Author: admin

ትራምፕ ለውጭ አገራት የሚደረገው ዕርዳታ እንዲቀንስ ያቀረቡት ሀሳብ በሴናተሮች ተቃውሞ ገጥሞታል

አሜሪካ ለውጭ አገራት የምታደርገው እርዳታ በጀት እንዲቀንስ ሀሳብ ማቅረባቸው ከሴናተሮች ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡ የዴሞክራቲክ ፓርቲ አባል የሆኑት ሴናተር ክሪስቶፈር ኮንስ ይህን የተናገሩት የደቡብ ሱዳን ስደተኞችን ተዘዋውረው ከጎበኙ በሃላ እንደሆነ ተነግሯል፡፡ ከጥቂት ሳምንታት በፊት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራንፕ ሀገራቸው ለውጭ ሀገራት የምታደርገውን የእርዳታ በጀት በእጅጉ እንዲቀንስ መነሻ ሀሳብ ማቅረባቸው ጉዳዮ በሴናተሩ ትኩረት እንዲያገኝ ማድረጉን ዋሽንግተን ፖስት የዜና ምንጭ አስነብቧል፡፡ ሴናተሩ በደቡብ ሱዳን በአማፂያን ይዞታ ስር ባለችው ‹‹ጋንዮል›› በተባለች ከተማ ጉብኝት ስያደርጉ ሁሉም የመዲናይቱ ነዋሪዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው በመመልከታቸው ድንጋጤ እንደፈጠረባቸው ገልፀዋል፡፡ ደቡብ ሱዳን በእርስ በርዕስ ግጭት ሳቢያ በአፍሪካ ከፍተኛ የስደተኛ ቁጥር ያላት ሀገር በመሆኗ የአገራቸው መንግስት የተለየ ትኩረት ሰጥቶ ሰብዓዊ ድጋፍ...

Read More

ፍቅረኛውን ሌላ ወንድ ይዛብኛለች በሚል አሲድ ፊቷ ላይ የደፋው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ

ፍቅረኛውን ሌላ ወንድ ይዛብኛለች በሚል ምክንያት አሲድ ፊቷ ላይ በመድፋት ከፍተኛ ጉዳት ያደረሰው ግለሰብ በፅኑ እስራት ተቀጣ። ተከሳሽ ክበበው አሳየ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጓጉሳ ሽኩዳድ ወረዳ ጋጉና ማሪያም ቀበሌ ነዋሪ ነው። ከተማሪ ብርቱካን ስማቸው ጋር የትምህርት ገበታ ለመቋደስ በጋራ ወደ ትምህርት ቤት ከመመላለሳቸው የተነሳ፥ አብረው በማጥናትና ያልገባቸውን በመጠያየቅ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ መትጋትን አላማ አድርገው ተቀራርበዋል። በጊዜ ሂደትም ትምህርት፣ ጥናት እና መተጋገዝ ላይ የተመሰረተው የሁለቱ ግንኙነት አቅጣጫውን ቀይሮ ወደ ፍቅር አመራ። የተማሪዎቹ ፍቅር የግል ተበዳይ ቤተሰብን እያሳሰበ በመምጣቱ ልጃቸውን ራቅ ወዳለ ቦታ ወስዶ ማስተማርን አማራጭ አደረጉ። ለዚህም ደብረ ማርቆስ ከተማን መርጠው ተማሪ ብርቱካንም ትምህርቷን በዚያው ቀጠለች። ፍቅረኛሞቹም የቦታው ርቀት...

Read More

የአለማችን እድሜ ጠገቧ ሰው በ117 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት ተለዩ

የአለማችን እድሜ ጠገብ አዛውንት በ117 አመታቸው ከዚህ አለም በሞት መለየታቸው ተሰማ። ጣሊያናዊቷ ኤማ ሞሬኖ በሰሜናዊቷ ቨርባኒያ ከተማ በሚገኘው መኖሪያቸው ነው ያረፉት። ወይዘሮ ኤማ ሞሬኖ በፈረንጆቹ ህዳር 18 99 ተወልደው ረጅም እድሜ የኖሩ አዛውንቷ እመቤት መሆናቸውን መረጃዎች ያሳያሉ። እድሜ ጠገቧ ወይዘሮ በኖሩባቸው ጊዜያት ሁለቱም የአለም ጦርነቶች ሲካሄዱ አይተዋል። ሃገራቸው ጣሊያንንም ከ90 በላይ መንግስታት ሲመሯት ተመልክተዋል። ረጅም እድሜን ለመኖር የታደለ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን ረጅም እድሜ ለመኖራቸው ምክንያት አድርገው ይናገራሉ። ከዚህ ባለፈም ለበርካታ አመታት በቀን ሶስት እንቁላል መመገባቸው የምድራችን ረጅም እድሜ ኗሪ ለመሆን እንዳበቃቸውም ተናግረዋል። እርሳቸው ከ90 አመታት በላይ ለሆነ ጊዜ በቀን ሶስት እንቁላል እየተመገቡ ያሳለፉ ሲሆን፥ ከዚህ ውስጥ ሁለቱን በጥሬው እንደሚመገቧቸው...

