Author: admin

‹‹ሴቶች ሁልጊዜ የተሻለ ሠርተንና ልዩ ነገር ይዘን ካልወጣን በስተቀር አስቸጋሪ ነው››

ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ፣ የእናት ባንክ የቦርድ ሊቀመንበርና የሕግ ባለሙያ ወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ ተወልደው ያደጉት በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል አሶሳ ከተማ ነው፡፡ የመጀመሪያና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን የተከታተሉትም በአሶሳ ከተማ ነው፡፡ ከፍተኛ ትምህርታቸውን ደግሞ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተከታትለው በሕግ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ወስደዋል፡፡ ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ደግሞ በኢንተርናሽናል ሪሌሽንስ  አግኝተዋል፡፡ ከአሶሳ ወጥተው አዲስ አበባ ከተማን ለመጀመሪያ ጊዜ የረገጡት አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ለመማር ተመድበው በመጡበት ጊዜ ነው፡፡ የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን ካገኙ በኋላ መጀመሪያ ወደ ሥራው ዓለም የቀላቀሉት ንግድ ሚኒስቴር ነው፡፡ ንግድ ሚኒስቴርን ከለቀቁ በኋላ በከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኛ ሆነው ሠርተዋል፡፡ ብዙም ያልገፉበትን የዳኝነት ሥራ ለቀው በሕገ መንግሥት ኮሚሽን ውስጥ ሠርተዋል፡፡ በተለይ በሕገ መንግሥት ኮሚሽን መሥራታቸው...

Read More

በሊቢያ ባህር ዳርቻ አቅራቢያ አንዲት ጀልባ ላይ በደረሰ አደጋ 97 ስደተኞች ጠፍተዋል

)ከሊቢያ ባህር ዳርቻ በሜዲትራኒያ ባህር ላይ ትጓዝ ነበረች ጀልባ ሰምጣ በትንሹ 97 ሰዎች መጥፋታቸው ተነገረ፡፡ የሊቢያ የጠረፍ ጠባቂን ጠቀሶ አልጀዚራ እንደዘገበው፥ ከሊቢያ ትሪፖሊ በ10 ኪሎሜተሮች ርቀት ላይ ጀልባዋ ከሰመጠች በኋላ 23 ስደተኞች ማዳን እንደተቻለ ታውቋል፡፡ ጀልባዋ ተለያዩ አፍሪካ ሀገራት ሰደተኞችን አሳፍራ ወደ አውሮፓ እያመራች በለበት ወቅት በድንገት ባህር ውስጥ ሰምጣለች፡፡ ከአደጋው በኋላ ሳይሰምጡ እንዳለቀረ የተጠቀሱት 97 የሚሆኑ ስደተኞች የጠፉ ሲሆን ፥ ከነዚህም 15 የሚሆኑት ሴቶች እና 5 ህጻናት እንደሚገኙበት ተጠቅሷል፡፡ እስካሁን ያልተገኙት ሰዎች የመትረፍ እድላቸው የመነመነ መሆኑ እና ፍለጋውን ለማካሄድ የአየር ሁኔታው አስቸጋሪ እንዳደረገው የሊቢያ ጠረፍ ጥበቃ ቃል አቀባይ አዮብ ቃሲም ተናግረዋል፡፡ ሊቢያ ከሜዲትራኒያ ወደ አውሮፓ የሚሸጋገሩ የ ስደተኞች...

Read More

ለምን ይሳደባሉ?

