Author: admin

ክህደት ከፈጸሙ ወዳጆቻችን ጋር መታማመንን እንደገና መመለስ የሚቻልባቸው ስልቶች

በጥንዶች መካከል ክህደት ተፈፅሞ ወዳጅነት ሲሻክር መተማመንን እንደገና መመለስ እንደሚቻል የስነልቦና ባለሙያዎች ይናገራሉ። ጤናማ የሆነ ወዳጅነት እና ግንኙነት አለ የሚባው ጥንዶቹ የጋራ ግባቸውን ለማሳካት በአንድ ላይ ሲሰሩ እና እርስ በርስ እየተረዳዱ ሲኖሩ ነው፡፡ መተማመን የሚመጣው በጥንዶቹ መካከል አንዳቸው ለአንዳቸው ልባዊ ፍላጎት ሲያድሩ እና ስኬታማ ግንኙነትን መፍጠር ሲቻል ነው፡፡ መተማመን ጥንዶቹ በተስፋ እንዲኖሩ፣ ህልማቸውን እውን ለማድረግ እንዲጥሩ እና እርስ በርሳቸው እየተደጋገፉ በፍቅራቸው ላይ ተጨማሪ እሴት እየፈጠሩ እንዲኖሩ ያደርጋል፡፡ በጥንዶች የኑሮ ሂደት ውስጥ የግል ጥቅም እና ፍላጎትን ብቻ ለማሟላት መሞከር ይህንንም ለዘወትር መፈጸም መተማመንን ፈተና ውስጥ ይከተዋል፡፡ የፍቅር ግንኙነት ረጅም እና ውስብስብ ነገሮችን ያቀፈ በመሆኑ፥ በጊዜ ሂደት ከጥንዶች መካከል አንዱ በሆነ...

Read More

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በ2 ሺህ ሜትር ያስመዘገበችው ክብረ ወሰን ፀደቀ

አትሌት ገንዘቤ ዲባባ በስፔን ሳባዴል በሁለት ሺህ ሜትር ያስመዘገበችው አዲስ ክበረ-ወሰን በዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ጸደቀ። የክብረ-ወሰኑን መጽደቅ ተከትሎ አትሌት ገንዘቤ የክብረወሰኖቿን ቁጥር ስድስት አድርሳለች። ገንዘቤ ጥር 30 ቀን 2009 ዓም በስፔን ሳባዴል ከተማ በተደረገው የሁለት ሺህ ሜትር የቤት ውስጥ ውድድር አዲስ ክብረ-ወሰን በማስመዝገብ ማሸነፏ ይታወሳል። ርቀቱን 5 ደቂቃ 23 ሰከንድ 75 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በመግባት ነበር ክብረወሰኑን የሰበረችው። ገንዘቤ የሰበረችው አዲስ ክብረ-ወሰን በስሟ መመዝገቡን ነው ዛሬ የዓለም አቀፍ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማህበር ይፋ ያደረገው። አትሌት ገንዘቤ በስሟ ያስመዘገበችው የ2 ሺህ ሜትር የዓለም የቤት ውስጥ ውድድር ከ22 ዓመት በፊት በአየርላዳዊቷ አትሌት ሶኒያ ኦ ሱሊቫን 5 ደቂቃ ከ25 ሰከንድ...

Read More

ኢትዮጲያን እንደሀሳብ መዝፈን ማለት ይህ ነው

ኢትዮጲያን እንደሀሳብ መዝፈን ማለት ይህ ነው ቴዎድሮስ ጸጋዬ ቴዎድሮስ ካሳሁን በአዲሱ አልበሙ ላይ ኢትዮጲያን ከየትኛውም ቀድሞ ከሚታወቅ ግለሰብ ጋር ሳያዛምድ፣ ቀድሞ ከገነነ ልዩ ክስተት ጋር ሳያገናኝ እንደጽንሰ ሀሳብ ቢዘፍናት እወዳለሁ ብዬ ነበር፡፡ እነሆ ኢትዮጲያ የተሰኘውን ዘፈን አደመጥኩ፡፡ እናም፣ የሻትኩትን አገኘሁ፡፡ ኢትዮጲያ በዚህ የቴዎድሮስ ካሳሁን ዘፈን ላይ እንደማንነት፣ እንደአገርነት ተዘፍና በመስማቴ ደስ ተሰኝቻለሁ፡፡ ኢትዮጲያ በዚህ የቴዎድሮስ ግጥም ውስጥ ከዚህ ቀደም ቴዎድሮስ ካሳሁን ከሚያደርገው በተለየ መልኩ ከግለሰቦችና ክስተቶች በላይ ልቃ፣ በረቂቅ ሀሳብነት፣ በሁለንተና ጥላነት ተገልጻለች፡፡ በብዙሀን ቤዛነት፣ በልጆቿ መስዋእትነት የተዋጀች አገር መሆኗ ተዚሟል፡፡ ኢትዮጲያ በልባችንና በነፍሳችን ያላትን ጥልቅ ትርጓሜና ተሻጋሪ አንድምታ ያነሳል ይህ የቴዎድሮስ ካሳሁን የዘፈን ግጥም፡፡ እንኳን ሰማይ ላይ ባንዲራዋን...

