ስሜታዊነትን መቆጣጠር ለግለሰቦች የተሰጠ መብት እና ግዴታ ነው ይላል አዲስ የተጠና ስነልቦናዊ ጥናት፡፡
በየዕለቱ የሚያበሳጩ ወይም ስሜታዊ የሚደርጉ ነገሮች ሲያጋጥሙ በደመነፍሳዊነት ስሜታዊ ምላሽ የሚሰጡ ሰዎች ለስነ ልቦናዊ ጉዳት የተጋለጡ ናቸው፡፡
ስሜታዊነትን ለመቆጣጠር በሚያግዙ መንገዶች ዙሪያ በርካታ ጥናቶች ተሰርተዋል፡፡
ሰዎች የራሳቸውን ድክመት እና ጥንካሬ ሌላ ሰው እስካልነገራቸው ድረስ በራሳቸው መንገድ ያለመለየት ባህሪ ኣላቸው፡፡
በዚህም ምክንያት ስሜታዊ የሚያደርጉ ነገሮችን ራስን ተቆጣጥሮ ችሎ ለማለፍ ይቸገራሉ፡፡
የአውበርን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪው ዳንኤል ሊ እንደሚለው ራስን መጠየቅ ስሜታዊነትን የመቆጣጠር አቅምን ያዳብራል፡፡
ይህ ራስን የመመልከቻ ጥያቄ ሁልጊዜ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ስሜታዊ ድርጊቶች ለመራቅ እና የተረጋጋ ሁኔታ እንዲኖር ይረዳል ነው የሚለው ተመራማሪው፡፡
በተፈጠረው ነገር ስሜታዊ ሆኛለሁ፣ በጣም ተበሳጭቻለሁ ወይስ ብዙ ስሜታዊ አላደረገኝም የሚሉ ጥያቄዎችን መጠየቃቸው መልካም ነው ብሏል፡፡
በመሆኑም ሰዎች ስሜታዊነታቸውን የመቆጣጠር አቅማቸውን ለመሞከር እና ለማዳበር የሚከተሉትን ዘጠኝ መንገዶች ቢከተሉ መልካም ነው ሲል በጥናቱ ጠቁሟል፡፡
1. ማህበራዊ ድጋፍን መሻት፡- ችግር ሲፈጠር ወይም ያልታሰበ መጥፎ ሁኔታ ሲያጋጥም ሰዎችን ማወያየት መልካም ነው፡፡
2. የተፈጠረውን ሁኔታ መቀበል
3. ስሜታዊነትን ሊፈጥር የሚችለው ነገር አንዲስፋፋ አለማመቻቸት
4. ለተከሰተው ችግር አዎንታዊ ምላሽ ማዘጋጀት
5. ራስን የሚረጋጉ ቀላል መፍትሔዎችን መጠቀም
6. የሌሎችን ስሜት መረዳት መቻል
7. ሌሎች ሰዎችም እኛ ልንፈጥረው በምንችለው ስሜታዊ ምላሽ ሊጎዱ እንደሚችሉ ማሰብ
8. ስሜታዊ ከሚያደርጉ ባህሪያት ለመራቅ መሞከር
9. አዕምሮ ስለስሜታዊነት እንዲያስብ አለመፍቀድ
እነኝህን ተግባራት በየዕለቱ በማከናወን ስሜታዊነትን የመቆጣጠር አቅምን ማሳደግ ይቻላል ሲል ሳይኮሎጂ ቱደይ አስነብቧል፡፡
በምህረት አንዱአለም