የአድዋ ድል እሴቶችን በበቂ ደረጃ ለአለም ለማሳወቅና የቱሪስት መስህብ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር አስታወቀ፡ሚንስቴር መስሪያቤቱ ከ121 ዓመታት በፊት ኢትዮጵያውያን በወራሪው የጣልያን ጦር ላይ የተቀዳጁትን አንፀባራቂ ድል የሚዘክር ሙዚየም እንደሚገነባም ገልጿል፡፡ድሉ የተገኘበት ስፍራ ድረስ ተገቢውን ትኩረት አግኝቶ ለቱሪስት መስህብነት እንዳልዋለ የባህል እና ቱሪዝም ሚንስትሯ ዶ/ር ሂሩት ወ/ማሪያም አስታውቀዋል፡፡ስፍራው በአድዋ የሚኮሩ ጥቁር ህዝቦች የሚጎበኙት እንዲሁም የቱሪስቶች መዳረሻ እንዲሆን ሙዚየም ተገንብቶ ለ125ኛው የድል በአል እንደሚመረቅም ሚኒስትሯ ገልፀዋል፡፡ የተለያዩ የአለም አገራት ካሏቸው የተፈጥሮ መስህቦች ባሻገር በታሪክ አጋጣሚ የተሳተፉባቸውን እንዲሁም ድል ያደረጉባቸውን የጦርነት ስፍራዎችና የተጠቀሟቸውን የጦር መሳሪያዎች በታሪክ መዝገብነት አስቀምጠው ለቱሪስት መስህብነት ይጠቀሙበታል፡፡