ሞሮኮ በ2017 የዓለም የደስተኞች ሀገራት ሪፖርት ላይ 84ኛ ደረጃ ነው የተሰጣት፡፡ሆኖም ይህን ደረጃ ለማሻሻል ወጣቶቿ ብዙ እየጣሩ ሲሆን በስራቸው “የደስተኛነት ወታደሮች” ተብለዋል፡፡የ20 ዓመቱ አነስ ኤል ሃዲ የሰዎችን አዎንታዊ አስተሳሰብ በዓለም እንዲሰርፅ ከሚፈልጉት ወጣቶች አንዱ ነው፡፡
ከጓደኞቹ ጋር በመሆንም በሞሮኮ በተለያዩ ምክንያች የተደበሩ ሰዎች ዘና እንዲሉ እየሰሩ ነው፡፡ሃዲ እንደሚናገረው በማህበራዊ የትስስር ገጾች የሚለቀቁ ምስሎችና የሚራመዱ ሃሳቦች ሰዎችን ለማህበራዊ ቀውስ እየዳረጉ ናቸው፡፡በመሆኑም በሳይበር ጥቃት እነዚህን ሃሳቦችን የሚያራምዱ ሰዎችን ለመታገል ወስነናል ነው ያለው ሃዲ፡፡
በሌላ በኩል የደስተኛነት ወታደር የተባሉት ወጣቶቹ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ለድብርት የተጋለጡ ሞሮኳውያን ከዚህ አዚም የሚወጡበትን መንገድ ለማመቻቸት ዘና የሚያደርጉ የመድረክ ቲያትሮችን እያዘጋጁ ያሳያሉ፡፡እንደ ፎረም ትያትር ታዳሚዎችም እንዲሳተፉ ያደርጋሉ፡፡
አካል ጉዳተኛ ህጻናትን እና የአካል ጉዳት የሌለባቸውን ልጆች በአንድ መድረክ በማሳተፍም አዎንታዊነት ነፍስ እንዲዘራ እያደረግን ነው ይላሉ ወጣቶቹ፡፡በእነዚህ ስራዎች ራሳቸውን ለማጥፋት የወሰኑ በርካታ ተስፋ የቆረጡ ሰዎችን መታደጋቸውን ገልፀዋል።የደስታ እና የስኬታማነት ማህበሩ መስራች ኢድሪስ ካቲብ ሀሳባችን ሰዎች አዎንታዊ አስተሳሰቦችን እንዲቀበሉ እና በተግባር እንዲፈፅሙ ማድረግ ነው ብሏል፡፡