በቀን ውስጥ ሶስት ሲኒ ወፈር ያለ ቡና መጠጣት የወንዶች የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ ተጋላጭነትን በ50 በመቶ እንደሚከላከል ጥናት አመለክቷል።
በዓለማችን ላይ ከሚገኙ ከስድስት ወንዶች አንዱ የሽንት ፊኛ መግቢያ አፍ ላይ የሚገኝ ቱቦ ካንሰር /ፕሮስቴት ካንሰር/ የተጋለጠ መሆኑን መረጃዎች ያመለክታሉ።
ሆኖም ግን በዚህ ካንሰር ከተጠቁ 36 ወንዶችው ውስጥ አንዱ ብቻ ነው ለሞት የተጋለጠው።
ምክንያቱ ደግሞ ፕሮስቴት ካንሰር በወንዶች ላይ ሞት እንዲከሰት በምክንያትነት ከሚቀመጡ በሽታዎች ወስጥ ሶስተኛ ደረጃን የያዘ በመሆኑ ነው።
ተመራማሪዎች አዲስ አገኘነው ባሉት የጥናት ውጤት ከፌይን ንጥረ ነገርን አብዝተው የሚወስዱ ወንዶች ለፕሮስቴት ካንሰር ያላቸው ተጋላጭነት የቀነሰ መሆኑን ያመለክታል።
በጣሊያኑ “ኢንስቲተዩቶ ኒዮሮሎጂኮ ሜዲትሪያኖ ኔዩሮሜድ (IRCCS)” ተቋም በተሰራው ጥናት ላይ 7 ሺህ ወንዶች የተሳተፉ ሲሆን፥ ተሳታፊዎቹም በቀን ውስጥ ምን ያክል ቡና ይጠጣሉ የሚለውን ተመራማሪዎች በጥናቱ ወቅት ለአራት ዓመታት ተመልክተዋል።
በዚህም በቀን ውስጥ ወፈር ያለ ሶስት ሲኒ ቡና የሚጠጡ ወንዶች በቀን ውስጥ ሁለት አሊያም ምንም ቡና ከማይጠጡት ጋር ሲነጻጸሩ ለፕሮስቴት ካንሰር ተጋላጭነታቸው ከ50 እስከ 53 በመቶ ቀንሶ መታየቱን ነው ተመራማሪዎች የሚናገሩት።
ምክንያቱ ደግሞ በቡና ውስጥ የሚገኘው ካፌይን ንጥረ ነገር የፕሮስቴት ካንሰር ሴሎች እንዳያድጉ ስለሚያደርጋቸው ነው ሲሉም አብራርተዋል።
ምንጭ፦ www.dailymail.co.uk