ፍራፍሬዎች ብቻቸውንም ሆነ ከተለያዩ የምግብ አይነቶች ጋር በመቀላቀል ቢመገቧቸው በርካታ ጠቀሜታዎችን ያገኛሉ።
ከጣፋጭነታቸው ባለፈ የጤና በረከቶች እንዳሏቸውም ይነገራል፤ ከፍራፍሬ ዘሮች አንዱ የሆነው እንጆሪም በርካታ የጤና ጠቀሜታዎች አሉት።
በቀን ስምንት ፍሬ እንጆሪን ቢመገቡ፥ ብርቱካን ተመግበው ከሚያገኙት ቫይታሚን ሲ በተሻለ መጠን ማግኘት ይችላሉ።
አፕልን ሲመገቡ የሚያገኙትን የስኳር መጠን ግማሹን ያገኛሉ፣ ከሙዝ የሚያገኙትን 1/3 የካሎሪ መጠን እንዲሁም ከወይን የሚያገኙትን የአሰር መጠን በእጥፍ እንዲያገኙ ይረዳወታል።
ከዚህ ባለፈ ግን እንጆሪ ቢመገቡ እነዚህን የጤና በረከቶች ያገኛሉ፤
ለልብ ጤንነት፦ እንጆሪን ብቻውንም ሆነ ከተለያዩ ምግቦች ጋር ቀላቅሎ መመገብ የልብ እና ተያያዥ የጤና እክሎችን እንዲሁም የደም ግፊትን ይቀንሳል።
ምክንያቱም እንጆሪ በውስጡ ለልብ ደህንነት የሚረዱ እንደ ቫይታሚን ሲ፣ ፎሌት፣ አሰር፣ ፖታሺየም እና መሰል ንጥረ ነገሮችን በውስጡ ይዟል።
የተደረጉ ጥናቶች በሳምንት ውስጥ በዛ ላለ ጊዜ እንጆሪ የሚመገቡ ሴቶች ከማይመገቡት ይልቅ በ30 በመቶ የልብ ህመም ተጋላጭነታቸውን ይቀንሳሉ።
ለአዕምሮ ንቃት፦ ሌላው ጠቀሜታው ደግሞ በእድሜ የማይገደብ የአዕምሮ ንቃትን እንዲያገኙ ማስቻሉ ነው።
እንጆሪ በውስጡ የያዘው ፍላቮኖይድስ የተሰኘ ንጥረ ነገር በአዕምሮ አካባቢ የሚፈጠርን እብጠት እና የአንጎል ክፍል አካባቢ የጤና እክልን መከላከል ይችላል።
ይህም ለአዕምሮ ጤና መቃወስ የሚዳርጉ አጋጣሚዎችን ይቀንሳል፥ ከከፍተኛ ጭንቀትም ይከላከላል።
ጥናቶችም እንጆሪን ከተለያዩ ምግቦች ጋር አዋህዶ መመገብ በእድሜ መግፋት የሚመጣውን የአዕምሮ ንቃት እና የማስታወስ ችግር በ2 ነጥብ 5 አመት እንደሚቀንስ ያሳያሉ።
ካንሰርን ለመከላከል፦ በውስጡ የያዘቸው እንድ አሰር፣ ፎሌት፣ ቫይታሚን ሲ፣ ኢላጂክ አሲድ እና ፍላቮኖይድስ የተሰኙ ንጥረ ነገሮች የሰውን ልጅ በካንሰር የመጠቃት እድል በእጅጉ ይቀንሳሉ።
ንጥረ ነገሮቹ ከፍተኛ ከሆነ ጭንቀት እና በሰውነት ውስጥ በሚፈጠር እብጠት እና መሰል አጋጣሚዎች የሚመጣን የነርቭ እና ህዋሳት መደንዘዝና መሞት እንደሚከላከሉም ነው ተመራማሪዎቹ የሚገልጹት።
በእንስሳት ላይ በተደረገ ጥናትም ሁለቱ ውጤቶች ታይተውበታል።
ለጨጓራ ተስማሚና ቀላል መሆናቸው፦ ከማንኛውም አይነት ምግብ ጋር ቀላቅለውም ሆነ በጥሬው ቢመገቧቸው ሆድን የማያስጨንቁና ቀላል መሆናቸውም ተመራጭ ያደርጋቸዋል።
ይህም በከፍተኛ የመጥገብ ስሜት የሚፈጠር ምቾት ማጣትን ለመቀነስ ይረዳል።
ምንጭ፦ webmd.com/