በበርካታ ደቡብ አፍሪካውያን ልብ ውስጥ ያለ እድሜዋ እርጅናን በመጋፈጥ የምትታወቀው ኦንትላሜስ ፋላስ በ18 ዓመቷ ከዚህ ኣለም በሞት ተለይታለች።ሃኪሞች ኦንትላሜስ ፋላስ ያለእድሜዋ ያጋጠማት እርጅና ከ14 ዓመት በላይ በሕይወት እንዳትኖር ያደርጋታል ብለው ነበር፡፡የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚዳንት ጃኮብ ዙማ ለኦንትላስ ቤተሰቦች የሞት ሀዘን በመላክ የቀደማቸው የለም፡፡ሟቿ በጓደኞቿ እና በቤተሰቦቿ ዘንድ “ቀዳማዊት እመቤት” የሚል ስያሜም ተሰጥቷት ነበር፡፡
የደቡብ አፍሪካው ኢንካ መገናኛ ብዙኃን የሀገሪቱ የመልካምነት ሻምፒዮን ብሏታል፡፡ቤተሰቦቿም ሃላሰን ለማዳን ላደረጉት ከፍተኛ ጥረት ሁሉ አመስግነው “በጣም ትናፍቂናለሽ፤ ነፍስሽን በገነት ያኑራት” ብለዋል፡፡
ኦንትላሜስ ባለፈው ወር 18ኛ ዓመት የልደት በዓሏን ጃኮብ ዙማ በተገኙበት ያከበረች ሲሆን በዘር መዛባት ምክንያት ለሚከሰት ያለ እድሜ የማርጀት ክስተት የተጋለጠች ብቸኛዋ ጥቁር ሴት ነች፡፡የዘረመል መዛባት (ፕሮጀሪያ) የሚያስከትለው ያለእድሜ እርጅና ከ4 ሚሊየን ሰዎች ውስጥ በአንዱ የሚከሰት ነው።ለዚህ ክስተት የተጋለጠ ሰው በአማካይ በሕይወት የመቆየት እድሉ 13 ዓመት ነው።