የ77 ዓመቷ ቻይናዊት አዛውንት ከስራቸው በጡረታ ከተሰናበቱ በኋላ 10 ሺህ ስእሎች መሳላቸውን ይናገራሉ።

ዋንግ ሞ የሚባሉት አዛውቷ እነዚህን ስእሎች በሰሜናዊ ቻይና ሁቤይ ግዛት ሺጂያዙዋንግ በሚገኘው ቤታቸው ውስጥ ነው የሳሏቸው።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጣር በ1996 ከስራቸው በጡረታ የተገለሉት ዋንግ፥ ከዚያን ጊዜ አንስቶ የሳሏቸው ስእሎችም ከ10 ሺህ በላይ መድረሱን ይናገራሉ።

wang_mo_3.jpg

ዋንግ ከስራቸው በጡረታ ከመገለላቸው አስቀድመው ለ30 ዓመታት ያክል በኢንደስትሪያል ዲዛይነርነት ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን፥ ስራቸውም በቻይና እና ከቻይና ውጭ በርካታ ሽልማቶችን እንዳስገኘላቸው ገልፀዋል።

በጊዜው ሲሰሩት የነበረው ዲዛይንም ከ200 ጊዜ በላይ የተለያዩ አውደ ርእዮች ላይ ቀርበውም ተጎብኝተዋል።

ዋንግ ይናገራሉ፥ “እኔ እና ብሩሽ ከተገናኘት ረጅም ዘመናትን አስቆጥረናል፤ ስእል መሳል ደሜ ውስጥ ገብቷል”።

wang_mo_2.jpg

በቻይና አማካኝ በጡረታ ከስራ የመሰናበቻ ጊዜ 60 ዓመት ነው፤ ሆኖም ግን በርካቶች እድሜያቸው ረጀም በመሆኑ የተነሳ ያለ ስራ ለመቀመጥ ይገደዳሉ።

በዚህ እድሜም የሚሰሩትን ማግኘት ለበርካቶች የሀገሪቱ አዛውንቶች ፈተና መሆኑ ነው የሚነገረው።

ምንጭ፦ CGTN