በየ ዓመቱ በሚካሄደው የዓመቱ ምርጥ መምህር ሽልማት ካናዳዊቷ ማጂ ማክዶኔል የዓመቱ ምርጥ መምህር ተብላ የ1 ሚሊዮን ዶላር አሸናፊ ለመሆን በቅታለች፡፡በውድድሩ ከተለያዩ አህጉራት የተወጣጡ 20ሺህ መምህራን ተሳትፍዋል፡፡ህልሜ አካባቢ ጥበቃን መሰረት ያደረገ የአኗኗር ዘይቤ ያለው ትውልድ መፍጠር ነው ስትል ተሸላሚዋ ማጂ ተናግራለች፡፡
ተሸላሚዋ ማጂ በካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ትሪዶ የመጪውን ዘመን ቀራጭ ተብላ ተሞካሽታለች፡፡በአርክቲክ በረዶ አካባቢ የሚኖሩ ህፃናትን ፈጠራ በታከለበት መንገድ ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ ማድርጓ የተሸላሚዋ ልዩ ጥረት ተብሏል፡፡ልማቱን ያበረከተው አከባቢና ትምህርት ጥራት የሚሰራው ቫርኪ ፋውንዴሽን የተባለ ድርጅት ነው፡፡
ምንጭ፡-ዩሮ ኒውስ