በአዲስ አበባ በተለምዶ ቆሼ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ የተከመረ ቆሻሻ በ15 መኖሪያ ቤቶች ላይ ተደርምሶ እስካሁን የ35 ሰዎች ህይወት አለፈ።
የአዲስ አበባ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ባደረሰን መረጃ፥ በአካባቢው ለረጅም ጊዜ ተከምሮ የነበረው ቆሻሻ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በአካባቢው በሚገኙ ቤቶች ላይ ተደርምሶ ጉዳት አድርሷል።
ትናንት በምሽት በደረሰው አደጋ ከሞቱት በተጨማሪም በ37 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የአካል ጉዳት መድረሱንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአለርት ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።