኔ 12 ቀን 2006 ዓ.ም በኢትዮጵያ አዕምሮአዊ ንብረት ጽሕፈት ቤት በአነስተኛ የፈጠራ ሥራ ዘርፍ ተመዝግቧል፡፡ በፈጠራ ባለመብቷ የተሰራው በእጅ የሚሰራ ማሽን ለማገዶ የሚውል የብርኬት ምርት ማምረቻ ሲሆን፤ ወደ ላይ አንድ ሜትር ከግማሽ፣ ወደጎን ደግሞ አንድ ሜትር በሆነ መጠን ሙሉ በሙሉ ከተቀቀለ እንጨት የተሰራው ነው፡፡ በማሽኑ ከቡና ገለባ፣ ከእንጨት ፍቅፋቂ (ሰጋቱራ)፣ ከእርሻና ከተለያየ ተረፈምርት የብርኬት ማገዶው ይመረታል፡፡ የምርት ሂደቱም ግብአቱን ወደታች ጨምቆ ማውረድ በሚያስችለው መሣሪያ ወይም ኃይድሮሊክ በመጫን ቅርፅ ይዞ እንዲወጣ በማድረግ ይከናወናል፡፡ ከተለያየ ምርት የሚገኘውን አንድ እጅ ተረፈምርት ለማጣበቂያ የሚውል አንድ እጅ...

Read More