እንደ አሁኑ ወንበር ተቀምጦ ከመመገብ በፊት ወለል ላይ ማዕፍድ ቀርቦ መመገብ የተለመደ ነበር።
ወለል ላይ ተቀምጦ መመገብ ምንም እንኳን በምዕራቡ ዓለም የተለመደ ነገር ባይሆንም አሁንም እንደ ባህል የቀጠለባቸው አንዳንድ ሀገራት አሉ።
ይህ ጥንታዊ ልማድ ከዮጋ እና ከህንዳውያን ባህላዊ ህክምና (አዩርቬዳ) ጋር ተያይዞ የመጣ ሲሆን፥ ሳይንሳዊ ጥናቶችም ጠቀሜታውን አረጋግጠዋል።
እርስዎም ወለል ላይ መቀመጥ የሚመችዎ ከሆነ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ምግብዎንም ወለል ላይ ተቀምጠው ይብሉ፤ እነዚህን ጥቅሞችም ታገኛላችሁ ብሏል ቶፕ ሄልዝ ሪሜይዲስ።
ወለል ላይ ተቀምጦ የመመገብ ጥቅሞች
1. እግር አቆላልፎ ወለል ላይ መቀመጥ የዮጋ ስፖርት ለማድረግ ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል፤ በተለይም ከአንገት በላይ እንቅስቃሴዎችን ለማድረግ ምቹ ነው።
2. የምግብ መፈጨትን ያፋጥናል
3. ከተቀመጥንበት ወለል ያለምንም የእጅ ድጋፍ መነሳት ረጅም እድሜ ለመኖር ያግዛል።
በ2012 በኢሮፒያን ጆርናል ኦፍ ፕረቨንቲቭ ካርዲዮሎጂ የታተመ ጥናት፥ ከተቀመጡበት ያለምንም የእጅ ድጋፍ መነሳት ለረጅም አመታት በህይወት ከመቆየት ጋር ግንኙነት እንዳለው አመላክቷል።
ጥናቱ እንደሚለው ከተቀመጡበት ለመነሳት የሰውነታ መተጣጠፍ እና ጥንካሬን ይፈልጋል።
4. የሰውነት ጥንካሬ እና የመተጣጠፍ ብቃትን ይጨምራል
5. የተስተካከለ የሰውነት ገፅታ ያላብሳል፤ ተቀምጦ መመገብ የሰውነት አቋምን ወዲያውኑ ያስተካክላል።
6. የደም ዝውውርን ያፋጥናል፤ በተለይም የደም ዝውውር ችግር ያለባቸው ሰዎች ወለል ላይ ተቀምጠው ቢመገቡ ይመከራል።
7. ክብደትን ለመቀንስ ይረዳል
ወለል ላይ ተቀምጦ መመገብ አዕምሮን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎችን የማረጋጋት ሚናው ከፍ ያለ ነው።
የተረጋጋ ሰውነት ደግሞ የምንመገበውን ምግብ መጠን ለመወሰን የማንቸገር በመሆኑ ከልክ በላይ እንዳንመገብ ያደርጋል።
8. ቤተሰባዊ ወዳጅነትን ይጨምራል
ከቤተሰብ ጋር ወለል ላይ ተቀምጦ ምሳ ወይም ራት መመገብ ከቤተሰብ አባላት ጋር ልዩ የሆነ ግንኙነት ለመመስረት ያግዛል።
ከልጆች ጋር እኩል ወለል ላይ ተቀምጦ መመገብ በቀላሉ ከእነርሱ ጋር ለመግባባት እና ስሜት እና ፍላጎታቸውን ለመረዳት እንደሚያግዝም ነው መረጃዎች የሚያሳዩት።
በአጠቃላይ ወለል ላይ ተቀምጦ መመገብ አዕምሯችን እና የተለያዩ የሰውነት ክፍሎቻችን ዘና እንዲሉ በማድረግ ጥሩ ስሜት ይፈጥራል ተብሏል።
ምንጭ፦ http://journals.sagepub.com/ እና www.top10homeremedies.com/