በዓለማችን በሚሊየን የሚቆጠሩ ሰዎች በራስ ምታት የሚሰቃዩ ሲሆን፥ ህመምተኞቹ ለራስ ምታቱ ያጋለጣቸውን ነገር በብዛት እንደማያውቁም ይነገራል፡፡
ጥናቶች ለከፍተኛ የራስ ምታት የሚያጋልጡ ምክንያቶችን ይፋ ያደሰረጉ ሲሆን፥ የራስ ምታት በጭንቀት፣ በከፍተኛ የራስ ህመም፣ እና በአዕምሮ ነርቭ ጉዳት ሊገለፅ ይችላል ይላሉ፡፡
የራስ ምታትን በመፍጠር እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ በማድረስ የሚከተሉትን ነገሮች ዋነኛ ተጠቃሽ ምክንያቶችን አቅርበዋል፡፡
1. የህመም ማስታገሻዎችን አብዝቶ መጠቀም
የህመም ማስታገሻን በብዛት መጠቀም ስቃዩን ሊቀንስ ይችላል እንጅ እንዴት የራስ ምታቱን ይጨምራል የሚል ጥያቄ ሊነሳ ይችላል፡፡
ሆኖም የህመም ማስታገሻዎችን በብዛት እንደ መፍትሔነት መጠቀም ለከፍተኛ የራስ ህመም እንደሚያጋልጥ በኔዘርላንድስ የተደረገ አንድ ጥናት አመላክቷል፡፡
2. ውሃ አብዝቶ አለመጠጣት
ውሃ በብዛት አለመጠጣት አንጎል ሚዛናዊ ስራውን እንዳያከናውን የሚያደርግ ሲሆን፥ አንጎላችን ወደ ራስ ቅል በሚንቀሳቀስበት ጊዜ በቂ ውሃ በሰውነታችን ውስጥ ስለማይኖር ጉዳት ያጋጥመውና የራስ ህመምን ይፈጥራል፡፡
3. የአቀማመጥ ችግር
የራስ ምታት በ30 ደቂቃ ወይም በአንድ ሰዓት ውስጥ ሊጠፋ የሚችል የተለመደ ህመም ነው፤ ሆኖም ዘና ሳንል ወይም ጎብጠን በምንቀመጥበት ጊዜ የራስ ምታት ይከሰታል፡፡
አንገት እና ትከሻ እንዲሰበሰበቡ በማድረግ በሚመጣ የጡንቻ መኮማተር ነው የራስ ህመሙ የሚፈጠረው፡፡
4. ምግብ አለመመገብ
ምግብ ሳይመገቡ ለብዙ ጊዜ መቆየት በደም ውስጥ የሚገኘውን የስኳር መጠን ዝቅ በማድረግ ለራስ ህመም ወይም ከፍተኛ የራስ ምታት ይዳርጋል፡፡
5. አልኮል አብዝቶ መጠጣት
አልኮል አብዝቶ መጠጣት ለስካር እንደሚዳርግ እና የአንጎልን መደበኛ ስራ እንደሚያስቀር ይታወቃል፡
እንደ ናሽናል ሄድኤክ ፋውንዴሽን መረጃ በአልኮል ውስጥ ያለው ኢታኖል የደም ቧንቧዎች እንዲሰፉ እና የደም ግፊት እንዲቀንስ ያደርጋል፤ ይህ ደግሞ ለራስ ምታት ያጋልጣል፡፡
በተጨማሪም ኢታኖል በባህሪው የሰውነት መድረቅን ያስከትላል፡፡
6. ጉንፋን
የበሽታ መከላከል ሳይንስ ምሁር የሆኑት ዶክተር ጀን ታን እንደሚናገሩት፥ በጉንፋን ምክንያት የሚመጣ የራስ ምታት ትኩሳትንም ይፈጥራል፡፡
ምክንያቱም የሰውነት የሙቀት መጠን ሲጨምር የደም ቧንቧዎች ስለሚሰፉ ውስጣዊ የራስ ምታትን እንዲፈጠር ስለሚያደርግ ነው፡፡
7. የጭንቅላት ጉዳት
የጭንቅላት ጉዳት ደረጃው ቢለያይም የተለያየ የራስ ምታት እንዲከሰት ያደርጋል፡፡
አንዳንዱ የማቃጠል፣ የማደንዘዝ፣ የትኩሳት ወይም የውጋት ስሜት እንዲፈጠር ያደርጋሉ፡፡
ይህ በሚያጋጥም ጊዜ መቀመጥ እና እረፍት ማድረግ ይመከራል፡፡
8. በእንቅልፍ ወቅት የትንፋሽ ማጠር
በእንቅልፍ ወቅት በአተኛኘት ችግር ለተወሰነ ጊዜ የመተንፈሻ አካላት በቂ አየር ሳያስገቡ ሲቀሩ፥ በደም ውስጥ ባሉት የኦክስጅን እና የካርቦን ዳይኦክሳይድ መጠን ላይ ጫና በመፍጠር የራስ ህመም ይከሰታል፡፡
9. አነቃቂ ነጥረ ነገሮችን በብዛት መጠቀም
በርካታ አነቃቂ ነገሮችን በየጊዜው መውሰድ ለተወሰነ ቆይታ፥ በኋላ የራስ ምታት እንዲፈጠር እና በድጋሚ አነቃቂ ንጥረ ነገሮችን ለመውሰድ ያስገድዳል::
ይህ ደግሞ የራስ ምታቱን ተዘውታ እና የባሰ ሁኔታ ውስት እንድንገባ ያደርጋል፡፡
10. በሴቶች ላይ የሚታዩ የሆርሞን ለውጦች
ሴቶች የወር አበባን የመሳሰሉ የሆርሞን ለውጦች በሚጋጥሟቸው ወቅት፥ የራስ ህመም ወይም ከፍተኛ የትኩሳት እና የውጋት ስሜት ፈጠርባቸዋል፡፡
11. የኮምፒውተር ስክሪን
በኮምፒውተር ስክሪን ላይ ብዙ ጊዜ ማሳለፍ በዕይታ ትኩረት ላይ በሚፈጥረው ጫና፥ የራስ ምታት እንዲከሰት ምክንያት ይሆናል፡፡
ይህን የራስ ምታት ለመቅረፍም አልፎ አልፎ እይታን ከኮምፒውተር ስክሪኖች ማሸሽ እና እረፍት ማድረግ ተገቢ ነው፡፡
በአጠቃላይ አብዛኛውን ጊዜ የራስ ምታት በማስታገሻ ወይም ራስን ከሁኔታዎች ጋር በመመለወጥ ሊድኑ ቢችሉም፥ ቶሎ የማይለቅ የራስ ምታት ሲያጋጥም ግን ወደ ህክምና ተቋም መጓዝ ይመከራል፡፡
ምንጭ፡-ዘ ሀፊንግተን ፖስት