ዓለማችን ላይ ስልሳ ሺህ የዛፍ ዝርያዎች እንዳሉ አንድ ጥናት አስታወቀ፡፡
በአለም ላይ በሚገኙ እጽዋቶች ላይ የተደረገው አጠቃላይ ጥናት እንዳመለከተው በአለም ላይ ከስላሳ ሺ በላይ የዛፍ ፍሪያዎች ይገኛሉ፡፡
ዓለም አቀፉ የቦታኒካል አትክልት ጥበቃ ከአምስት መቶ አባል ድርጅቶቹ የሰበሰባቸው መረጃዎች ዋቢ በማድረግ ነው የዝርያ አይነቶቹን ይፋ ያደረገው፡፡
ድርጅቱ የሰባሰባቸው መረጃዎች በቁጥር አናሳ የሆኑትንና ሊጠፉ የተቃረቡትን የዛፍ ዝርያዎች በመለየትና ዝርያዎቹን ለመታደግ አስቸኳይ እርምጃ ለመውሰድ ተስፋ ሰጪ መሆኑን ገልጿል፡፡
በዘርፉ በተደረገው ጥናት መሰረት ብራዚል የ8715 የተለያዩ የዛፍ ዘርያዎች መገኛ በመሆን ትልቁን ድርሻ ይዛለች፡፡
በንፍቀ ክበብ አከባቢ የሚገኙ አገራት ምንም አይነት የዛፍ ዝርያ የሌላቸው መሆኑንና በአርክቲክ አከባቢ የሚገኙ የሰሜን አሜሪካ አገሮች ደግሞ ከ1400 በታች የሆነ የዛፍ ዝርያዎች እንዳላቸው ተገልጿል፡፡
58 በመቶ በላይ የሚሆኑት ዝርያዎች በአንድ አገር ውስጥ መገኘታቸውን የጠቀሰው መረጃው፤ እነርሱም ከደን መጨፍጨፍ ጋር በተያያዘ ለጥቃት ተጋላጭ ይሆናሉ የሚል ስጋት መኖሩን አመልክቷል፡፡
ሶስት መቶ የሚሆኑት የዛፍ ዝርያዎች በአስጊ ሁኔታ ውስጥ መሆናቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