Author: admin

ለታናሿ እንዳንሰጋ

የሴቶች ጉዳይ የማይመለከተው ሰው፣ ተቋም፣ ማህበረሰብ፣ መንግስታዊም ሆነ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ወይም አገር  የለም። ለዛም ነው የሴቶች ጉዳይ ቢሮዎች ማስፈለጋቸው፤ የለውጥ አስተባባሪና ቀስቃሽ እንዲሆኑ። ተመሳሳይ የሥራ ድርሻ ከተሰጣቸው መካከል ታዲያ የሴቶችና ህጻናት ጉዳይ ሚኒስቴር አንዱና ዋነኛው ነው። ስለዚህ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ሥራ አፈጻጸም ላነሳ አይደለም፤ ይልቁንም ከቀናት በፊት በመሥሪያ ቤቱ የተካሄደ አንድ የጥናታዊ ጽሑፍ ጉባኤ ልነግራችሁ ነው። በሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ የሴቶች ጉዳይ ማካተትና ተጠቃሚነት የማረጋገጥ ዳይሬክቶሬት የሚባል ክፍል አለ። ከዚህ ክፍል ተግባራት መካከል ደግሞ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት አንዱ ነው። ይህንንም ተከትሎ በየሁለት ወሩ የሚካሄድ የስርዓተ ጾታ ምርምር ትምህርታዊ ጉባኤ ያዘጋጃል። ይህ ቀጥሎ ዳሰሳ ያደረግንበት መድረክ ለሰባተኛ ጊዜ የተዘጋጀ ሲሆን...

Read More

የፀጉር መርገፍ እና መሳሳትን ለመከላከል የሚረዱ ምግቦች

የምንወስደው ምግብ በፀጉራችን እድገት ላይ ቀጥተኛ የሆነ አዎንታዊ ወይንም አሉታዊ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ለጤናማ የፀጉር እድገት በቫይታሚን (ኤ፣ ሲ፣ ኢ፣ ቢ5፣ ቢ6፣ እና ቢ12) እንዲሁም በዚንክ፣ ፕሮቲን፣ ሰልፈር እና ሲሊካ የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ እንደሚገባ ተመራማሪዎች ይገልፃሉ። የፀጉር መርገፍ እና መሳሳት ችግርን ለመቅረፍ ለፀጉር እንክብካቤ የሚውሉ ምርቶችን ለመግዛት ብዙ ገንዘብ ከማውጣት አመጋገባችንን ማስተካከሉ አዋጪ መሆኑንም ነው የሚናገሩት። ከዚህ በታች የተዘረዘሩት 10 የምግብ አይነቶችም የፀጉር እድገትን በማፋጠን የፀጉር መሳሳት ችግርን ያቃልላሉ ተብሏል። 1. እንቁላል ፕሮቲን ለፀጉር እድገት ቀዳሚው አጋዥ ንጥረ ነገር ነው። በመሆኑም እንደ እንቁላል ያሉ በፕሮቲን የበለፀጉ ምግቦችን መውሰድ የፀጉርን ጤንነት ለመጠበቅ ይረዳል። እንቁላል ከፕሮቲን በተጨማሪ የቢዮቲን እና የቢ ቫይታሚኖችን የያዘ...

Read More

በህዋ ላይ ለረጅም ጊዜ በመቆየት አሜሪካዊቷ የስነ ከዋክብት ተመራማሪ አዲስ ክብረ ወሰን አስመዘገቡ

አሜሪካዊቷ የናሳ ጠፈርተኛ ፔጊ ዊትሰን በህዋ ላይ ረጅም ጊዜ በመቆየት አዲስ ክብረ ወሰን ይዘዋል፡፡ እኒህ ሴት የጠፈር ተመራማሪ ዛሬ በፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በልጃቸው ኢቫንካ ትራምፕ አማካኝነት ከኦቫል ኦፊስ በቀጥታ መልዕክት ይገናኛሉ ተብሏል፡፡ ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና ልጃቸው ኢቫንካ ፔጊ ዊትሰንን እንኳን ደስ አለዎት እንደሚሏቸው ተጠቁሟል፡፡ የአሜሪካው የጠፈር ምርምር ተቋም (ናሳ) መረጃ እንደሚያሳየው ዊትሰን በጀፍ ዊሊያም የተያዘውን ለ534 ቀናት በጠፈር የቆይታ ጊዜ ነው ያሻሻሉት፡፡ ዊትሰን ህዋ ላይ በሚገኘው ዓለም አቀፉ የጠፈር የምርምር ማዕከል የደረሱት፥ በፈረንጆች ህዳር 19 ቀን 2016 ላይ ነበር፡፡ በመጪው መስከረም ወርም ወደ ምድር እንደሚመለሱ ይጠበቃል፡፡ ዊትሰን የጠፈር ምርምር ጣያቢው ሴት አስተዳዳሪ በመሆን፥ የመጀመሪያዋ ተመራማሪ ናቸው፡፡ ማዕከሉን ሁለት...

