ቻይናዊቷ በሆዷ ውስጥ እያደገ የነበረ እንጉዳይን ሀኪሞች በቀዶ ህክምና አውጥተውላታል፡፡
የ50 ዓመቷ ግለሰብ ደረቅ እንጉዳዮችን ሳታበሰብስ እና በደንብ ሳታላምጥ በመመገቧ ነው በሆዷ ውስጥ ብቅለት የጀመረው፡፡
እንጉዳዩ በሴትዮዋ አካል ውስጥ እያደገ እንደነበርም ተነግሯል፡፡
በዚህም እድገቱ 7 ሳንቲሜትር የደረሰው እንጉዳይ የጨጓራ ህመም እያስከተለ ያስቸገራት ሴትዮዋ ወደ ሆስፒታል ስትሄድ ሃኪሞቹ ባደረጉት ምርመራ እንጉዳዩ በጨጓራዋ ተንሰራፍቶ ያገኙታል፡፡
ከቀዶ ጥገና ሀኪሞቹ አንዱ የሆኑት ዶክተር ዋግ ዌይፈይ እንዳሉት፥ በምርመራቸው ወቅት በቀጭን አንጀቷ እና በጨጓራዋ መገናኛ ድንበር ላይ በርካታ የእንጉዳይ ጥርቅም ተገኝቷል፡፡
ሃኪሞቹም ባደረጉላት የቀዶ ህክምና እንጉዳዩን ሙሉ በሙሉ አውጥተውታል፡፡
ሰዎች እንጉዳይን ከመመገባቸው በፊት በውሃ በደንብ ማራስ ወይም ማበስበስ እና በደንብ አብስሎ አላምጦ መዋጥ እንደሚገባቸውም ተመክሯል፡፡
ምንጭ፡-www.dailymail.com