ልጆች የሚፈልጉትን ማንኛውንም ነገር በቀጥታ እንዲጠይቁ እና አላስፈላጊ ይሉኝታ እንዳይዛቸው ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
ይሉኝታ ልጆች የሚፈልጉትን ነገር በአግባቡ እንዳይናገሩ በማድረግ በአዕምሯቸው ውስጥ መጥፎ ስሜትን ይፈጥራል ይላሉ አውስትራሊያዊው የስነልቦና ምሁር ሮቢን ግሪል፡፡
ወግ አጥባቂ ቤተሰቦች በአብዛኛው ልጆቻቸው አንገታቸውን ዝቅ የሚደርጉ እና ዝምተኛ እንዲሁም ይሉኝታ ያላቸው ልጆች እንዲሆኑ እንደሚያደርግ ሌላዋ የስነ ባህሪ አጥኝዋ እና ደራሲዋ ዶክተር ሊን ናምካ ይገልጻሉ፡፡
1. በጥቃቅን ጉዳዮች ሁሉ ጥፋተኛነት እንዳይሰማቸው እና ይሉኝታ እንዳያጠቃቸው ማበረታታት
ማንኛውም ወላጅ ልጆቹን በስነምግባር የሚቀርፅበት መንገድ ልጆች ይሉኝታ እንዲኖራቸው በማህበረሰቡ ዘንድ ግብረ ገብ እንደሆኑ የሚያሳይ አስተዳደግን ይከተላል፡፡
ሆኖም በየዕለቱ በሚያከናውኑት ተግባር ስላጠፉት ጥፋት እና ስለሚፈልጉት ማንኛውም ነገር ያለ ማሸማቀቅ የሚገባቸውን ጥሩ ነገር ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
ለአብነትም ትምህርት ቤት ሲሄዱ እቃ ቢጠፋባቸው ወይም ቤት ውስጥ ጥፋት ቢጠፉ ለምን ጣልክ ወይም ለምን አጠፋህ ብሎ ከመቆጣት ይልቅ እቃው እንደሚገኝ እና ሆን ብለው እንዳላጠፉ ወደፊትም ማጥፋት እንደሌለባቸው መምከር ተገቢ ነው፡፡
2. ወላጆች ልቻቸውን በሚፈልጉት መልካም የባህሪ አርዓያ መቅረፅ
ልጆች በማህበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት ያላቸውን የሕይወት መርሆች እና የስነምግባር እሴቶች እንዲንጸባርቁ እና እንዲላበሱ የወላጆች ሚና ከፍ ያለ ነው፡፡
በዚህም ሰዎችን አክባሪነትን ማወቅ ስለሚፈልጉት ጉዳይ በግልጽ ጠያቂነትን እና በጎ ተግባር አደርጊነተን ከወላጆቻቸው መማር ይርባቸዋል፡፡
ለዚህም ወላጆች ልጆቻቸው በራሳቸው የሚተማመኑ እና ድብቅ እንዳይሆኑ በተጨማሪም በሰዎች ዘንድ ምስጉን የሚያደርጓቸውን ከአላስፈላጊ ይሉኝታ እንዲርቁ ማድረጋቸው መልካም ይሆናል፡፡
3. በማንኛውም ጉዳይ ላይ ውይይትን ማድረግ
ሚስጥራዊነት ወይም ድብቅ መሆን ይሉኝታን ያስፋፋል፤ ይሉኝታም ሚስጢራዊ ወይም ድብቅ መሆንን ያመጣል፡፡
ወላጆችም ማንኛውንም ነገር ከልጆች በተሰወረ መንገድ ለብቻቸው የሚያደርጉ እና የሚወያዩ ከሆነ ድብቅነትን ለነገ ተተኪዎቻቸው እያስተማሩ ነው ማለት ነው፡፡
በመሆኑም ወላጆች እና ልጆች በጋራ ጉዳዮች ላይ በተለይም በታዳጊዎች አዕምሮ ላይ ተፅዕኖ በሚፈጥሩ አካላዊ፣ ስነልቦናዊ፣ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚዊ እና ባህላዊ ትስስሮች ላይ በግልጽ መወያየት አለባቸው፡፡
4. ልጆች በየዕለቱ ባህሪያዊ መሻሻል እንዲያመጡ ጠበቅ ያለ አወንታዊ ጫና ማድረግ
ልጆች በራሳቸው መንገድ የባህሪ እድገት ወይም ለውጥ ማስመዝገባቸውን የሚያሳዩ ስራዎችን ሲያከናውኑ ወላጆች ብርታትን ሊጨምሩላቸው እና ገደብ ያለው አድናቆትን ሊቸሯቸው የግድ ነው፡፡
ይህ እንዲሆንም ወላጆች ይሉኝታቢስነትን ለልጆች በማያላብስ መልኩ መልካም ተግባራትን እንዲያከናውኑ የሚፈልጉት ጥያቄ ካለ እንዲጠይቁ፣ መስራት የሚፈልጉትን ስራም ያለ ፍርሃት እንዲከናው ጫና ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
ልጆች ይህን ተግባር በየዕለቱ እንዲያደርጉ እና እንዲለማመዱ ከተደረገ በራስ መተማመናቸው ይጨመራል፤ ስህተቶች እንዳይፈጠሩ ጠንቃቃ ይሆናሉ፤ ግልጽ እና ፍላጎታቸውን ወይም አቋማቸውን በግልፅ የሚያንጸባርቁ ይሆናሉ፡፡
5. ልጆች ሲያጠፉ አላስፈላጊ ቅጣት ከመስጠት መቆጠብ
ህጻናት በአዕምሯዊ እና አካላዊ እድገት ሂደታቸው በርካታ ጥፋቶችን ሊያጠፉ ይችላሉ፡፡
ይህ የሚሆነው የልጅነት የእድገት ደረጃቸው ስለሚያስገድዳቸው ሲሆን፥ በየደረጃውም በወላጆች ዘንድ ነውር የሆኑ ተግባራትን የማድረግ አዝማሚ በልጆች ላይ ሊንጸባረቅ ይችላል፡፡
እንደዚህ ዓይነት ነገሮች ሲከሰቱ ወላጆች መጥፎነቱን በሚገባው ምልኩ በማሳየት እና በማስረዳት ሊከለክሏቸው ይገባል።
አጥፍተው ሲያገኟቸውም ከመቅጣት ይልቅ ያደረጉት ነገር በእነርሱ ላይ ጉዳት እንደሚያመጣ፣ ሰው ቢያውቅባቸው እንደሚቀየማቸው መናገር ተገቢ ይናል፡፡
በለስላሳ እና በመውደድ ንግግር ልጆች ትክክለኛውን ከስህተቱ፣ መጥፎውን ከመልካሙ እንዲለዩ ለማድረግ መጣር ግዴታቸው ነው፡፡
ሆኖም አንዳንድ ጊዜ ወላጆች ልጆች ሲያጠፉ በስሜት ግርፋትን ጨምሮ ሌሎችንም ቅጣቶች ተግባራዊ ያደርጋሉ፡፡
ይህ ዓይነቱ ተግባር ልጆች በራስ መተማመንን እንዳያዳብሩ ሁልጊዜም ጥፋተኛ እንደሆኑ እና ራሳቸውን ያለ አግባብ ዝቅ እንዲደርጉ እና የመገለል ስሜት እንዲሰማቸው ስለሚየደርግ ወላጆች ቅጣትን ከመተግበር መቆብ ይኖባቸዋል፡፡
ምንጭ፡-ሳኮሎጂ ቱዴይ