ዜድ ቲ ኢ በዓለም የመጀመሪያውን የ5ኛ ትውልድ የሆነ በሰከንድ አንድ ጊጋ ባይት የማውረድ አቅም ያለው ስማርት ስልክ አስተዋወቀ፡፡
የፈረንጆች 2020 ሲደርስ የዓለም ትውልድ መረጃዎቹን በአምስተኛ ትውልድ በደረሰ የኔትወርክ አቅም አሁን ያለውን ገመድ አልባ የመረጃ ማስተላለፊያ መንገድ ይቀይራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንደ ኖኪያ፣ ሳምሰንግ፣ አልካቴል ያሉ የስማርት ስልክ አምራቾች በእርግጥ በከፊልም ቢሆን የአምስተኛ ትውልድ የቴክኖሎጂ እድገት ላይ ደርሰዋል፡፡
በቅርቡም የቻይናው የስማርት ስልክ አምራች ዜድ ቲኢ በባርሴሎና በዓለም አቀፉ ሞባይል ኮንፈረንስ ላይ አምስተኛ ትውልድ የኔትወርክ አቅም ያለው ስማርት ስልኩን አስተዋውቋል፡፡
ስልኩ በመረጃ ማውረድ ፍጥነቱ የተነሳ ˝ጊጋ ባይት ስልክ˝ የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፥ አንድ ጊጋ ባይት መረጃን በሰከንድ የማውረድ (download) አቅም ያለው የመጀመሪያው ስልክ ተብሏል፡፡
ይህም አሁን ያሉት የኣራተኛ ትውልድ የቴክኖሎጂ እድገት የደረሱ ቀዳሚ ስማርት ስልኮች ከሚያወርዱበት በ10 እጥፍ የሚፈጥን መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
ይህ የዜድ ቲ ኢ ስማርት ስልክ ያልተፈለጉ መረጃ የማውረድ ሂደቶችን የሚከላከሉ እና ለጠለፋ የሚያጋልጡ መተግበሪያዎች ተግባር ላይ እንዳይውሉ በራሱ በተሰራለት መተግበሪያ ይከላከላል ተብሏል፡፡
ለመደበኛ አገልግሎት በተገጠሙ የኢንተርኔት ገመድ አልባ ኔትወርኮች ማውረድ የማይቻሉ ከፍተኛ የኔትወርክ አቅም የሚጠይቁ ምስሎችን እና ሙዚቃዎችን የማውረድ አቅም አለው ነው የተባለው፡፡
ስልኩ ሙሉ የኤል ቲ ኢ ወይም ከፍተኛ የሞባይል ኔትወርክ አቅምን የሚጠቀሙ የአገልግሎት ክፍሎች እና መተግበሪያዎች ባለቤትም ነው፡፡
ምንጭ፡- www.techworm.net