Read More

የቻርሊ ቻፕሊን አድናቂዎች የዓለምን ክብረ ወሰን ለመስበር አልመዋል

በመቶዎች የሚቆጠሩ የዝምተኛው ኮሜዲያን ቻርሊ ቻፕሊን አድናቂዎች 128ኛ የልደት ቀኑን ለ25 ዓመታት በኖረበት የቀድሞ ቤቱ ውስጥ ተገኝተው ለማክበር ተሰባስበዋል፡፡ ቻፕን ትራምፕ በሚባለው ዝምተኛ እና ከቦታ ቦታ በመዘዋወር በሚታወቀው ቤት አልባው ተዋናይ ይታወቃል፡፡ በፊልሙ ውስጥ ዝምተኛው ትራምፕ በሚያደርጋቸው ድርጊቶች ብቻ የሰውን ቀልብ በመሳብ የሳቅ ምንጭም ሆኗል፡፡ በድንቅ ትወናው ዘመን ተሻጋሪ ሲሆን ዛሬም ድረስ እንደ አዲስ የኮሜዲ ፊልሞቹ ይታያሉ፡፡ ታዲያ አድናቂዎቹ በስዊዘርላንድ በሚገኘው የቻርሊ ቻፕሊን ቤት በመገኘት፥ ትራምፕ የተባለውን ገፀባህርይ ሲጫወት የለበሰውን አለባበስ ለብሰው የልደት ቀኑን ለማክበር በርካቶች ተሰባስበዋል፡፡ እነዚህ አድናቂዎቹ ከ660 በላይ ሲሆኑ በፊልሙ ውስጥ እንዳለው ትራምፕ ሁሉ ጺም አቆራረጣቸውን፣ ጥቁር ቆብ ጨምሮ ጥቁር በጥቁር መልበሳቸው፣ ከዘራ መያዛቸው፣ አካሄዳቸውን ሁሉ...

Read More

በየዕለቱ የሚደረግ ሩጫ ተጨማሪ ሰባት ሰዓት የመኖር እድልን ይፈጥራል-ተመራማሪዎች

ተመራማሪዎች በየዕለቱ ለአንድ ሰዓት የሚደረግ ሩጫ ተጨማሪ ሰባት ሰዓት በሕይወት የመኖር እድልን እንደሚፈጥር ገልፀዋል፡፡ የአይኦዋ ግዛት ዩኒቨርሲቲ በየዕለቱ ለአንድ ሰዓት የሚደረግ ሩጫ ተጨማሪ ሰባት ሰዓታትን በሕይወት የመኖር እድልን እንደሚጨምር በጥናት ደርሼበታለሁ እያለ ነው፡፡ በአሜሪካ የካርዲዮሎጂ ኮሌጅ ጆርናል ላይ የሰፈረው የዩኒቨርሲቲው ጥናት፥ በየቀኑ ከ5 እስከ 10 ደቂቃ መሮጥ በልብ እና በደም ቧንቧ ህመም ሊመጣ የሚችልን ሞት ይቀንሳል ይላል፡፡ ጥናቱ በዳላስ የኩፐር ኢንስቲትዩት የቀረበውን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ መረጃ ተንትኗል፡፡ ምርምሩ በአካላዊ እንቅስቃሴ ፕሮፌሰሩ ደክ ቹል ሊ መሪነት የተሰራ ሲሆን፥ በየዕቱ የሚደረግ ሩጫም የአንድን ሰው አስቀድሞ የመሞት እድሉን በ40 በመቶ ይቀንሳል የሚል ግኝትን ይፋ አድርጓል፡፡ በሳምንት ውስጥ ሁለት ሰዓታት የሩጫ ልምምድ ማድረግ...

Read More