Read More

ልጆች አላስፈላጊ ይሉኝታ እንዳይሰማቸውና የበታችነት ስሜትን እንዳያዳብሩ ለማድረግ የሚረዱ ስልቶች

ልጆች የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር በቀጥታ እንዲጠይቁ እና አላስፈላጊ ይሉኝታ እንዳይዛቸው ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡ ይሉኝታ ልጆች የሚፈልጉትን ነገር በአግባቡ እንዳይናገሩ በማድረግ በአዕምሯቸው ውስጥ መጥፎ ስሜትን ይፈጥራል ይላሉ አውስትራሊያዊው የስነልቦና ምሁር ሮቢን ግሪል፡፡ ወግ አጥባቂ ቤተሰቦች በአብዛኛው ልጆቻቸው አንገታቸውን ዝቅ የሚደርጉ እና ዝምተኛ እንዲሁም ይሉኝታ ያላቸው ልጆች እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ሌላዋ የስነ ባህሪ አጥኝዋ እና ደራሲዋ ዶክተር ሊን ናምካ ይገልጻሉ፡፡ 1. በጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ጥፋተኛነት እንዳይሰማቸው እና ይሉኝታ እንዳያጠቃቸው ማበረታታት ማንኛውም ወላጅ ልጆቹን በስነምግባር የሚቀርፅበት መንገድ ልጆች ይሉኝታ እንዲኖራቸው በማህበረሰቡ ዘንድ ግብረ ገብ እንደሆኑ የሚያሳይ አስተዳደግን ይከተላል፡፡ ሆኖም በየዕለቱ በሚያከናውኑት ተግባር ስላጠፉት ጥፋት እና ስለሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ያለ ማሸማቀቅ የሚገባቸውን ጥሩ ነገር...

Read More

የትሮፒካል በሽታዎችን በማከም ረገድ አበረታች ውጤት ታይቷል-ቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን

ቸል የተባሉ የትሮፒካል በሽታዎችን ለማከም የተደረገው የመድሃኒት ስርጭት ስኬታማ መሆኑን ቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን አስታወቀ፡፡ የትሮፒካል በሽታዎች ከሚባሉት ትራኮማ፣የስጋ ደዌ በሽታ፣የጊኒዎርም፣የእብድ ውሻ በሽታና ዝሆኔ(lymphatic filariasis) ይጠቀሳሉ፡፡ መድሃኒቶቹን የማድረስ ጥረት የተጠናከረው ከአምስት አመት በፊት ለንደን ላይ ከተካሄደው ወሳኝ ጉባኤ በኋላ መሆኑም ተመልክቷል  ፡፡ በ2015 በአለም አቀፍ ደረጃ አንድ ቢሊየን ያህል ሰዎች ቢያንስ አንድ የትሮፒካል በሽታ ህክምና አድርገዋል ፤ካምፓኒዎችም ከ2012 ጀምሮ ሰባት ቢሊየን ያህል መድሃኒቶችን አሰራጭተዋል ፡፡ የውሃንና የንፅህና አቅርቦትን በማሻሻል የበለጠ ውጤት ማግኘት እንደሚቻልም የአለም ጤና ድርጅት አስታውቋል፡፡ የለንደኑ ጉባኤ ቸል የተባሉ 10 የትሮፒካል በሽታዎችን ለመቆጣጠር አልያም ለማስወገድ ቃል የተገባበት ነበር ፤ከነዚህም እኤአ በ2020 ጊኒ ዎርም ፣ሪቨር ብላይንድነስ እና ትራኮማን...

Read More