ማለዳ ተነስተው የመኪናቸውን ጎማ እየቀየሩ ነበር፡፡ ቀድሞውንም ብዙ የማይግባቡዋት ጎረቤታቸው አጠገባቸው መጥታ ምራቅ እንደተፋች ይናገራሉ፡፡ እሳቸውም በአፀፋው ሰው ፊት ምራቅ እንዲህ አይተፋም ብለዋል፡፡ ይህን ጊዜ ግን ዳግም መናገር የማይፈልጉትን ስድብ ትሰድባቸዋለች፡፡ እሳቸውም በአፀፋው በራሷ ሳይሆን በሰዎች እርጥባን እንደምትተዳደር አድርገው ይሰድቧታል፡፡ ሴትዮዋ የዛኑ ዕለት ፖሊስ ጣቢያ ሄዳ ሰድቦኛል፣ ክብሬ ተዋርዷል ብላ ትከሳለች፡፡ ከፖሊስ ጣቢያ መጥሪያ ይደርሳቸውና በተጠሩበት ቀን ይቀርባሉ፡፡ ፖሊስ ጣቢያ የተጠሩበትን ምክንያት መርማሪ ፖሊሱ አስረድቶ በእሳቸው በኩል ያለውን ይጠይቃቸዋል፡፡ እሳቸውም ስትሰድባቸው መሳደባቸውን ይናገራሉ፡፡ ግጭታችሁን በእርቅ ፍቱ የሚል ሐሳብ በፖሊሱ ሲቀርብ እሳቸው እርቁም ክሱም ይመቸኛል ቢሉም ሴቲቷ ፈቃደኛ አልሆነችም፡፡ በዚህም ምክንያት ጉዳዩ ፍርድ ቤት ይቀርባል፡፡ በፍርድ ቤት ክሱ ተነቦላቸው የሚሰጡት...

Read More

በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ሳዑዲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የምሕረት አዋጁን አለመጠቀማቸው መንግሥትን አሳስቧል

4,000 ስደተኞች ብቻ የጉዞ ሰነድ ወስደዋል የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በአገሪቱ በሕገወጥ መንገድ ኑሯቸውን የሚገፉ የውጭ ዜጎችን በተመለከተ ያወጣውን የምሕረት አዋጅ፣ በመቶ ሺሕ የሚቆጠሩ ኢትጵያውያን እየተጠቀሙበት ባለመሆኑ የኢትዮጵያ መንግሥትን በእጅጉ አሳስቦታል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲሱ ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ለመጀመሪያ ጊዜ በጽሕፈት ቤታቸው ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ፣ የአገሪቱን ወቅታዊ የዲፕሎማሲ ሁኔታ አብራርተዋል፡፡ በተለይ በቅርቡ የሳዑዲ ዓረቢያ መንግሥት በሕገወጥ መንገድ የሚኖሩ ስደተኞችን በተመለከተ ያወጣውን አዋጅ አስመልክተው ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ በሳዑዲ ዓረቢያ የመኖሪያና የሥራ ፈቃድ ሳይኖራቸው የሚኖሩ የውጭ ዜጎች ከመጋቢት 21 እስከ ሰኔ 20 ቀን 2009 ዓ.ም. ያለምንም ቅጣትና መዋከብ፣ እንዲሁም የጣት አሻራ መስጠት ሳያፈልጋቸው በተቀመጠው የ90 ቀናት የጊዜ ገደብ እንዲወጡ የአገሪቱ...

Read More

የስድስት ወሯ ነፍሰ ጡር በሠራተኛዋ ተገደለች

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የበረራ አስተናጋጅ የነበረችውና የስድስት ወራት  ነፍሰጡር መሆኗ የተገለጸው የ29 ዓመት ወጣት ወ/ሮ ሔዋን ሳህሌ፣ በሠራተኛዋ በደረሰባት ድብደባ ተገደለች፡፡ በቦሌ ክፍለ ከተማ ደሳለኝ ሆቴል አካባቢ ነዋሪ የነበረችው ወ/ሮ ሔዋን ትዳር ከመሠረተች ስድስት ወራት እንደሆናትና የስድስት ወራት ነፍሰጡር መሆኗን የገለጹት የአካባቢው ነዋሪዎች፣ በተጠርጣሪ ሠራተኛዋ ተደብድባ ግድያ የተፈጸመባት መጋቢት 28 ቀን 2009 ዓ.ም. ከምሽቱ 12 ሰዓት አካባቢ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ ሠራተኛዋ የግጭታቸውን ምክንያት ገና በግልጽ ባትናገርም፣ ‹‹ተጋጨንና ገደልኳት›› በማለት በቁጥጥር ሥር በዋለችበት ወቅት ለፖሊስ መናገሯን በሥፍራው የነበሩ ሰዎች ተናግረዋል፡፡ ሠራተኛዋ ለቤት ውስጥ ማሞቂያ (ቺሚኒ) የተዘጋጀ ፍልጥ እንጨት በማንሳት፣ የሟችን ጭንቅላት ደጋግማ በመምታት ሕይወቷ እንዲያልፍ ካደረገች በኋላ በግቢው ውስጥ በሚገኝ ጢሻ...

Read More