Read More

ቴዲ አፍሮ ግን

ቴዲ አፍሮ ግን ፣ ነገስታቱን እና ባለሟሎቻቸውን ከሚያሞካሽበት ሰዓት እና ጊዜያቱ ላይ ትንሽ ቀንሶ ለአብዛኛው እና ዝቅተኛው የህብረተሰብ ክፍል ወገናዊነቱን የሚገልጽበት ጊዜ ቢኖረው ምን ይለዋል? አዎ ፣ በቀደሙት ዘመናት የተሰሩ ጥቂት መልካም ታሪኮች ነበሩን። ሆኖም ግን ፣ ባለብዙ ብሄር ፣ ብሄረሰብ ፣ ሃይማኖቶች ፣ ቋንቋዎች ፣ ባህሎች እና የመሳሰሉ እሴቶች በእኩልነት የማይስተናገዱባት የነበረችው ኢትዮዽያ ለአብዛኛው ህዝብ የፍዳ እና የማይመች ህይወት መግፊያ ሆና መኖሯን ሳይሰማ የቀረ አይመስለኝም። ይሄንንም ስል ፣ በራሱ ሞያ አካባቢ የነበሩትን ብርቅዬ የኪነጥበብ ሰዎችን እና ታላላቅ አትሌቶችንም ህይወት ጨምሮ ፣ ከእጅ ወደ አፍ ኖሮ ደሃ ሆኖ መሞት በጣም የተለመደ እንደነበርም በማሰብ ነው። የኪነጥበብ ሰው ሆኖ የናጠጠ ሃብታም...

Read More

በጀርመን በሃይድሮጂን ሀይል የሚሰራ እና ውሃ ብቻ የሚያወጣ ባቡር ተሰራ

በጀርመን የመጀመሪያ የተባለ “ሀይድሬል“ የተሰኘ በሀይድሮጂን ኃይል የሚሰራ ባቡር ተሰርቶ የመጀመሪያ ሙከራ ተደረገ፡፡ ባቡሩ ድምጽ አልባ መሆኑን እና  አካባቢን የማይበክል መሆኑ ተነግሮለታል፡፡ አዲሱ ባቡር በዲዝል ዘይት ከሚሰራ ባቡር በ60 በመቶ ድምጹ የቀነሰ ነው ተብሏል፡፡ ባቡሩ በፍጹም ጭስ የሌለው ሲሆን ፥ብቸኛ የሚያወጣው ድምጽ የሚሰማው ከባቡሩ መዘውሮች እና የንፋስ ግፊት መሆኑን የባቡሩን ለሙከራ ያቀረበው ፈረንሳዊ አምራች አስታወቋል፡፡ “ሀይድሬል“ አሰራሩ ልክ የዲዝል ዘይት እንደሚጠቀመው ባቡር ቢሆንም ፥ለየት የሚያደርገው በዲዚል ፋንታ ሀይድሮጂንን በሃይልነት መጠቀሙ ነው፡፡ በባቡሩ አናት ላይ የሚቀመጠው የነዳጅ ማስቀመጫ ውስጥ ሀይድሮጂን እና ኦክሲጅን በማዋህድ የኤሌክትሪክ ሃይል ተለውጦ ወደ ባቡሩ ባትሪ ይገባል፡፡ በለሁለት ፍርጎው ባቡር 207 ፓወንድ ታንክ ሃይደሮጂን የሚፈልጉ ሲሆን፥ በአንድ ነጠላ...

Read More